በተለያዩ ማዕድናትና ቫይታሚኖች ማለትም አይረንና ፎሌት እንዲሁም ቫይታሚን A፣ C እና E የበለፀገ ሲሆን በተጨማሪም ከአትክልት ተዋፅኦ የሚገኝ የገንቢ ንጥረ ነገር (plant source protein) እና አሰር በጥሩ መጠን ይይዛል።
የአስምና ሌሎች ተመሳሳይ የመተንፈሻ አካላት ህመሞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር፤
በደም ውስጥ የሚገኝ የሄሞግሎቢን መጠንን በማሻሻል የደም ማነስን ሊያሻሸል ይችላል፤
ሆድን በማጠብ ለአንጀት ጤና አስተዋፅኦ ያደርጋል፤
የማስታወስ ችሎታን (memory) ያሻሽላል፤
የወር አበባ መዛባትን ያስተካክላል፤
ለቆዳና ፀጉር ጤንነት ከፍተኛ የሆነ አስተዋጾ አለው፤
የሚያጠቡ እናቶች ላይ የጡት ወተት ምርታማነተን ይጨምራል፤
የሰውነት የበሽታ መከላከል አቅምን ይጨምራል፤ የደም ስኳር መጠንን ይቆጣጠራል እንዲሁም የደም ግፊትንና ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞችን ይከላከላል።
እነዚህን ጥቅሞች ለማግኘት ፌጦን በአመት 1 ጊዜ ከመመገብ ባለፈ በሳምንት ውስጥ ከ1-2 ጊዜ 1 የሾርባ ማንኪያ ብንጠቀም በቂ ይሆናል።
References:
- http://www.webmd.com/vitamins/ai/ingredientmono-453/garden-cress&ved
- https://fppn.biomedcentral.com/articles/10.1186/s43014-022-00114-z&ved
- https://m.netmeds.com/health-library/post/garden-cress
- https://www.sciencedirect.com/science/article/pii/B9780123756886100623&ved
ኬብሮን ሠናይ (የስነ ምግብ ሕክምና ባለሙያ)
Telegram: t.me/HakimEthio