በኢትዮጵያ ኦጋዴን ሰርጥ ካሉብና ሂላል አከባቢ የሚገኘውን የነዳጅ ሃብትና የተፈጥሮ ጋዝ አውጥቼ ወደ ምርት እገባለሁ ያለው የቻይናው ነዳጅ አውጪ ካምንፓኒ Poly GCL ተመልሶ የነዳጅ ማውጣት ፍቃድ አግኝቶ ወደ ስራ መግባቱ ተነግሯል።
ይህ ኩባኒያ ረዘም ላለ ግዜ ነዳጅ በመፈለግ ስራ ላይ ተሰማርቶ ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም ባሳየው መዘግየት ምክንያ ፍቃዱ ተነጥቆ ቆይቷል። ነገር ግን ከቻይና መንግስትና ከድርጅቱ ጋር በተደረገ ዘለግ ያለ ድርድር በቀጥታ ወደ ምርት ስራ እንዲገባ ከስምምነት ተደርሶ ፍቃዱ ተመልሶለታል ተብሏል።
ከሁለት ዓመት በፊት የአሜሪካው ኔዘርላንድ ስዌል ኤንድ አሶሽትስ ኢንክ ኩባንያ ለአራት ወራት ባደረገው ጥናት፣ ለተፈጥሮ ጋዝ ሀብቱ መጠን አለም አቀፍ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ተሰጥቶ ከሰባት ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ በላይ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችትና በርካታ ቢሊየን ኪዩቢክ ድፍድፍ ነዳጅ መገኘቱ ሙሉ በሙሉ ተረጋግጧል ።
እንደሚታወቀው የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዞች ዋነኛ ስራ መኖሩንና ምንያክል መጠን መሆኑን ማረጋገጥ ሲሆን ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ለረጅም ዓመታ ” አለ” ከሚል መረጃ ያለፈ በዚህ ደረጃ ማስተማመኛ የፈጠረ በትክክል በሚታወቅ ቦታና መጠን የግኝት ስራ ተሰርቶ አያቅም።
ይህ የተፈጥሮ ጋዝ ሲወጣ ከሀገር ውስጥ ፍጆታና የውጭ ምንዛሬ ገቢነቱ ባሻገር ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመታት እጀምረዋለሁ ካለችው ለግብርናው ዘርፍ ትልቅ ስኬት ያመጣል የተባለውን የማዳበሪያ ማምረት ስራ ወደ ተግባር እንድትገባ ያደርጋታል።
የከዚህ ቀደም ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ኢትዮጵያ ከካሉብና ሂላል በሚገኘው የተፈጥሮ ጋዝ ሽያጭ ብቻ ከ8 ቢሊየን ዶላር በላይ ዓመታዊ ገቢ ማግኘት እንደምትችል ይጠቁማል።
Via ኢትዮጵያዊነት Ethiopiawinet