ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀደመው ቀያቸው እንዲመለሱ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ከወልቃይት አካባቢ የተፈናቀሉ መሆናቸውን ገልጾ ትህነግ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ዝርዝር ማቅረቡ ተገለጸ። የቀረበው ዝርዝር ተቀባይነት ማጣቱም ተመልክቷል። በሱዳን ድንበር ላይም 300 ሺህ ሰዎችን በተፈናቃይነት ተመዝግበው እንዲመለሱ ጥያቄ ቀርቧል።
ዶከተር ዳኛቸው አሰፋ ከሉዓላዊ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ይህን ዝርዝር ያቀረበው በቅርቡ በተደረገው ስምምነት መሰረት ነው።
በወልቃይት ጉዳይ ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው እየሰሩ እንደሆነና ከመንግስም ጋር ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን የጠቀሱት ዶክተር ዳኛቸው ” ትህነግ ወደ ልቦናው የተመለሰ አይመስለኝም” ብለዋል። ሲያብራሩም ተመልሰው ወልቃይት እንዲሰፍሩ ለቀረቡት ከሁለት ሚሊዮን በላይ የትግራይ ተወላጆች ወልቃይት የት፣ ከማን ጋር፣ እንዴት ይኖሩ እንደነበር አድራሻ ጠቅሶ ዝርዝሩን እንዲያቀርብ ተጠይቆ ማቅረብ እንዳልቻለ አመልክተዋል።
ከዚህ ቀደም እንደሆነው ወልቃይትን በሃይል መያዝ ፈጽሞ የሚታሰብ እንዳልሆነ ዶክተር ዳኛቸው ተናግረዋል። ዝግጅቱ ጥልቅ መሆኑንን አስረድተው የሚበጀው እውነት ላይ ተመርኩዞ በስምምነቱ መሰረት ለተግባራዊነቱ መስራት ብቻ ነው።
“ህዝብ ይተዋወቃል” የሚሉት ዶከተር ዳኛቸው ትህነግ ያቀረበውና በማስረጃ ሊደገፍ ያልቻለው ዝርዝር ተቀባይነት አላገኘም። በተመሳሳይ ሱዳን ድንበር አካባቢ 30 ሺህ የሚጠጉ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን አመልክተው ትህነግ በተመሳሳይ ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን ጠቅሶ ዳግም እንዲመለሱ መጠየቁን ገልጸዋሎኦ ይህም የሱዳንን ኮሪዶር ለመቆጣጠር ያላቸውን ፍላጎት የሚያሳይ ከመሆን የዘለለ እንዳልሆነ ጠቁመዋል።
የሱዳን ኮሪዶር የኢትዮጵያ ህልውና እንደሆነ አመልክተው፣ “በፊት የባህር በር አጣን አሁን ደግሞ የመድር ድንበርም ልናጣ ነው የሚፈለገው። ይህ ከሆነ ግብጽና ሌሎች የኢትዮጵያ ጠላቶች ይፈነጩብናል” ሲሉ የመንግስትን አቋምም አመልክተዋል።
እግረ መንገዳቸውን የራያን ጉዳይ አንስተው መንግስትን ለመን ዝመ አለ ሲሉ የወቀሱት ዶክተር ዳኛቸው ” የራያ ወጣት/ ህዝብ አሁን የት እንዳለ ታውቃለ” ሲሉ ጠይቀው፣ ” እኔ መረጃው አለኝ በቅርቡ የራያ ህዝብ ነጻ ይወጣል። የሰሞኑ ሰላማዊ ሰልፍ ምስክር ነው” ብለዋል።
ከአማራ ክልል ረብሻና አለመረጋጋት ጋር አስታከው “ፋኖን በሶስት እከፍለዋለሁ” ብለዋል ዶክተሩ። ሲያብራሩም አማራ ተበደለ ብለው የተነሱ፣ ግርገር ለሌባ ያመቻል እንደሚባለው ዝርፊያ ወስጥ ያሉ፣ መንግስት መገልበጥ አለበት የሚሉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ከመጀመሪያዎቹ ፋኖዎች ጋር መንግስት ጥያቂአያቸውን ሰምቶ ሊነጋገር እንደሚገባ ጠቁመዋል። ዘራፊ ያሉዋቸውን በህግ አግባብ ማረም እንደሚገባ ጠቁመው፣ የመንግስት ለውጥ የሚሹትን ” መብታቸው ነው ግን በጠብመንጃ አይሆንም። ህዝብ እሺ ካለ በሰላማዊ ትግል ብቻ ነው ሊሆን የሚገባው” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ትግራይ የደረሰውን ቀውስ ዘርዝረው አማራ ክልልም ወደ እዛው ለማምራት ጫፍ ላይ መድረሱን የገለጹት ዶክተር ዳኛቸው ሰላማዊ ውይይት ሊቀድም እንደሚገባ አበክረው አሳስበዋል።
በምስራቅና ምዕራብ አማራ ዞን ተማሪዎች ትምህርት ማቆማቸውን አስደንጋጭ አሃዝ ገልጾ መንግስት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ አማራ ክልል ምን ያህል ቀውስ ውስጥ እንዳለ ሰሞኑን በርካቶች እየተወያዩበት ነው። አሁን ላይ ውጊያ የሚደረገው በአገሪቱ አምራጭ አካባቢዎቾ በመሆኑና አርሶ አደሮ ማዳበሪያ እንዳይደርሰው እየተደረገ መሆኑንን ዶክተር ዳኛቸው አንስተው አስጠንቅቀዋል። ሁሉም ወገን ወደ ቀልቡ ሊመለስ እንደሚገባውም አመኦልክተዋል።