ደጅ ጥናትን እንደ ሙስና እያየን እንዴት ብለን ጉዳያችንን ልናስረዳ እንችላለን። ግብፅ እኮ አሜሪካና አውሮፓ ትልልቅ ደጅ ጠኝዎችን (lobbying power house) በሚሊዮን ዶላር ቀጥረው ጉዳያቸውን በየመስሪያ ቤቱ እየዞሩ ያስረዳሉ። መልዕክታቸውን በታዋቂ መገናኛ ብዙሃንና ተመራማሪዎች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችና ጋዜጠኞች በኩል ያስነግራሉ፣ ብሶታቸውን ያሳማሉ። ሰኔ ወር ላይ ታዋቂው Wall street journal ስለግድቡ ሁኔታ ያዝጋጀውን ዘጋቢ ፊልም ልብ ይሏል።
(የተግባቦት ድክመት ማሳያ)
ማይክ ፓምፒዮ በጋሽ ትራምፕ አስተዳደር ዘመን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፀሃፊና የሲአይኤ ዳይሬክተር ሆኖ አገልግሏል። በሪፐብሊካኖች ቤት ከፍተኛ ተሰሚነት ያለው ጉምቱ ሰው ነው። ከሶስት ቀን በፊት ትራምፕን ዳግም ዕጩ አድርጎ ባቀረበው የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ(RNC) ድስኩር ካቀረቡት ትልልቅ የፓርቲው ሰዎች መካከል አንዱ ነበር። የዘር ሃረጉ ከጣልያን ይመዘዛል።
ፓምፒዮ በትራምፕ ዘመነ መንግስት በአራት አመት ያሳለፈውን የስራ ቆይታ የሚያትት Never Give An Inch: Fighting for America I Love የተሰኘ ግለ-ታሪክ መፅሃፍ አምና-2023 አሳትሞ ለንባብ አብቅቷል።
እኔም ሃገሩን እንደሚወድ የ-OSINT ጎልጓይ ፓምፒዮ ስለኢትዮጵያ ምን ይላል የሚለውን ቀድሜ ለማየት የመፅሃፉ የቁልፍ ቃላት መጎልጎያው ጋር “ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል አስገብቸ ፈተሽኩት። ስለኢትዮጵያ 3 ገፅ ያህል ፅፏል። አንኳር መልዕክቱ የዲፕሎማሲ ጥረት ሁሌም እንደማይሳካ ማመላከቻ ነው።
ይኸውም፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅን ለማነጋገር እና የአሜሪካን ብሄራዊ ጥቅም ለማስከበር ግዴታ ስለ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ስምምነት ስለሚደርሱበት ሁኔታ ማሸማገል አስፈላጊ ነበር ይላል።
ሶስቱን ሃገራት ስለ ግድቡ ሙሌት ሁናቴ እንዲስማሙ በአሜሪካ ግምጃ ቤት በጅሩንድ አሸማጋይነት ጥረት ቢደረግም ሊሳካ አልቻለም። አስራ ሶስት (13) ወር ሙሉ ስለ አሜሪካ ጉዳይ ለመነጋገር ግዴታ ስለግድቡ ቅሬታ መቀበልና ማስተናገድ ነበረብን ይላል።
እኔን የገረመኝ ግን ፓምፒዮ ስለሕዳሴው ግድብ ያለው እይታ ነው፣ ይህም የኢትዮጵያ መንግስት አለም አቀፍ ተግባቦት ላይ ምን ያህል ደካማ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
ምን ይላል መሰላችሁ:-
The Ethiopians have been building the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) on the Blue Nile, one of the major tributaries for the Nile River. The name is outrageous, as neither will the dam guarantee an Ethiopian renaissance nor is it really all that grand, being built largely by Chinese construction companies using Chinese labor.
ግድቡ ስሙን አይመጥንም ፤ ታላቅም አይደለም፤ የኢትዮጵያን ሕዳሴንም አያረጋግጥም ይላል። እንዲሁም በአብዘሃኛው በቻይና ካምፓኒ እና የሰው ሃይል እንደሚገነባ ይገልፃል።
ፓምፒዮ ይህን ማለቱ አያስገርምም።
ይህ የራሳችንን የተግባቦት የቤት ስራ እንዳልሰራን አስረጅ ነው። የአሜሪካን አስተዳደር የተግባቦት ስርዓት አልተረዳነውም። ደጅ ጥናትን እንደ ሙስና እያየን እንዴት ብለን ጉዳያችንን ልናስረዳ እንችላለን። ግብፅ እኮ አሜሪካና አውሮፓ ትልልቅ ደጅ ጠኝዎችን (lobbying power house) በሚሊዮን ዶላር ቀጥረው ጉዳያቸውን በየመስሪያ ቤቱ እየዞሩ ያስረዳሉ። መልዕክታቸውን በታዋቂ መገናኛ ብዙሃንና ተመራማሪዎች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችና ጋዜጠኞች በኩል ያስነግራሉ፣ ብሶታቸውን ያሳማሉ። ሰኔ ወር ላይ ታዋቂው Wall street journal ስለግድቡ ሁኔታ ያዝጋጀውን ዘጋቢ ፊልም ልብ ይሏል።
እኛ ግን እንደልቡ ነን። ግድ አይለንም። ያሳዝናል።
ሌላው አስገራሚው ነገር ግንባታው በቻይናዎች የሰው ሃይል እየተገነባ እንደሆነ የገለፀው ነገር ነው። እውነት ይሆን? አይመስለኝም። የሲቪል ግንባታው በጣልያኑ ሳሊኒ እንደሚገነባ አውቃለሁ። የኤሌክትሪክ መካኒኩም በሌላ ይገነባል። ቻይናዎች ተቋራጭ ሆነው ገብተው እንደሆን አላውምቅ። ይህም አንዱ የተግባቦት ችግር ነው።
ፓምፒዮ የህዳሴው ግድብን ከላይ እንደገለፀው የኢትዮጵያን ህዳሴ እንደማያረገጥ አድርጎ ጨለምተኛ በሆነ መልኩ አይተወውም። እንደውም ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል በማመንጨት ሃገሪቷን ወደ ሌላ የኤሌክትሪክ ምዕራፍ እንደሚያሻግራት ይግልፃል፣ እንዲህ በማለት:-
But the dam is a massive structure designed to generate huge amounts of energy for Ethiopia and lift the country into a new electrified era.
ይህም ሆኖ ግድቡ በሶስቱ ሃገራት መካከል ለዓመታት የዘለለቀ የሕግ፣ የዲፕሎማሲ እና የንግድ መፋለሚያ አበይት ጉዳይ እንደነበር ይገልፃል። ሶስቱም ሃገራት ስለግድቡ ቅሬታቸውን ሳያሰሙ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ማድርግ እንደማይቻል ይገለፃል። ዋና ብሄራዊ ጥቅማቸው ስለሆነ።
የሆኖ ሆኖ የዲፕሎማሲው ጥረት ቢደረግም ስምምነት ላይ አልተደረሰም። ይህ የዲፕሎማሲ ጥረት የአሜሪካ የፀረ-ቻይና ዘመቻ ፕሮጀክት(Counter china project) አካል እንደነበር ፓምፒዮ ይገልፃል።
ማስታወሻ- ዲፕሎማሲና ዓለም አለም ዓቀፍ ግንኙነት ትምህርት መማር ብቻውን በቂ አይደለም። በተግባር የተፈተነ የሕይወት ማስታወሻዎችን ማንበብ ከንድፈ ሃሳብ የበልጠ ተጨባጭ እውቀት ያስጨብጣል። መጪውን የዓለም ጂኦፓለቲካ ሁኔታ ለመረዳት እና ቢሆኖችን ለማማዘጋጀት ይረዳል። ከፓምፒዮ ግለ-ታሪክ የተረዳሁት መጪው ዘመን(ቢያንስ ለአርባ አመት) በቻይና እና በአሜሪካ መካከል ከፍተኛ የሆነ great power strategic competition እንደሚደረግ ነው። እኛም የዚኸው አካል ነን።
ቀድሞ ማዎቅ ያሸልማል!
አትፍዘዝ
ታመጣለህ መዘዝ!