በአማራ ክልል በኤች አይቪ የተጠቁ መድሃኒት ማግኘት አልቻሉም። ህጻናት ትምህርት አቁመዋል። የስኳርና የኩላሊት በሽተኞች ስቃይ ለመናገር የሚከብድ ነው። በጦርነት ፈርሶ ያላገገመው አማራ ክልል አሁን ደግሞ ጎጃም እየወላለቀበት ነው። ህዝብ እንዳሻው መጓጓዝ ተስኖታል። የክልሉ ገቢ ሞቷል። ቱሪዝም የለም። እርሻ ተስተጓጉሏል። እናቶች በወሊድ እየሞቱ ነው። ዝርፊያ፣ እገታ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ስርዓተ አልበኛነት ወዘተ ቅጥ አጥቷል። ባለሙያዎችና ራሱ የክልሉ አመራሮች በየዘርፉ በሚያቀርቡት ሪፖርት አማራ ክልል ቢያንስ ሃያ ዓመት ወደሁዋላ ተመልሷል። ሌሎች ክልሎች በልማት እየሮጡ ነው። ለዚህ ነበር ፋኖ መሪ መርጦ ወደ ድርድር እንዲሄድ በተስፋ ሲጠበቅ የከረመው።
ማንም እየተነሳ የሚፈተፍትበት፣ ይህ ታላቅ ህዝብ ከአብራኩ ያፈራቸው አስተዋይ ልጆች የሌሉት ይመስል እዛም እዚህም የስካር ትርምስ የሚታይበት የአማራ ክልል እንቅስቃሴ፣ ሆን ተብሎ አማራ ላይ ሲደረግ የነበረውን በደልና የጅምላ ጥቃት ሊያስቀር ቀርቶ ጭራሹኑ ክልሉንም ህዝቡንም እየደፈቅ ወደ ባሰ ችግር እየከተተ ነው።
ልክ ወለጋ እንደሆነው አማራ ክልልም በደከፋ የስጋት ድወረጃ ከመድረሱ በፊት አንድ በመሆኑ በሚቻለው ሁሉ በድርድር ወደ አንድ ግብ ለመድረስ እንዲቻል ሲገፉ የነበሩ ተስፋ ያደረጉት ጉዳይ ተራ የሰበር ዜና ግብግብ ከመሆን አለማለፉ እጅግ አሳዛኝ ሆኗል። እነዚህ በሰበር ዜናና በልመና የደለቡ አካላት ስለምን ለህዝቡ፣ በተለይም ለህጻናት፣ እናቶችና አዛውንቶች ማሰብ ተሳናቸው? የሚለው ጥያቄ አሁን በተያዘው መንገድ እንኳን መልስ ሊያገኝ ፍንጭም የለም። ለዚህም ምስክሩ ስሞኑን ይፋ የሆኑት የዚዲዮ መረጃዎችና የእስክንድርን ምርጫ ተከትሎ እየወጡ ያሉት መረጃዎች ናቸው።
የአማራ ፋኖ በጎጃም፣ የወሎና የሸዋ እንዲሁም ከፊል አደረጃጀቶች በያዙት የጋራ አቋምና በተካሄደ ምርጫ “አርበኛ እስክንድር ነጋ የፋኖ መሪ ሆኗል” በሚል በደቂቃዎች ውስጥ በቅብብል ሰበር ዜና ቢገለጽም፣ አፍታ ሳይቆይ በሌላ ሰበር ዜና ” ሃሰት ነው። እናወግዘዋለን። አንቀበለውም። ሴራ ነው” በሚል በይፋ መግለጫ የሚቃወሙ ድምጻቸውን አሰምተዋል። ከሁሉም ወገን የሚወጡትን መረጃ ያደመጡ ደግሞ የአማራ ህዝብ እጣ ፈንታ በዚህ ደረጃ በሚያስቡ ወገኖች እጅ መውደቁ አሳዝኗቸዋል።

ስብሰባ ተካሂዶ እስክንድር ነጋ የፋኖ መሪ ተደርጎ መመረጡን ከሚወኩልት የፋኖ አደረጃጀት ተሰይመዋል የተባሉ በየተራ ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ ተደርጓል። ዜናውን ያወጁ እንዳሰሙት ከሆነ እስክንድርን መምረጣቸውን በደስታና በኩራት ማረጋገጣቸውን በድምጻቸው ያሰሙት የፋኖ የተለያዩ አደረጃጀቶች ናቸው ተብሏል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳስደር ኢርቪን ማሲንጋ ” የታጠቁ ኃይሎች ከውይይት ይልቅ በሁከት ፖለቲካዊ ዓላማዎችን ለማሳካት መሞከራቸው በደሎች እንዲፈጸሙ በር ይከፍታል” በሚል ንግግር ሲያደርጉ የፋኖ ሃይሎች አንድ ሆነው ለድርድር ቢዘጋጁ እንደሚያዋጣቸው መክረው እንደነበር ይታወሳል።
ይህንኑ ይተከትሎ ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ወዲያውኑ መገለጫ የሰጠው እስክንድር ነጋ፣ በአማራ ክልል ያለውን ግጭት በንግግር ለመፍታት ከመንግሥት ጋር ሊደረግ ስለሚቻልበት ውይይትን በተመለከተ “ገና ከውሳኔ አልደረስንም” ካለ በሁዋላ በየአቅጣጫው ትግል ላይ ያሉት የፋኖ አደረጃጀቶች የየራሳቸው መሪ ስላላቸው ወደ አንድ ለመምጣት ስራ መጀመሩን ሃላፊነት ወስዶ ተናግሮ ነበር።
እነዚህኑ አካላት በማሰባሰብ ወደ አንድ ለማምጣት ንግግር መጀመሩን ያስታወቀው እስከንድር ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ ከመንግሥት ጋር ሊደረግ ስለሚችል ድርድር ውሳኔ ላይ መድረስ እንደሚቻል አመልክቶም ነበር። በዚሁ ቃለ ምልልሱ “በመርህ ደረጃ ድርድር ተቀባይነት ያለው ነገር ነው” ሲል ድርድር ስለሚደረግበት አግባብ ፍንጭ አመላክቶ ነበር።በአፍሪካ ያለውን ተሞክሮ በማንሳት “ከብዙ የሰው እልቂትና የንብረት ውድመት በኋላ ተዋጊ ኃይሎች ወደ ድርድር ሲመለሱ ተመልክተናል” ሲል ድርድር አይቀሬ ጉዳይ እንደሆነ አመልቷል።
ይህ ከተባለ ጀምሮ በተለያዩ አግባቦች ፋኖ መሪና ወጥ የሆነ አደረጃጀት እንዲኖረው እየተሰራ መሆኑን ከየአቅጣጫው የሚወጡ የዩቲዩብ ወሬዎች ሲያስታውቁ ቆይተው ትናንት በሰበር ዜና እስክንድ መሪ ሆኖ መመረጡን አውጀዋል።
የሃይል አሰላለፉ ሙሉ በሙሉ ግልጽ ባይሆንም ሰሞኑን ተጠልፎ ይፋ የሆነው የጎጃም ፋኖ ቃለ አቀባይ ከሸዋ አሰግድና ከግዮን ሚዲያ ምናላቸው ስማቸው ጋር ያደረጉት ንግግር ልዩነቱ መኖሩን ከሰበር ዜናው በፊት አመልክቶ ነበር።
የፋኖ መሪና አመራሮች በምደባ እንጂ በምርጫ እንደማይሆን ይፋ ሲነጋገሩ፣ እስክንድር ነጋን እንደማይቀበሉና መሪው ዘመነ ካሴ ሊሆን እንደሚገባው ሲመክሩ በሚሰማበት የስልክ ልውውጥ የአስክንድርን ሚስጢር እንደሚዘረግፈው ምናላቸው ሲዘት ይሰማ ነበር። እስክንድር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር አጽቀ ስላሴ ጋር በስልክ ማውራቱን መረጃ እንዳገኙ ጠቅሰው ያደረጉት ውይይት ከፍተኛ የአካሄድ ግድፈትና ሚስጢር ያወጣ በመሆኑ አንድ ነገር እንደሚሰማ የገመቱ ጥቂት አልነበሩም።
ለጊዜው ግልጽ ያልሆነውና የትህነግ ደጋፊ ሚዲያዎችን ሳይቀር ጮቤ ያስረገጠው የአስክክንድር ነጋ ምርጫ ሰዓታት ሳይቆይ ከጎጃም፣ ከወሎና ከሸዋ እንዲሁም ከጎንደር ፋኖ ተቃውሞ እንደገጠመው ተሰምቷል።
የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ሰብሳቢና የጦር አዛዥ እንደሆኑ ተጠቅሰው በግዮን ሚዲያ ከምናላቸው ስማቸው ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ሻለቃ ዝናቡ ልንገርህ “በሰበር መረጃ ስም እየወጣ ያለው መረጃ የአማራን ህዝብ አይወክልም” ሲሉ ተቃውመውታል። “ትግሉን ለመጥለፍ ነው” ሲሉም አጣጥለውታል።
ምርጫ ያልተደረገበትና የግል ፍላጎት ያላቸው የተበተቡት የሴራ ፕሮፓጋንዳ እንደሆነም ገልጸዋል። የእስክንድርን ሚስጢር አደባባይ ላይ እንደሚያሰጣ ቀድሞ ያስታወቀው ምናላቸው ስማቸው ጠያቂ ሆኖ በቀረበው በዚህ ቃለ ምልልስ ሻለቃ ዝናቡ በዚህ ዓይነት ተግባር የሚሳተፉና እየተሳተፉ ያሉ ላይ ታጣቂዎቻቸው በሁሉም አደረጃጀት እርምጃ እንዲወስዱም አደራ ብለዋል።
“በብቃት፣ በቁርጠኛነት፣ እንዲፈጽሙ” ሲሉ እርምጃ እንዲወስዱ አደራና ማሳሰቢያ የሰጡ የታጣቂዎቹ መሪ በየቀጠናው ያሉ አመራሮች መመሪያ እንደተሰጣቸው ይፋ አድርገዋል።
ምናላቸው ሲያጠቃልል የሸዋውን አሰግድን፣ የወሎውን ምሬን፣ የጎንደሩን ጨምሮ በተከታታይ በቃለ ምልልስ ይዞ እንደሚቀርብ ቃለ ገብቷል። ሲጠበቅ የነበረውን የፋኖ አንድ መሆን ዜና በዚህ መልኩ ያስተባገዱ ” የጨረባ ፖለቲካኤ ሲሉ ተደምጠዋል።
አሰግድና ምሬ ጦረንት ገጥመው በርካታ ሃይል ማስፈጀታቸው መዘገቡን፣ የአሰግድ መኖሪያ ቤትን የተቆጣጠሩ የምሬ ታጣቂዎች በምስል ያሳዩት መረጃ በምሬና አስገድ መካከል ሊታረቅ የማይችል ቅራኔና ቂም እንዳለ የሚያሳይ ሆኖ ሳለ ምላላቸው ስማቸው ሁለቱን በጋራ የእስክንድር ተቃዋሚ አድርጎ ማቅረቡ ለጊዜው ግራ አጋቢ ሆኖል።
ራሱን “የማሪያም ልጅ፣ የገብርዔል ባሪያ” የሚለው ዘመዴ እስክንድር አሰቅድሞ የትግራኛ ጋዜጣ የነበረው ወያኔ መሆኑን አመልክቶ ክፉኛ ስድብ የሰነዘረ ዚሆን ከታች በምስል ካሉት የፋኖ አመራሮች ውጪ ሌሎቹ ተቀባይነት እንደሌላቸው አስታውቋል። በሻእቢያ በሚደገፈው የመረጃ ቲቪ ላይ የሚቀርበው ዘመዴ በዚህ ደረጃ እስክንድርን ሊቃወም የፈለገበት ምክንያት አይታወቅም።
በአማራ ክልል በኤች አይቪ የተጠቁ መድሃኒት ማግኘት አልቻሉም። ህጻናት ትምህርት አቁመዋል። የስኳርና የኩላሊት በሽተኞች ስቃይ ለመናገር የሚከብድ ነው። በጦርነት ፈርሶ ያላገገመው አማራ ክልል አሁን ደግሞ ጎጃም እየፈራረሰበት ነው። ህዝብ እንዳሻው መጓጓዝ ተስኖታል። የክልሉ ገቢ ሞቷል። ቱሪዝም የለም። እርሻ ተስተጓጉሏል። እናቶች በወሊድ እየሞቱ ነው። ዝርፊያ፣ እገታ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ስርዓተ አልበኛነት ወዘተ ቅጥ አጥቷል። ባለሙያዎችና ራሱ የክልሉ አመራሮች በየዘርፉ በሚያቀርቡት ሪፖርት አማራ ክልል ቢያንስ ሃያ ዓመት ወደሁዋላ ተመልሷል። ሌሎች ክልሎች በልማት እየሮጡ ነው።
በዚህና በጥቅሉ ከክልሉ በሚወጡ አስደንጋጭ መረጃዎች ሳቢያ ነበር ህዝብ የፋኖን ወደ አንድ መምታትና በድርድር አስፈላጊውን ውጤት ለማግኘት ጥረት እንዲደረግ ሲናፍቅ የቆየው። የታሰበው ሳይሆን ከጅምሩ የመሪ ስያሜው የሁለት ወገኖች የሚዲያ ፍልሚያ እንጂ ለክልሉም ሆነ ለህዝቡ ይዞት የመጣው ረብ የለም።
ትናንት አብረው ሲሰሩ የነበሩ ባልደረቦች ሁለት ጽንፍና የየራሳቸው ጋላቢ ፈጥረው ፋኖ መሪ እንዳይሰየም አድርገውታል። የግል የንግድ ተቁማቸው አድርገው የተቀራመቱዋቸውን የፋኖ መሪዎች ግንባር እያደረጉ ገንዘብ መለመኛ፣ በክልሉ የደረሰውን ጉዳይ እያሳዩና እያስለቀሱ የህዝብ ኪስ ማራቆቻ አድርገዋል። በዚህ ስልት ሃብት ሰብስበዋል። በድምና በህይወት እየነገዱ ከብረዋል። የበቁ የክልሉ ተወላጆች ወደ ትግሉ እንዳይገቡና መንገድ ጠርቅመው በመዝጋት፣ በሚዲያዎቻቸው እየተቀባበሉ ስም በማጥፋትና በማስፈራራት አዋቂዎችን አፍ አዘግተዋል። በዚህም የተነሳ ጀርባቸው ቆሻሻ፣ ልምዳቸው ክህደት፣ ግባቸው ንግድ፣ የሆኑ ምናምንቴዎች በአማራ ህዝብ ስም ፈትፋች እንዲሆኑ አድርገዋል።
ነገ በትክክል ምን እንደሚሰማ ባይታወቅም ለዛሬው የስክንድር ምርጫ ጉዳይ ለሰሞኑ መነታረኪያና ሌላ የሃብት መሰብሰቢያ ዕድል ከመሆን እንደማይዘል የታመነ ነው። የፋኖ የአሜሪካ ሰበር ዜና አያልቅምና ዲያስፖራ ኪስህን እያወለቅ ሰበር ዜና ስማ። አገርና ህዝብህን ሃብትን እያሟጠጥክ አሰቃይ፣ አፍርስ!!

በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ አንድ የአማራ ፋኖ ማእከላዊ እዝ እና ድርጅት ለመፍጠር ከሌሎች የፋኖ አደረጃጀቶች ጋር በመሆን የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ ቆይቶዋል::
በዚህ ሂደትም እጩዎችን መመልመል ላይ የደረስን ሲሆን ከ 14 ያላነሱ የመመልመያ መስፈርቶች ተዘርዝረው ግማሽና ከዛ በላይ የሆኑትን ማለፍ ያልቻለው አቶ እስክንድር ነጋ ካልተመረጠ በሚል እሱና መሰሎቹ ዉይይት እቁዋርጠው ወጥተዋል::
በመሆኑም ይህ የተጀመረ ሂደት በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ አቶ እስክንድር ነጋ በአንድ አመት ጊዜ ዉስጥ ሶስተኛዉን የፋኖ ድርጅት እንደተለመደው እራሱን ዋና አዛዥ አድርጎ መመስረቱን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰምተናል::
ስለሆነም “የአማራ ፋኖ ትግል በቀዳሚነት ለአማራ ህዝብ ህልዉና” መሆኑን ለማይቀበልና ከዚህ ሰብአዊ ትግል ስሪት ዉጭ ለሆነ በአማራ ህዝብ የህልዉና ትግልና መስዋእትነት የዘመናት የስልጣን ጥሙን ለማርካት ለተነሳ ግለሰብ አሳልፈን መስጠት እንደሌለብን ስለምንረዳ በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ በማህበራዊ ሚዲያ ከሰማነው ነውረኛ ተግባር እንደሌለበት ለህዝባችን ማሳወቅ እንወዳለን::
ከዚህ ጋር ተያይዞም በቅርቡ በእውነተኛ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች እውነተኛ የአማራ ህዝብ ቤትና ድርጅት ሰርተን እንደምንመጣ ለህዝባችን ማብሰር እፈልጋለሁ::
” አማራ በልጆቹ መስዋእትነት ይሻገራል::”
ከAbebe Yonas Fentaw

