ጥኖቶች እንሚጠቁሙት ከሆነ በ2040 ዓለም ከፍተኛ የውሃ እጥረት እንደሚገጥማት ነው:: በተለይ ለእርሻ እና ለመጥጥ የሚውል የFresh ውሃ እጥረት:: ለዚህ እጥረት መነሻው የአየር ብክለትና መዛባት ውጤት ፅዋውን ሞልቶ መፍሰስ ስጀምር መሆኑ ነው:: እሄንን ተከትሎ ከፍተኛ ሆነ የዝናብ ስርጭ መዛባትና መቆራረጥ፣ የወንዞችና ሀይቆች መድረቅ እና የከርሰ ምድር ውሃ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ከላይ የተጠቀሰው ወቅት ስደርስ ዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ የውሃ እጥረት እንድከሰት ያደርጋል::
ያ ዘመን ስመጣ የውሃ እጥረቱ ለመቅረፍ በእውቀት፣ በቴክኖሎጂና በገንዘብ ጡንቻቸውን ያዳበሩ ሀገራት የባህርና ከርሰ ምድር ውሃን ከጨው ነፃ (desalinated) እያደረጉ ለእርሻ እና ለመጠጥ ይጠቀሙታል:: በሌላ በኩል የሴራ ፖለቲካን በማራመድ በብሔር፣ በሃይማኖትና በዘር በመከፋፈል ጡንቻችን ዳብሮ እርስ በርስ በመባላት ዘመኑ በሚዋጀው እውቀት፣ በቴክኖሎጂና በገንዘብ ጡንቻቸውን ማዳበር ያልቻሉ እንደኛ ያሉ ሀገራት ወቅቱ ስደርስ ምን ይውጣቸዋል? የሚል ጥያቄ ከወዲሁ መነሳት ያለበትና መልስ ልፈለግለት የሚገባ ጥያቄ ነው::
በርግጥ የዚህ ፅሁፍ ፀሐፊ ሁሴን የሚባል ሰው 2040 ድረስ ላይኖርም ልኖርም ይችላል:: ሁሴን ባይኖርም ግን ትውልድ ይቀጥላል:: እዚህ ጋር ያሁን ትውልድ ማንሳት ያለበት አንገብጋቢ ጥያቄ፤ መጭው ትውልድ መጪው ዘመን ላይ ምመጣበትን ፈተና እንደት ልቋቋመው ይችላል? የሚል ሆኖ ለጥያቄው አጥጋቢ መልስ መስጠት ይኖርባታል:: አጥጋቢ መልስ ለመስጠት መጀመሪያ የሴራ ፖለቲካን እርግፍ አድርጎ በመተው በብሔር፣በዘር እና በሃይማኖት ተከፋፍሎ እርስ በርስ መባላትን ማስቀረትና ሀገራችን የጀመረችውን Fresh የውሃ የማከማቸትና መልሶ ለልማት የማዋል አብዮትን አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል::
ከአዋሽ ወንዝ በመለስ 11 ታላላቅ የኢትዮጵያ ወንዞች ዘላኖች በመሆናቸው ወንዝ ዳር ቁጭ ብለን እያየናቸው አፈር እና ውሃችንን ያለከልካይ ወደ ሌላ ሀገር ያሻግራሉ:: ኦሞ ወንዝና ታላቁ ግዮን (አባይ ወንዝ) ላይ የተጀመረው የውሃ አብዮት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት:: ባሮ እና አኮቦ ወንዞች ገና ጫቸው አልተነካም:: ቀሪዎቹ ታላላቅ ወንዞቻችንም እንደዛው::
ከላይ ከ12ቱ ወንዞች አኳያ አብዮቱ መቀጠል አለበት ያልኩት እንዳለሆኖ በየዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ያሉ ትናንሽ ወንዞች ላይ ዞኖችና ወረዳዎች ባላቸው አቅም አነሰሰተኛ ግድብ በመስራት ውሃን የማከማቸትና መልሶ ለልማት መጠቀም ላይ አድብቶ መስራት ይኖርብናል:: ከፌደራል እስከ ቀበሌ ውሃን አከማችቶ መልሶ ለልማት የማዋል ልምዳችን ከዳበረ በእርግጠኝነት መጭው ትውልድ በ2040 ይከሰታል ስለሚባል ከፍተኛ የውሃ እጥረት እና ድርቅ ሰለባ አይሆንም::
ሌላው በፌደራል ደረጃ ቅርብ ካሉ ጎሮ ቤት ሀገራትም ይሁን እሩቅ ካሉ ሀገራት ጋር ድንበር ተሻጋሪ በሆኑ የውሃ ሃብታችን ላይ የሚደረጉ ስምምነቶች 2040 ላይ ይከሰታል የሚባለውን የውሃ እጥረት ታሳቢ ያደረገ መጪውን ዘመን ትውልድ አደጋ ላይ የሚጥል ሳይሆን ከአደጋ የሚታደግ ስምምነት መሆን ይኖርበታል:: ለምሳሌ ብልጣ ብልጧ ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር በሚታደርጋቸው ድርድሮች አሳሪ ስምምነት እንድኖር አጥብቃ የሚትሻበት ምክንያቶች አንዱ ኢትዮጵያን እንደ ሁለተኛና የማይነጥፍ የውሃ ባንክ በመጠቀም መጪው ትውልዷ ላይ ልደርስ የሚችለውን አደጋ ለመከላከል ታሳብ አድርጋ ነው::
Hussen Abdella Hussen via Facebook