ጌታዬ! ይኸውልህ ቁምነገር! ከታች የመረግኩት ጉብል ሰሞኑን ዶናልድ ትራምፕ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ በእጩነት ያቀረበው የ39 ዓመት ጎልማሳ ነው። JD Evance ይባል።
ታድያ ለኛ ምን ጥቅም ትል? ይሆናል። ሸጋ ጥያቄ ነው።
ትራምፕ ለምን መረጠው ብለን ስንጠይቅ መልሱን እናገኘዋለን። የወደፊት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ እና የኢኮኖሚ ፓሊሲ ፍንትው ብሎ ይገለጥልሃል፣ ዋና ስታራቴጅያቸውን (Grand strategy) ትረዳለህ። እንደሃገር፣ ቢሆንህን ሰርተህ ብሄራዊ ጥቅምህን ለማስከበር ከወዲሁ ትዘጋጅበታለህ። እንደ ግለሰብ ደግሞ በፈተና ውስጥ ወደ ስኬት ማማ እንዴት እንደሚወጣ ትማርበታለህ።
ጄዲ ኢቫንስ ማን ነው?
ጄዲ የተወለደው ኦሃዮ ግዛት ውስጥ ነው። ወላጆቹ በፋይናንስና በስራ እጦት ምክንያት በዕፅ እና መጠጥ ሱስ የሚሰቃዩ ነበሩ። እናቱ እናቷ አባቷን በጋዝ አርከፍክፋ በቁም ስታቃጥለው አይታለች። በዚህ በተሰበረ ቤተሰብ፣ ግድያና ወንጀል በተሰራፋበት እና የስኬት መንገድ በተዘጋበት፣ በሌሎች የአሜሪካ ግዛቶች ያሉ የኢኮኖሚ ዕድሎች የሌሉበት፣ በ21ኛ ክፍለ ዘመን ውስጥ ለመኖር የሚያስፈልገው መሰረታዊ መረጃ (knowledge Economy) ማግኘት በማይቻልባት የኦሃዮ ግዛት ውስጥ ማደግ መጨረሻህ ነፍሰ ገዳይ፣ ዕፅ አዘዋዋሪና ሰካራም ብቻ መሆን ነው።
መቼም አሜሪካ ውስጥ ይህ አይነት ችግር ይኖራል ብለን አናስብም ኣ?
ጄዲ ይናገራል ኦሃዮ እንዲህ የተራቆተችው አሜሪካ ብረትና ኮል ከቻይና ማምጣት በመጀመሯ እና ኢንዱስትሪዎች በመዘጋታቸው፤ Deindustralised ፓሊሲ በመከተላቸው ነበር። በሚሊየን የሚቆጠር የአሜሪካ ዜጋ በዚህ ፓሊሲ ምክንያት ከስራ ውጭ ሆኑዋል። ይህ ደግሞ የአሜሪካ ህልማችንን እውን እንዳናደርግ አድርጎናል ይላ ጄዲ።
የጄዲ እና ሱሰኛ ብትሆንም ልጇ የሷን እና ሌሎች ዱርየ የሰፈሩ ልጆችን መንገድ እንዳይከተል ትጥር ነበር። እንደ እድል ሆኖ እርዳታ አገኘ። የሃይስኩል ትምህርቱን ጨረሰ። ታዋቂው የሕግ ትምህርት ቤት የል ዩንቨርስቲ ነፃ የትምህርት አገኘ። በዚህ ሂደት ያሳለፈውን ስቃይ ይናገራል። ከሕይወት ፍልስፍናየና እምነቴ ውጭ ሊበራል እንደሆንኩ ገልጨ ፍሮም ሞልቻለሁ ይላል። እንዲህ የነፃ ትምህርት ስለሚገኝብት ሁናቴ እንኳ የኦሃዮ ተወላጆች መረጃ የለንም ይላል። ለ21ኛው ክፍለዘመን የሚያስፈልገው Knowledge Economy አልነበረውም። ከትምህርት ውጭ በኔትወርክ(በጓደኛ፣ ቤተሰብና ዝምድና) ወይም ባለህ social capital የሚገኘውን የስኬት መንገድ እውቀት አልነበረውም።
ጌታዬ! አንተስ ኔትወርክ አለህ ወይ? ዘመኑን የሚፈልገውን እውቀት ታጥቀሃል ወይ? ለመጪው የኢንዱስትሪ አብዬት እየተዘጋጀህ ነው? Retool እያደረክ ዘመኑን እየዋጀህ ነው ወይስ መያዣ መጨበጫ በሌለው ወደ ጨለማ ሕይወት በሚወስደው የነፃነት ትግል ላይ ነህ? ንቃ!
የሆኖ ሆኖ….
የሕግ ትምህርቱን እንደጨረሰ የባህር ሃይል ሰራዊትን ተቀላቀለ። አራት አመት ሰለጠነ። በዚህ ስልጠና ወሳኙን የባህሪ ማነፅ ትምህርት ወሰደ። ጧት መነሳት፣ አልጋ ማንጠፍ፣ ልብስ ማጠብ እና ገንዘብን እንዴት ማስተዳደር እንደሚቻል ተማረ። ይህ ስልጠና የወደፊት ሕይወቱ እና ስኬቱ ትልቅ ተፅዕኖ አበርክቶ እንዳለው ይገልፃል። ለሃገሩ ኢራቅ ዘመቶ ግዳጆን ጨርሶ ተመለሰ።
ወደ ሥራ…
ዩንቨርስቲ ያተዋወቃትን የህግ ባለሙያ አገባ። የጥብቅና ካምፓኒ ተቀጠረ። ባገኘው ገንዘብ ቬንቸር ከፒታል መሰረተ። ኦሃዮና ሌሎች ግዛቶች ኢንቨስት ከሚያድርጉ ጋር ሽርክና እየገባ ወደ ሃብት ጉዞ አደርገ። ስኬትን ተጎናፀፈ። በኔ የደረሰ በሌሎች መድረስ የለበትም ብሎ የአሜሪካን የኢኮኖሚ ፓሊሲ በመቃወም የተዘጉ የብረትና የኮል ኢንዱስትሪዎች እንዲከፈቱ ተከራከረ። ሪፐብሊካን ፓርቲን ተቀላቀለ። ትራምፕን ደገፈ። ያለማቋረጥ America first አቀንቃኝ አሰላሳይ ቡድኖችን በገንዘብ እና በሃሳብ ደገፈ።
ግለ-ታሪኩን የሚያትት Hillybilly elegy የተሰኘ ድንቅ መፅሃፍ ፃፈ። ተቸበቸበ። ፊልም ተሰራለት። አሁን በኔትፍሊክስ በከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር እየታ ይገኛል።
ትርክቱ ገዥ አገኘ…
የመካከለኛው ሰራተኛ መደብ ሆን ተብሎ ለትልልቅ ካምፓኒዎች ጥቅም ሲባል እንደተበደሉ የሚያትተው ትርክት የአሜሪካን ህዝብ አይምሮና ልቦና ማሸነፍ ቻለ። እንኳን ሪፐብሊካኖች ዲሞክራቶችም ይህን ትርክቱን ገዙት። ባይደን ከትራምፕ የበለጠ የኢኮኖሚ ብሄርተኛ ሆነ። Foreign policy for middle class የተሰኘ ፓሊሲ ተግባራዊ አደርጉ። እያንዳንዷ የውጭ ጉዳይ ውሳኔ ለመካከለኛው መደብ ስራ የሚፈጥር መሆን አለበት ተባለ። Inflation reduction act እየተባለ የሚጠራው ህግ ዋነኛ ግቡ አሜሪካን Reindustralised የሚያደርግ ነው። ኢንዱስትሪ መገንባት። የአቅርቦት ሰንሰለቱን በአቅራቢያ እና በሃገር ውስጥ ማድረግ ላይ ያተኮረ ነው። የኛው አየር መንገድ እንኳ የቦይንግ ደንበኛ በመሆኑ በመቶ ሺ ለሚቆጠር ሰራተኛ የስራ እድል ይፈጥራል፣ ከኛ ጋር ያላቸው ስትራቴጅክ ጥቅም በዋናነት ይኸው ነው። ማይክ ሃመር አላማው ይህን ማሳካት ነው፣ ውል እንዳይፈስ። ደንበኝነትን ማስቀጠል።
ጄዲ ኢቫንስ በዚህ ተፅዕኖው እና የመካከለኛው መደብ ሰራተኛ መበደል ምልክት ስለሆነ ዶናልድ ትራምፕ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጠው። እንግዲህ ትራምፕ ቢያሸንፍ ከባይደን የበለጠ አክራሪ ኢኮኖሚክ ናሽናሊስት እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው። ያኔ በመጀምሪያው ዙር ከቻይና ጋር የጀመረውን የንግድ ጦርነት አጧጥፎ ይቀጥላል። የቻይናን ግስጋሴ ለማዳከም ማናቸውንም ብሄራዊ የተፅዕኖ መሳሪያዎች (National instrument of power) ይጠቀማል። ቻይናን ከአጋሮቿ በውዴታና በግዴታ መነጠል ይፈልጋል። በዚህ ሂደት የኛስ ጉዳይ ምን ይሆናል ብሎ ማሰቡ ፅሩ ነው።
አጅሬ አጋህን ለይ ቢልህ ምን ምላሽ አለህ?
ቀድሞ ማወቅ ያሸልማል እንዲሉ በውጭ ጉዳዩም ሆነ በሌሎች የሃገርና የግለስብ የይወት መስኮች መጪውን ጊዜ ለማወቅ መረጃ መታጠቅ ያስፈልጋል።
አትፍዘዝ
ታመጣለህ መዘዝ
እንዲል Eyobአይደለም’ዴ ጌታዬ!
List Frederick fb