ሰሞኑን ” ኢትዮጵያ ላይ ኢንቨስት አታድርጉ፣ ያደረጋችሁም ሳይመሽ ለቃችሁ ጥፉ” የሚል ጥቅል ዓላማ ያለው ሪፖርት ላቀረበው “vates” የተባለ የህቡዕ ቡድን ቁጥር ሁለት ሪፖርት ግብዓት የሚውሉ ዜናዎች እየተመረቱ እንደሆነ፣ ይህም የሚደረገው በማነበብ፣ አጀንዳ በመቅረጽና በመናበብ እንደሆነ የኢትዮሪቪው የዜና ሰዎች አመለከቱ።
“vates” ትርጉሙም “prophet” ነቢይ፣ ወይም Fortune teller ትንቢት አብሳሪ፣ የወደፊቱን ገላጭ ማለት ሲሆን ሰሞኑን situation analysis የሁኔታዎች ትንተና ሪፖርት ። Ethiopia: Situational Analysis (Horn of AfricaSituational Analysis Series (HoA-SA)), July 04, 2024; Reporting Period: June 20 – July ። የሚል ሪፖርት ማሰራጨቱ ይታወሳል።
ይህ ሪፓርት ካነሳቸው ማስፈራሪያ መካከል “የሰማዕታት ቃል ኪዳን” የሚል አዲስ ኦፕሬሽን መጀመሩን ነው። ኦነግ ሸኔ በዚህ ኦፕሬሽኑ የመንግስትና የግል ባለሃብቶችን ሃብት የማውደም፣ በደፈጣ የማጥቃት ተግባር ለመፈጸመ መዘጋጀቱን ደጋግሞ የአገር ውስጥ የዜና አውታሮችን የተለያዩ ሪፖርቶችና ድርጅቱ ያወጣቸውን መረጃዎች ሰብስቦ ነበር ኢንቨስተሮችን “ወደ ኢትዮጵያ አትሂዱ” ሲል በቅድመ ስጋት ትነተና ስም ያስፈራራው።
መንግስት ድፍን ወለጋን መቆጣጠሩና በኦነግ ሸኔ ላይም ትርጉም ያለው ጥቃት ማድረሱን በምስል አስደግፎ በተደጋጋሚ ይፋ ካደረገ በሁዋላ ጃል መሮ “ወለጋ በቃን” በሚል “የተቀባው” ያሉት የኦነግ ጦር በአምስት አቅጣጫ ወደ አዲስ አበባ? እንዳመራ ካስታወቁ በሁዋላ የወጣው የዚህ የህቡዕ ቡድን ሪፖርት አጉልቶ ያሳየው የኦነግ ሸኔን መመታት ሳይሆን ወደ ደፈጣ ትግል የቀየረውና መንፈሳዊ ስም የተሰጠው ኦፕሬሽን አደጋ ይዞ እንደሚመጣ ነው። ዓላማውም ኢንቨስትመንቱን ማስተጓጎል እንደሆነ ሪፖርቱን ያነበቡ በይፋ የገለጹት ጉዳይ ነው።
ራሱን የ”ነብዮች” ስብስብ ያደረገው ይህ ቡድን የመጀመሪያ ሪፖርቱን ይፋ ሲያደርግ በሰራነው አንድ አንድ ክፋይ ዜና ላይ እንዳልነው ስማቸው፣ ማነታችውና ማዕረጋቸው ስውር ከሆኑት የቡድኑ አባላት መካከል በተለያዩ ሙያዊና ተቋማዊ መዋቅር ሽፋን ተከልለው አዲስ አበባ የተቀመጡ እንዳሉ ምንጮችን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።
“መንግስትን መቃወምና በታገል የየትኛውም አገር የፖለቲካ ባህል ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አካሄድ ግን ብሄራዊ ጥቅምን፣ የህዝብ ጥቅምን፣ የአገር ገጽታን፣ የወደፊት ትውልድ ተስፋን ወዘተ ግንዛቤ ውስጥ የማያስገባ፣ ከዛም በላይ የሚያልፍ ክህደት እየሆነ ነው” የሚሉ ወገኖች በዚህ ደረጃ እንዴት ቁልቁል የክህደት ውለል ላይ የተከሰከሱ ዜጎች ሊፈጠሩ እንደቻሉ አይገባቸው። ይህ ጥያቄም የበርካቶች ነው።
የዜና ሰዎቻችን በላኩልን አዲስ መረጃ ይህ ራሱን ህቡዕ አድርጎ ኢትዮጵያ ላይ የዘመተውና በ”ሚታወቁ”ኢትዮጵያውያን ጭምር የሚነቀሳቀሰው ቡድን ክፍል ሁለት ሪፖርት እያዘጋጀ ነው። በዚህ የክፍል ሁለት ሪፖርቱ የሚካተቱና ለግብአትነት የሚጠቅሙ ሪፖርቶች ከወዲሁ እየተዘጋጁለት ወይም እየተመረቱለት ነው።
በስም ከሚታወቁ ሚዲያዎች፣ በስም ከሚታወቁ የድረገጽ አውታሮች፣ ለራሳቸው “አንቂ” የሚል ማዕረግ በሰጡ የማህበራዊ ድር ተዋናዮች፣ በቀጥታ በውጭ አገር በሚደጎሙ የኦንላይን የወሬ ዌብሳይቶች፣ ኤምባሲዎች ወዘተ. ከዚህም በተጨማሪ “ሰላማዊ ታጋይ ነን” በሚሉ የፖለቲካ ድረጅት አመራሮች፣ የሲቪክ ተቋማትና መሰል አደረእጃጀቶች አጀንዳ እየተቀረጸ በሚፈጸም ሴራ ዜና ይሆናል። ሴራው የሚያስከትለው ውጤት ሌላ ዜና ያስከትላል። ከላይ የተዘረዘሩት ወገኖች እንዲቀባበሉት ይደረጋል። ከዚያም ዜናው ለህቡዕ ድርጅቱ ሪፖርት ግብአት እንደሚሆን ትንተናና ጥናት አስቀድሞ መሰራቱን የዜናው ምንጮ ይናገራሉ።
በዚሁ ተግባር ከተሳተፉት መካከል በህቡዕ ከሚታወቀው ቡድን ጋር አብረው የሚሰሩ መኖራቸው፣ ማንነታቸው ተለይቶ እንደሚታወቅ ያመለከቱት የዜናው ሰዎች፣ አዲስ አበባ ተቀምጠው አገራቸው ላይ ” የውጭ ኢንቨስትመንት እንዳይገባ ዘመቻ የከፈቱት ከሃጂዎች” ጉዳይ በቅርቡ መንግስት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደግ አመልክተዋል።
መቅመጫውን ኬንያ እንዳደረገ ከመግለጽ ውጭ አንዳችም ነገር ስለ አባላቱ የማይተነፍሰው ይህ የህቡዕ ቡድን ላቀረበው ሪፖርት ማብራሪያ፣ ወይም ማስተካከያ እንዲያደርግ የሚጠየቅ አይደለም። ሰዎቹ እንዳሉት ኢትዮጵያ በዚህ ደረጃ ዘመቻ እየተከፈተባት FDI / Foreign Direct Investment ወይም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት 3.3 ቢሊዮን በማግኘት ከምስራቅ አፍሪቃ አንደኛ መሆኗ ያበሳጫቸው ክፍሎች አንዱ ስለማይበቃ ሌላ ሪፖርት ለማሰራጨት ተግተው እየሰሩ መሆኑን አመልክተዋል።
ኦነግ ሸኔ የፊት ለፊት ውጊያ በማቆም የሽምቅ ጥቃት እንደሚጀምር፣ ዒላማ ያደረጋቸውን ተቋማት ገልጾ ይፋ ባደረገና የህቡዕ ድርጅቱ ይህንኑ ይፋ ካደረገ በሁዋላ ኦፌኮ “በኦሮሚያ 22 ዞኖች ውጊያ እየተካሄደ ነው” ሲሉ መግለጫ መስጠቱን ጠቅሰው መረጃ የሰጡን ወገኖች ” የኦፌኮ አመራሮች ይህን መረጃና ዳታ ከየትኛው የኦነግ አመራር አገኙት” ብሎ የሚጠይቅ እንደሌለ አመኦልክተዋል። አያይዘውም መግለጫው እንደተሰጠ ለዚሁ የህቡዕ ቡድን ግብዓት እንዲሆን የሚታወቁት ክፍሎች አዲስ አበባ ሆነ ዜናውን እንደ ቅርጫ እየበለቱ ማከፋፈል ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ ተከታታይ የውድቀት፣ የችግር፣ የስጋት፣ የአደጋ፣ የቀውስ፣ የውድመት፣ የጥፋት ወዘተ ዜናዎች እንዲመረቱ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑንን ያመልከቱት ወገኖች “ይህን ስንል አገሪቱ ውስጥ ሽግር የለም። ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ ነው። መንግስትም እንከን የለበትም ለማለት ግን አይደለም። መንግስት እጅግ በርካታ ችግር አለበት። ትግል ያስፈልጋል። ግን ብሄራዊ ጥቅምንና አገረን አደጋ ላይ የሚጥል ትግል በምንም መሰርት አይዋጣም” ብለዋል።
መንግስት እጅግ ሰፊ ችግር ቢኖርበትም የሚሰራቸውን በጎ ስራዎች ማበረታት ከዜጎች ሁሉ እንደሚጠበቅ በተደጋጋሚ ሲገለጽ መቆየቱ አይዘነጋም። ጭፍን ድጋፍም ሆነ ጭፍን ጥላቻ አገርንም ሆነ ዜጎችን እንደማይጠቅም እነዚሁ ወገኖች ደጋግመው በሰፋፊ ጥናት ማቅረባቸው የሚታወስ ነው።
“vates” የሚባለው የህቡዕ ቡድን ያሰራጨውን ሪፖርት ይፋ መሆኑንን ተከትሎ በርካቶች ያነሱትን ጥያቄ የዜናው ሰዎች “ኢትዮጵያን አስመልክቶ የውድቀት፣ የዕልቂት፣ የጥፋት፣ ወዘተ መረጃ ይፋ ሲሆን አፍታ ሳይቆይ በድረገጾቻቸውና በማህበራዊ አውታሮቻቸው የሚያቀረቡት የሚታወቁ ሚዲያዎች፣ የሚታወቁ ገለሰቦች ይህን ሪፖርት በዝምታ አልፈውታል” ሲሉ ጉዳዩ ጥናት እንደሚያስፈልገው ይገልጻሉ። አያይዘውም “ለምን ዝም አሉት? ለምን እንዳላየ አለፉት? ህቡዕ ድርጅት ስለሆነ ወይስ ሚናቸው ግብዓት መስጠት ብቻ በመሆኑ?” ሲሉ በመጸት ልብ ያላቸው እንዲመረመሩ ጥቆማ ሰጥተዋል።
ኦፌኮ በሰጠው መግለጫ ላይ ብረት ያነሱ ሁሉ ወደ ሰላም ንግግር እንዲመጡ ማሳሰቡ ፣ መንግስትም ለስለማዊ ውይይት ከሁሉም በላይ ሃላፊነት መውሰድ እንዳለበት መግለጹ፣ የተዘጉበት ቢሮዎቹ እንዲከፈቱለት መጠይቁ አግባብ መሆኑን የሚያምኑ በተመሳሳይ ኦፌኮ ናይሮቢና አዲስ አበባ፣ ሰላማዊና የተነኮል አካሄድን ማጣቀሱን ሊያቆም እንደሚገባ አመልክተዋል።
የኦሮሚያ ክልልም ሆነ መንግስ የፓርቲውን ጽህፈት ቤቶች መክፈት እንዳለበት የሚያሳስቡ ሌሎች ወገኖች ኦፌኮ ኦሮሚያ ብልጽግናም ደጋፊ እንዳለው በረጋ ስሜት እንዲመረመሩ አሳስበዋል። ራሳቸውን ልዩ የኦሮሞ ድርጅት አድርጎ በታሪክ መመዘን ድርጅቱን የጎዳው እንደሚመስላቸው የጠቆሙ ” ለህቡዕ ቡድኑ” የሚውሉ ሪፖርቶችን በውደ ናይሮቢ ከማድረስ ይልቅ ዙሪያን በመገምገም አቋቋምን ማስተካከል እንደሚገባ መክረዋል።