የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበጀት ዓመቱ ሰባት ነጥብ ቢሊዮን ዶላር ወይም ሲቀመጥ 402 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ። ትርፉ ካለፈው ወቅት ጋር ሲነጻጸር የአስራ አራት በመቶ ብልጫ አሳይቷል።
ራሱን ለማብቃትና ተወዳዳሪነቱን ከፍ ለማድረግ እየሰራ እንደሆነ የሚነገርለት የአፍሪካ ኩራት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስቀድሞ ካዘዛቸው ሃያ የሚሆኑ አውሮፕላኖች ጋር ተደምሮ 125 የሚሆን አውሮፕላኖች ለመግዛት ማዘዙን ዋና ስራ አስኪያጁ ጠቁመዋል። ከቦይንግ የታዘዙ አውሮፕላኖች አለመገኘታቸውን ተከትሎ የአውሮፕላን እጥረት እንዳጋጠመ ተናግረዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንዳሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመቱ 577,746 ሰዓታትን በሯል። ይህ የበረራ ሰዓት ቀደም ሲል ከተመዘገበው በአስራ ዘጠኝ በመቶ እድገት አሳይቷል።
በበጀት ዓመቱ አየር መንገዱ 17.1 ሚሊየን ተጓዧችን አጓጉዟል። 13.4 ሚሊዮን የሚሆኑት ዓለም አቀፍ ተጓዦች ሲሆኑ፣ 3.7 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ የሀገር ውስጥ መንገደኞቸ እንደሆኑ ተመክቷል።
የሀገር ውስጥ በረራ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረ ያወሱት ዋና ስራ አስኪያጁ፣ ባለፈው የበጀት ዓመት አየር መንገዱ 2.7 ሚሊዮን የሀገር ተጓዦች ብቻ ማስተናገዱን ተናግረዋል። ከዘንድሮው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የአንድ ሚሊዮን ተጓዞች ብልጫ ተመዝግቧል።
የካርጎ ጭነት ካለፉት ተመሳሳይ ወቅቶች ጋር ሲነጻጸር ቅናሽ አሳይቷል። በዚሁ መሰረት በጀት ዓመት አየር መንገዱ ያጓጓዘው ጭነት መጠን ከ54,681 ቶን ጭነት እንደሆነ ከዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።
ይህ ቅናሽ በገቢ ሲታየ ” አየር መንገዱ ከካርጎ ያገኘው ገቢ 1.65 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 8 በመቶ ቅናሽ እንዳሳየ ዋና ስራ አስፈጻሚው አስረድተዋል።
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring