በገልተኛነትና የሌሎች ሃይሎችን ዓላማ ያራምዳሉ በሚል ይከሰሳሉ። በዚህ ጉዳይ በተደጋጋሚ ሲጠየቁ ክሱን ውድቅ የሚያደርጉት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ዛሬ ተሸኝተዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ አሸኛኘት እንዳደረጉላቸው ተመልክቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በትናንትናው የፓርላማ ውሏቸው ” የሰብዓዊ መብት አዋጅ ፣ ተቋም፣ አሰራር ይፈተሽ ” በሚል ተናግረው ነበር።
ዳንኤል በቀለ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው ሰኔ 25 ቀን 2011 ዓ.ም መሾማቸው ይታወሳል፡፡ ተቋሙ ከለወጡ በሁዋላ ከተገነቡት ሁሉ እጅግ አስፈላጊና ከመንግስት ተጽዕኖ ገለልተኛ እንደሆነ ራሳቸው ኮሚሽነሩ ምስክር ሰጥተዋል። ይሁንና የስራ ጊዜያቸው ሊጠናቀቅ ሁለትና ሶሶት ወራት ሲቀራቸው ማስፈራራትና ዛቻ በተቋሙ ሰራተኞችና አመራሮች ላይ እንደሚደረግ ተመልክቷል። ይህንኑ ዜናም ዓለም ዓቀፍ ተቋማትና የዜና አውታሮች በስፋት ሲያስተጋቡት ነበር።
ይህ በንዲህ እንዳለ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ” ሰብዓዊ መብት ደስ የሚል ቋንቋ ነው፣ ለሰዎች የሚደረግ መብት በግርድፉ ሲታይ ደስ የሚል ቋንቋ ነው ግን ይሄ ቋንቋ ከዋናው የትርጉም ግንዱ ወጥቶ የፖለቲካ መጠቀሚያ እየሆነ ነው ” ሲሉ ትናንት በፓርላማ ውሏቸው ተናግረዋል። በርካታ የአድፍሪካ አገራትም የሚታመሱት በዚህ (ሰብዓዊ መብት) ታርጋ እንደሆነ አመልክተዋል።
ስለ እሰረታዊ የሰብዓዊ ልጆች መብት አንስተው ለዚሁ የሰው ልጆች መብት ማሰብ ጠቃሚና ቀዳሚ መሆኑንን ተናግረዋል። የሰውን ልጆችን ማክበር ፣ የተሻለ ቤት፣ ጥሩ መማሪያ እንዲኖራቸው፣ እንዲመገቡ ማስቻል ዋናና ቀዳሚው የሰው ልጆች መብት መሆኑንን ያመልከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ስለ ሰው ልጆች በልቶ ማደር ስለ መኖሪያ ቤታቸው ሳይጨነቁ በሚዲያና በዩትዩብ በመናገር ብቻ የሰው ልጆች መብት ተቆርቋሪ እንደማያሰኝ ገልጸዋል።
“የሰብዓዊ መብት አዋጅ፣ ተቋምና አሰራር መፈተሽ ያስፈልጋል ” ሲሉ ለተከበረው ምክር ቤት አሳባቸውን ያጋሩት አብይ አሕመድ፣ ” እኛ ደመወዝ የምንከፍለው፣ ሌሎች ኃይሎች የቀጠሩት፣ ለሌሎች ኃይሎች ሪፖርት የሚያደርግ ተቋም ኢትዮጵያ ውስጥ ከፈቀድን ምን ሊፈጠር እንደሚችል ለእናንተው መተው ነው ” ሲሉም አስጠንቅቀዋል።
“እኔ የሰብዓዊ መብት የሚባሉ ሃሳቦችና ተቋማት በየትም ቦታ ያሉ የማያቸው ልክ እንደመርፌ ነው ፤ መርፌ የራሱን ቀዳዳ መስፋት አይችልም። እነሱም የራሳቸውን ድክመት ማየት አይችሉም። ይሄ ጥሩ አይደለም ሀገር ያፈርሳል ጥቅም የለውም፤ ተቋሞቻችንን ጸዳ ማድረግ አለብን ” ሲሉ አፈርጥመው ተናግረዋል።
ሁለት ነገሮች ሊሰመርባቸው እንደሚገባ ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰብአዊ መበት ተሟጋች ድርጅቶች ላይ መንግስት ጫና ማድረግ እንደሌለበት፣ ይህም አግባብ እንዳልሆነ ጠቅሰው በተቃራኒው ደግሞ ተቋማቱ የሌሎች አገራትና ሃይሎች መጠቀሚያ እንዲሆኑ መፈቀድ እንደሌለበት ተናግረዋል። “የሰብዓዊ መብት ተቋማት ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ከሌላ ሀገራትና ፍላጎቶች ነጻ መሆን አለባቸው” በማለት አሳስበዋል።
“አሁን ላይ ያሉት ግን” አሉ አብይ አህመድ ” አሁን ያሉት ግን ከኢትዮጵያ መንግሥት ነጻ ቢሆኑም ከሌሎች ኃይሎች ነጻ አይደሉም” ሲሉ የተጠራቀመውን የመንግስትን ብሶት ይፋ አድርገዋል። ከዚህ ቀደም ፊልድ ማርሻል ብረሃኑ ጁላ በተመሳሳይ ተቋሙ ፍጹም ገለልተኛ እንዳልሆነ አምለክተው ነበር።
ዶ/ር ዳንዔል የሚመሩት ኢሰመኮ በአማራና አፋር ክልል ወረራ በተፈጸመት ወቅት፣ በማይካድራ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ በገሃድ ያላጋለጡ እንዲያውም፣ ለመሸፋፈን የሚከረ ሪፖርት በማቅረባቸው የተነሳ የተቋሙ ታማኝነት ማክተሙን በወቅቱ በርካታ ዜጎች አደባባይ ወጥተው ሲናገሩ እንደነበር ይታወሳል።
ብዙ ዝርዝር ጉዳዮችን ያላነሱት አብይ አህመድ የተቋሙን ችግር በድፈናው ሲገልጹ፣ በሀገሪቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የለም ማለት እንዳለሆነ ግልጽ አድርገዋል። በመብት ጥሰት ጉዳይ ስህተቶችን መገምገም ኃላፊነትም መውሰድ እንደሚገባ አልሸሸጉም።
መከላከያ እና ፌዴራል ፖሊስ ጥፋት የፈጸሙ አባሎቻቸው ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን ጠቅሰው ካመሰገኑ በሁዋላ “የሀገር መከላከያ በወታደራዊ ፍርድ ቤት በሺዎች የሚቆጠሩ አባላቱን ከ code of conduct ውጭ ኦፕሬሽን ሰርተዋል በሚል ምክንያት እስር ቤት ከቷል” ብለዋል።
የአብን አባሉ አቶ አበባው ደሳለው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት ጥያቄ ባለፉት 10 ወራት በአስቸኳይ አዋጅ ሰበብ በአማራ ክልል ፦የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደፈጸሙ፤ በበርካታ የአማራ ከተሞች ያልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎች በጅምላ እንደተገደሉ (ለምሳሌ ፦ በመርዓዊ ፣ በጅጋ ፣ በደብረ ኤልያስ ፣ በፍትኖተ ሰላም፣ ደብረሲና አካባቢ ፣ ጎንደር እና ወሎ) የጅምላ እስር አማራን መሰረት አድርጎ እንደሚፈጸም የምክር ቤት አባላት ሳይቀር በፖለቲካዊ አመለካከታቸው እስር ቤት እየማቀቁ እንዳለ ይህንን ጉዳይም የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት መዘገባቸውን አንስተው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቅርበው ነበር።
—–