ከአሜሪካ የተሰማው ዜና ለወትሮው በኢትዮጵያ የመብትና የዴሞክራሲ፣ እንዲሁም የመጻፍና መናገር መብት አቀንቃኝ እንደሆኑ በሚናገሩ ዘንዳ ዜና አልሆነም እንጂ የዓለም መነጋገሪያ ሆኖ ሰብቷል። ዜናውን የሰሙ ይህ ውሳኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢሆን ኖሮ ምን ይባል ነበር? የሚል ጥያቄ ሲያነሱ ተድምጠዋል።
- ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ጋዜጠኛ በተመሳሳይ ቢባረር ጩኸቱ የት ድረስ ይሆን ነበር?
- ጋዜጠኛዋ ከስራ እንድትባረር የተደረገው ፕሬዝዳንት ባይደንን እንድትጠይቅ ከተሰጣት ጥያቄዎች ውጪ ጠይቃለች በሚል ነው
አል አይን በጉልህ ከከተበው ውጭ ሌሎች አሜሪካን አገር የተተነፈሰ ሳይቀር ጠራርገው የሚያመግቡ ሚዲያዎች “አልሰማንም” ሲሉ ያለፉት ዜና ከስር እንዳለ ቀርቧል
ፕሬዝዳንት ባይደን በቃለ መጠይቁ ወቅት “እኔ በጥቁር ፕሬዝዳንት ስር ምክትል ሆኜ ያገለገልኩ የመጀመሪያዋ ሴት ነኝ” ማለታቸው ይታወሳል
ፕሬዝዳንት ባይደንን ቃለ መጠይቅ ያደረገችው ጋዜጠኛ ከስራ ተባረረች፡፡
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሰሞኑ በፊላዴልፊያ ግዛት ከሚሰራጨው ጥቁሮች ሬዲዮ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገው ነበር፡፡
የፕሬዝዳንት ባይደን ምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ከቃለ መጠይቁ በፊት ከሬዲዮው ጋር ባደረገው ድርድር ለፕሬዝዳንት ባይደን የሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች እንዲላኩለት አድርጎ ነበር፡፡
ፕሬዝዳንት ባይደንም ከሬዲዮ ጣቢያው ጋር በሚኖራቸው ቃለ መጠይቅ ጥያቄዎቹን ተቀበለው ዝግጅት አድርገው እንደነበርም ተገልጿል፡፡
ሎውፉል ሳንደርስ የተባለችው የሬዲዮ ጣቢያው ጋዜጠኛም ለፕሬዝዳንት ባይደን ቃለ መጠይቁን እንደምታካሂድ ቀጠሮ ይያዛል፡፡
ይሁንና ጋዜጠኛዋ ሬዲዮ ጣቢያው ከፕሬዝዳንት ባይደን ቡድን ጋር በተስማሙት መሰረት የተሰጣትን ጥያቄዎች ከመጠየቅ ይልቅ የራሷን ጥያቄዎች ጠይቃለች ተብሏል፡፡
አዛውንቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አሁንም የአፍ ወለምታቸው ቀጥሏል
በዚህም ምክንያት ፕሬዝዳንት ባይደን ያልተገቡ እና ዝግጅት ያልተደረገባቸው ምላሾችን በመመለሳቸው ፓርቲያቸው እና ራሳቸው ፕሬዝዳንቱ መሳለቂያ እንደሆኑ ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
በዚህም ምክንያት ዉርድ የተሰኘው የጥቁሮች ሬዲዮ ጣቢያ ጋዜጠኛዋን ከስራ እንዳሰናበተ አስታውቋል፡፡
ፕሬዝዳንት ባይደን በቃለ መጠይቁ ወቅት “እኔ በጥቁር ፕሬዝዳንት ስር ምክትል ሆኜ ያገለገልኩ የመጀመሪያዋ ሴት ነኝ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም ፕሬዝዳንት ባይደን አክለውም “በዴላዊር ግዛት ውስጥ በልጅነቴ ሙሉ ለሙሉ ደምጽ ያገኘሁ ብቸኛው ፕሬዝዳንት ነኝ” ሲሉም በቃለ መጠይቃቸው ወቅት መናገራቸውን ተከትሎ በፕሬዝዳንቱ የአዕምሮ ጤና ላይ ተጨማሪ መጠራጠሮች እንዲነሱ ምክንያት ሆኗል፡፡