በጦርነቱ ወቅት ትህነግ በተደጋጋሚ ኤርትራን ተቆጣጥሮ ፕሬዚዳንት ኢሳያስን ማስወገድ ቀላል እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲናገር የነበረው ኤርትራ በቂ የሚባል ሰራዊት እንደሌላት መረጃ ስላለው እንደነበር ይታወሳል። ሰሞኑን ከኤርትራ የሚወጡ መረጃዎች ሻዕቢያ የሃይል እጥረትና ስጋት እንዳለበት የሚያሳይ መሆኑ ተመልክቷል። ሰራዊቱም በቂ ክብካቤ ስለሌለው ተሰላችታል።
በስደት ኤርትራን ለቀው የወጡ ወጣቶች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ያመለከቱ የመረጃ ምንጮች፣ ኤርትራ በአሁኑ ሰዓት ሰራዊቷ ከአመራር ጀምሮ በወጣቶች የተገነባ አይደለም። ከዚያም በላይ በቁጥርም ቢሆን እዚህ ግባ ሊባል አይችልም።
ትህነግ የአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ በፈጸመው ክህደት ሳቢያ፣ አማራና አፋርን ወሮ በፈጸመው ታሪክ የማይረሳው ጥፋት ሳቢያ በወቅቱ ሲሰጡ የነበረውን መረጃ የሚሰማና የሚቀበል ባለመኖሩ እንጂ ትግራይ ገብቶ የነበረው የሻዕቢያ ሰራዊት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊቱን አጥቷል።
የዝግጅት ክፍላችን የአዲስ አበባ ተባባሪ የጦርነቱን ጥሪ ሸሽተው በትግራይ በኩል አዲስ አበባ ከገቡ መካከል ያነጋገራቸው የኤርትራ ተወላጆችን ጠቅሶ እንዳለው፣ በቁጥር መግለጽ ያዳግታቸዋል እንጂ የኤርትራ ወታደሮች ላይ ሰፊ የሚባል ጉዳት ደርሷል። ማለቱን ገልጸን መዘገባችን ይታወሳል። ነዋሪነቷ አሜሪካ የሆነና ለዕረፍት አዲስ አበባ የነበረች የኤርትራ ተወላጅ በተመሳሳይ ለፈተና ከጠራ በሁዋላ ወደ ትግራይ እንዲዘምት የተደረገ ወንድሟ የት እንዳለ ቤተሰብ እንደማያውቅ ግልጻ ነበር።
በትግራይ ጦርነቱ ከቆመ በሁዋላ እንደወጡ የቀሩት የኤርትራ ወታደሮች ጉዳይ አሁን ላይ በስፋት መነሳት የተጀመረው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በሶማሌ በኩልና በአማራ ክልል በኩል ኢትዮያ ላይ ጦርነት እንዲነሳ እየሰሩ ያሉትን ስራ ተከትሎ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት ስጋት አለ። ይህን ስጋት ተከትሎ የተሰሩ ግምገማዎችን ጠቅሰው መረጃ ያካፈሉን እንዳሉት ኤርትራ አፍላ ወይም ወጣት ሰራዊቷ ተመናምኗል።
በለውጡ ማግስት በተደረገ የሰላም ስምምነት ወደ ኢትዮጵያ የጎረፉ የኤርትራ ወጣቶች አራት መቶ ሺህ እንደሚጠጉ የጠቆሙት ወገኖች፣ ዛሬ ላይ ኤርትራ ካላት 3,817,651 የሚጠጋ የህዝብ ብዛት አብላጫዎቹ ሴቶች ናቸው። አብዛኛው አምራች ዜጋ በሱዳን፣ ጅቡቲ፣ በስደተኞች ጣቢያዎች ምዘግባ፣ በባህር ወደ ሊሎች አገራት ተሰደዋል። አለያም ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ ናቸው። ለዚህም ይመስላል የህዝብ ቁጥሩ ዕድገት ከአምናው ጋር ሲነጻጸር 1.7 በመቶ ብቻ ነው የጨመረው።
መጽሃፍ ቅዱስን በሚፈልጉት መልኩ ተረድተው በሻቸው መልኩ እምነታቸውን ማራመድ እንኳን የማይፈቀድባት ኤርትራ የዜጎቿ ቁጥር በዚህ ደረጃ በመመናመኑ ሳቢያ አሳሳቢ ጉዳይ ሲኖር ለሚሊሻዎችና አባት ጦሮች ጥሪ እንደሚደረግ ስለ አሰራሩ የሚያውቁ ይናገራሉ። በቅርቡ ወደ ትግራይ ለዘረፋና ለበቀል አጋጣሚውን ጠብቆ የገባው የኤርትራ ጦር ከላይ በተገለጸው መልኩ ጥሪ አቅርቦ እንደነበር እነዚሁ ወገኖች ይገልጻሉ።
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከወዳጃቸው የሶማሌያ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼህ የወታደር ድጋፍ እንዲደረግላቸው ወይም በሰላም ማስከበር ስም የኤርትራ ወታደሮች የሚሰማሩበትን አግባብ ለማፈላለግ ጥያቄ አቅርበው አሉታዊ ምላሽ እንደተሰጣቸው የትህነግ ደጋፊዎች ከውስጥ መረጃ ማግነታቸውን ጠቅሰው መዘገባቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያ ችህግሯን በሰላማዊ መንገድ በውይይት ከጨረሰች ሻዕቢያን በሚገባው ቋንቋ ማናገር የቀናት ጉዳይ እንደሚሆን የተረዱት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ቀደም ሲል ጀምሮ ያደርጉት እንደነበር አሁንም ታጣቂ ኢትዮጵያ ላይ እያደራጁ በመላክ ላይ እንደሆኑ መንግስት ከበቂ በላይ መረጃ እንዳለው እየተገለጸ ነው።
ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር ሆነው የሚሰሩ ክፍሎች በኢትዮጵያ በአፋጣኝ የመንግስት ለውጥ እንዲያደርጉ በተቀመጠ አግባብ እየሰሩ መሆኑን መንግስት ስምና አገር ሳይጠቅስ ሰሞኑን ከቀናት በፊት ማስታወቁ አይዘነጋም።