የሰው ልጅ ዛሬ ለደረሰበት ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤ የብሩህ አዕምሮ ባለቤቶች የተለያዩ ሀሳቦችን አፍልቀዋል፣ ፍልስፍናቸውን አንፀባርቀዋል፣ እምነቶችን ፈጥረዋል፣ ምርምሮችን አድርገዋል፣ አስተምህሮቶችን ከጊዜ ወደ ጊዜ አሻሽለዋል፡፡ ቬሪያል ቶፕሊስት ኢሊትስ የተሰኘ የመረጃ ምንጭ አለምን የቀየሩ አስር ሳይንቲስቶችን ስም ዝርዝር አውጥቷል፡፡
10. አርስቶትል (384 – 233 ዓመተ ዓለም)
ይህ ግሪካዊ ፈላስፋ በተለያዩ መስኮች አዳዲስ ሀሣቦችን አፍልቋል፡፡ እንስሳትንና እፅዋትን በባህሪያቸው በመመደብ ሌሎች ተከታዮቹ (ተተኪዎቹ) በጥልቀት እንዲያጠኑ በር ከፍቶላቸዋል፡፡
9. አርኪመድስ (287 – 212 ዓመተ ዓለም)
ግሪካዊው አርኪመድስ ዛሬ የሰውን ልጅ ህይወት ያቀለሉትን የሒሳብና የፊዚክስ ትምህርት ቀመሮችን አበርክቷል፡፡ መላምትን ወደ ተግባር መለወጥ የጀመረ ሣይንቲስት ነው፡፡
8. ጋሊሎ ጋሊሊ (1564 – 1642 ዓመተ ምህረት)
ጣሊያናዊው ጋሊሎ ጋሊሊ አባቱ ህክምና እንዲያጠና ወደ ኮሌጅ ቢልኩትም የእሱ ፍላጐት ወደ ሳይንስና ሒሣብ በማዘንበሉ የትምህርት መስኩን ቀየረ፡፡ የመጀመሪያውን ቴሌስኮፕ በመስራት ፕላኔቶችንና ከዋክብትን በሰራው መሣሪያ ለማየት በቃ፡፡ ለጠፈር ምርምሩ ጉልህ ድርሻ አበርክቶ አልፏል፡፡
7. ሚካኤል ፋራዳይ (1791 – 1867 ዓመተ ምህረት)
በትውልድ እንግሊዛዊው ፋራዳይ ኤሌክትሪክን በመፍጠር አለምን ብርሐን አድርጓል
6. ቶማስ አልቫ ኤዲሰን (1847 – 1931 ዓመተ ምህረት)
ኤዲሰን በህይወት በቆየባቸው ዓመታት 1 ሺህ 93 ግኝቶችን ለአለም ለግሷል፡፡ ባትሪ፣ ቴሌግራፍ፣ የቁፋሮ ስራ፣ ሲሚንቶ ሐይል ወዘተ ግኝቶቹ መካከል ይጠቀሣሉ፡፡
5. ሜሪ ሉዋንዶስኪ (1867 – 1934 ዓመተ ምህረት)
የምድራችን የመጀመሪያዋ ሴት ሣይንቲስት ሜሪ ሱዋንዶሲኪ የመጀመሪያውን ተንቀሣቃሽ ኤክስሬይ (Mobile X- ray) በመፍጠር ሴቶችን ወደ ሣይንስ የሣበች እንስት ነበረች፡፡
4. ሊዊስ ፓስተር (1822 – 1895 ዓመተ ምህረት)
ሙሉ ህይወቱን በኬሚስትሪና በማይክሮ ባዮሎጂ ያሣለፈው ሊዊስ ፓስተር ነገሮችን ለማብላላት የሚያስችል ሣይንስን ፈጥሯል፡፡
3. ሰር አይዞክ ኒውተን (1643 – 1727 ዓመተ ምህረት)
የመሬት ስበት ህግን ለአለም አስተዋውቋል፡፡ ቁሳቁስን በቀላሉ ማንቀሣቀስ የሚችልበትንም ዘዴ አበርክቶ አልፏል፡፡
2. አልበርት አንስታይን (1879 – 1955 ዓመተ ምህረት)
የክፍለ ዘመኑ ምርጥ ሰው አንስታይን የጠለቁ የፊዚክስ ቀመሮችን በማውጣት አለምን ወደፊት ያንደረደረ የዘላለም ሰው ነው፡፡
1. ኒኮላ ተስላ (1856 – 1943 ዓመተ ምህረት)
ይህ ባለብሩህ አዕምሮ በሣይንስ ቴክኖሎጂ ቁጥራቸው የበዙ ፈጠራዎችን አበርክቷል፡፡ ስምንት ቋንቋዎችን አቀላጥፎ መናገር ይችል የነበረው ኒኮላ ተስላ ከእሱ በኋላ ለመጡ እንደነ ኤዲሰን፣ ዋትሰን ዋት ማረኮኒና መሰል ሣይንቲስቶች ለፈጠሯቸው ግኝቶች ተስላ ዋና መነሻቸው ነበር፡፡ “ተስላ ያልሰራው ስራ የለም” የሚል መለያንም አትርፎ አልፏል፡
በወጋየሁ አንዳርጌ addis linan