ኢትዮጵያውያን ለሃሳብ ሩቅ ነን። ጥናት የሰራ የለም። ሳይንሳዊ በሆነ መንገድም አልተረጋገጠም። ግን ብዙ ነገሮችን በቀላሉ በማስተዋል መደምደሚያው ለትክክልነት የተጠጋ መሆኑን እንገነዘባለን።
በቅርቡ ደጃፍ ቲቪ ፖድካስት ላይ አዘጋጁ ዳዊት ተስፋዬ ከአርቲስት ኪሮስ ኃይለሥላሴ ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር። ኪሮስ በ55 አመቱ ከብሔራዊ ቲያትር በግዜ ጡረታ ከወጣ በኋላ ሸገር ኤፍ ኤም ላይ ከአንድ ወዳጁ ጋር የሬዲዮ ፕሮግራም ጀምረው ነበር። የስፖንሰር ማስታወቂያ ሲያፈላልጉ ብዙ ድርጅቶች ኮሌጅ ነው የከፈታችሁት ወይ እያሉ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ይቀሩ ነበር። ይህን ሽሙጥ አዘል አስተያየት የጋበዘው፣ ማስታወቂያም ያሳጣቸው የፕሮግራማቸው ቁምነገር የበዛው ይዘት ነው። ቁምነገር አይፈለግም። የሚሰማ የለም። ድርጅቶችም ምርትና አገልግሎታቸውን በእንደዚህ አይነት ማንም በማይሰማው ፕሮግራም ማስተዋወቅ አይፈልጉም። አንድ!
ቴዎድሮስ ጸጋዬ ኢቢኤስ ቲቪ ላይ ከጥቂት አመታት በፊት ርእዮት በሚል ስም የሃርድ ቶክ ወይም ብርቱ ወግ የሚል ፕሮግራም ጀምሮ ነበር። ከጥቂት ሳምንት በላይ አልዘለቀም። ምክንያት? አያስቅም። ሃሳብ እንጂ ቧልት የለውም። የሚያሳስብ እንጂ የሚያዝናና አልነበረም። ፕሮግራሙ ተመልካች አጣ። ልክ ሲጀምር አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን ሪሞታቸውን አንስተው ጣቢያውን ይቀይራሉ። ሁለት።
ጋዜጠኛ ደረጀ ሃይሌ አርትስ ቲቪ ላይ በነገራችን ላይ የሚል ፕሮግራም ነበረው። ደረጀ የተዋጣለት ቃለመጠይቅ አድራጊ ነው። አብዛኛዎቹ እንግዶቹ የፖለቲካ ሰዎች ነበሩ። ይሄም በይዘቱ ቁምነገር አዘል የሆነ ሃርድ ቶክ ነበር። ፕሮግራሙ ግን አልቀጠለም። የተመልካች ማጣት ሊሆን ይችላል።
እስቲ ለረዥም ግዜ ሳይቋረጡ የቆዩ ፕሮግራሞችን ተመልከቱ። ምንም የቁምነገር ጠብታ የሌላቸው በዋነኝነት በማዝናናት ወይም በማሳቅ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ከሾው አቅም እንኳን ከአስር አመታት በላይ የዘለቀው ሰይፉ ሾው የተወዳጅነት ሚስጥሩ ምንም አይነት እንግዳ ቢጋበዝ ቁምነገር ከማውራት ይልቅ ሳቅ መፍጠር ላይ ያተኮረ ስለሆነ ነው።
መዝናናት ምንም ነውር የለውም። ግን ሰው እንዴት 24 ሰአት ሙሉ ያገጣል? ቀልድ እኮ ቅመም ነው። ወጡ ውስጥም ትንሽ ነው ጣል የሚደረገው። ቅመም ሙሉ ወጥ ይሰራል እንዴ?! እስቲ ሲትኮሞችን ተመልከቷቸው። ከ20 እና 30 ደቂቃ በላይ አይዘልቁም። ሳቅ ጥፍጥ የሚለው እጥር ምጥን ሲል ነው።
ፌስቡክ ላይም እንምጣ። ብዙ ሰው የሚያነባቸው ሳቅ የሚፈጥሩ አጭር ፖስቶችን ነው። ረዘም ያለ ወይም ቁምነገረኛ ፖስት ማንም ዞር ብሎ አያየውም። ግዜ ማጣት አይደለም። ስር የሰደደ የሃሳብ ጥላቻ ነው። እንደ ህዝብ አፍቃሪ ቧልት ነን።
ባለፈው አንዱን በእውቀቱ ስዩምን ታውቀዋለህ ስለው እ! ኮሜዲያኑ አለኝ። በእውቀቱ ኮሜዲያን አይደለም። ገጣሚና የወግ ጸሐፊ ነው። ይሄን የሚያክል ትልቅ የስነጽሁፍ ሰው በኮሜዲያንነት ያስፈረጀው የማህበረሰቡ ሃሳብ ጠል አስተሳሰብ ነው። በእውቀቱን በጥልቅ ሃሳቦቹ የሚያውቁት ጥቂቶች ናቸው። አብዛኛው የሚያውቀው ሳቅ በሚያጭሩት ወጎቹ ነው። በእውቀቱ ጥልቅ ቁምነገር በቧልት እያዋዛ አሳምሮ መጻፍ ይችላል። ብዙዎች ግን በቧልቱ ስቀው ማለፍ እንጂ ከስር ያለውን ቁምነገር ነገሬም አይሉትም።
ኢትዮጵያ ውስጥ በሚዲያ ደረጃ ትልቅ ቁምነገር ይዞ ብዙ አድማጭ ማግኘት የተሳካለት ሸገር ኤፍኤም ብቻ ነው። ሸገርም ቢሆን አብዛኛው አድማጮቹ ጎልማሳዎች ናቸው። የወጣቶች ተመራጭ ሚዲያ አይደለም። ለሸገር ስኬት የመአዛ ብሩ አስተዋጽኦ ጉልህ ነው። ሸገር ጨዋታና ሸገር ካፌን በመሳሰሉ ፕሮግራሞቿ ጥልቅ ቁምነገር በማይቸክ አቀራረብ ለአድማጭ ጆሮ በማድረስ የብዙዎችን ቀልብ መያዝ ችላለች።
ሌላው የሃሳብ ድሃ መሆናችንን የሚያሳየው ያሉት አዝናኝ የቲቪ ፕሮግራሞች እንኳን ፎርማታቸው እንዳለ ከውጪ የተኮረጀ መሆኑ ነው፦
ሰይፉ ሾው — Late Show with David Letterman
የቤተሰብ ጨዋታ — Family Feud
እስማማለሁ አልስማማም — Deal or No Deal
ድንቅ ልጆች — Little Big Shots
Jeopardy — ጥያቄና መልስ
የቲቪ ፕሮግራሞች ብቻ አይደሉም የሚኮረጁት። መጻህፍት፣ ሙዚቃ፣ የቢዝነስ ሃሳብ ወይም ምርት ሁሉንም ከውጪ በመኮረጅ ቀዳሚ ነን። ሃሳብ ከሸቀጥ እኩል import እናደርጋለን። የቁስ ብቻ ሳይሆን የሃሳብ ድሃ ነን። ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ከራሳቸው አመንጭተው ለአለም ያበረከቱት አንድም አዲስ ሃሳብ የለም። ስልጡን የምንላቸው ሃገሮች አሳቢዎቻቸው፣ ፈላስፋዎቻቸው፣ ደራሲዎቻቸው፣ አርቲስቶቻቸው፣ ሳይንቲስቶቻቸው በየመስኩ አዳዲስ ሃሳብ በየግዜው በየመስኩ እያፈለቁ ነው አስደናቂ ስልጣኔ የገነቡት። ሃሳብ ከሌለ ስልጣኔ የለም። እያንዳንዱ ስልጣኔ የሚጀምረው በአዲስ ሃሳብ ነው። እስቲ ኢትዮጵያ ያልነበረ ምን ወጥ ሃሳብ አፍልቃለች? ለ3000 ዘመን በበሬ የሚያርስበትን መንገድ ያልቀየርን ማህበረሰብ ነን። ይሄን ያህል ነው የሃሳብ ድህነታችን። ሌሎች የሰሩትን ትራክተር እንኳን ኮርጀን መስራት አንችልም። የዚህ ሁሉ ምንጭ የትምርት ስርአቱ ነው። እሱ ራሱ ከውጭ የተኮረጀ፣ የሃገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ፣ ከተግባር ይልቅ ጽንሰሃሳብ በማነብነብ ላይ የተመሰረተ ደካማ ስርአት ነው። የሚፈጥረውም እንደ ገደል ማሚቶ መልሶ የሚያስተጋባ ስንኩል ትውልድ ነው።
ደግሞም የሌሎችን ሃሳብ ሸምድዶ መልሶ የሚያነበንበውን እንደ አዋቂ እንቆጥረዋለን። ማርክስ እንዳለው፣ ኔቼ እንዳለው፣ አንስታይን እንዳለው ብሎ የሌሎችን ሃሳብ ሲደግምልን አዋቂ ከሱ በላይ ላሳር ብለን እናጸድቅለታለን። የምናፈራውም ምንም የራሳቸው ሃሳብ የሌላቸው በተውሶ እውቀት የሚኮፈሱ ፊደላውያንን ነው። አዲስ ነገር የሚነግረንን አሳቢ ግን ምሁራን መች እንደዚህ አሉ ብለን አፉን ለማስያዝ እንፈጥናለን። የአዲስ ሃሳብ ጥላቻ በውስጣችን ስር የሰደደ አደገኛ ባህል ነው። ለሺህ አመታት ባለንበት የምንረግጠው ለዚሁ ነው። ካለን አካል ሁሉ የማንጠቀምበት አእምሯችንን ነው። የኢትዮጵያዊ አእምሮ ምንም ያልተነካ ጥሬ ነው። ስንወለድ የነበረንን አእምሮ ይዘን ነው የምንሞተው። አንድም ቀን ሳናስብበት ኑሯችንን ሳንለውጥ፣ አካባቢያችንን ሳናሻሽል እንደ ከብት ኖረን እንደ ከብት እንሞታለን። እስከ አሁን ስልጣኔ የገነባ እንስሳ የለም። ፈረሶች ከዛሬ 100 አመት በፊትና አሁንም ያው ናቸው። አያስቡም። ይወለዳሉ። ይበላሉ። ይራባሉ። ያረጃሉ። ይሞታሉ። ኢትዮጵያውያን ከፈረሶች የምንለየው ጥቂት ነው። ልብስ እንለብሳለን፣ አልጋ ላይ እንተኛለን። ከንቃት አንጻር ግን ከፈረሶች ብዙም አንለይም። አእምሮ እያለን እንደሌለን ነን። ፈረስ የማያስበው ማሰብ ስለማይችል ነው። ኢትዮጵያውያን የምንለብስ፣ የምንዘንጥ፣ የምንናገር ሃሳብ-ቢስ ፈረሶች ነን!!
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring