ቱር ደ ፍራንስ ከፈተኛ የሚባለው የዓለማችን የብስክሌት ውድድር ነው። በዚህ ውድድር ከአፍሪካ አንድም አገር አሸንፎ አያውቅም። ለዚህ ነው የኤርትራው ቢኒያም ታሪክ ሰራ የሚለው ዜና የጎላው።
ከውድድሩ ፍጻሜ በኋላ ቢኒያም በደስታ ሲያነባ፣ ተወዳዳሪዎቹም ፍጹም ድንቅ ተወዳዳሪ እንደነበር እየገለጹ ሲያከብሩት የታየው። በዕርግጥም ቢኒያም ለትውልድ አገሩ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ብሎም ለጥቁር ሕዝብ ታሪክ ጽፏል።
ቢንያም ግርማይ በዓለም ላይ ከፍተኛ ቦታ ላይ የሚቀመጠውን የቱር ደ ፍራንስ የፈረንሳዩን የብስክሌት ውድድር ስቴጅ 3 በማሸነፍ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ እንደሆነ የዓለም መገናኛዎች በስፋት የዘገቡት።
ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ ተፎካካሪዎቹ ወደ ቢኒያምን አንገርቱን በማቀፍ አድናቆት ሰጥተውታል። ታዳሚዎችም ስሙን እየጠሩ አወድሰውታል። ” እንኳን ደስ አለህ ! አንተ እጅግ ምርጡ ነበርክ ፤ በጣም ጠንካራ አትሌት ነህ፤ ለአፍሪካና ለዓለም ታሪክ ሰርተሃል ፤ እንኮራብሃለን ” በሚል ያከበሩትን ድምጽ በቪዲዮው መስማት ተችሏል።
” በሁሉም መንገድ ብርታት ለሆነኝና የደገፈኝ ፈጣሪዬ ይመስገን ” ሲል አምላኩን ከድሉ ጎን አግንኖ አምስግኗል። የኤርትራ ብሄራዊ ጀግና የሆነው ቢኒያም በተለያዩ ጊዜያት ባስመዘገበው ስኬት ” የአፍሪካ የብስክሌት ንጉሥ ” የሚል ማዕረግ የተጎናጸፈ ምርጥ ብስክሌተኛ ነው።
የውድድሩን ግዙፍነት፣ የተወዳዳሪዎቹን ብዛትና ጥራት፣ የፉክክሩን ሃያልነት በየዓመቱ ለሚከታተሉ ቢኒያም የፈጸመው ገድል እጅግ ታላቅ እንደሆነ ይረዳሉ። የዝግጅት ክፍላችን እንኳን ደስ አለህ ይለዋል።