በሠሜን ሸዋ ዞን ሙሎ ወረዳ የሚገኘው ኮር ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በጥምረት በመስራት የፅንፈኞችን ዓላማ ማክሸፉን የኮሩ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል መስፍን በየነ ገልጸዋል። ከተይዙት መካከል ፎቅ እየገነቡ ያሉ መኖራቸው ተናግረዋል።
“በአካባቢው የነዳጅ ዲፖ ለማቃጠልና ወደ ገብረ ጉራቻ ለጥፋት ቡድኑ ተተኳሽና አልባሳት ለማስተላለፍ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሸኔ የጥፋት ቡድኖችን በህዝቡ መረጃ ሰጪነትና በሰራዊቱ ብርቱ ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል” ሲል ያስታወቀው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የመረጃ መረብ ዘመቻው በስውር መከናወኑን አስታውቋል።
ኮሩ ባደረጋቸው ዘመቻዎች የሽብር ቡድኑ ሲጠቀምበት የነበረ ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪን ጨምሮ የተለያዩ የነብስ ወከፍና የቡድን መሳሪያዎች ከነተተኳሻቸው መማረካቸውን የገለፁት ከፍተኛ መኮንኑ፣ መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ በማይቀበሉና በህዝቡ መካከል ሆነው የጥፋት እንቅስቃሴ የሚፈፅሙት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጫ መስተታቸውን ዘግቧል።
እጃቸውን ለሰራዊቱ ከሰጡት የጥፋት ቡድኑ አመራሮች መካከል ጃል ኤሬሳ በህዝብ ስም በዝርፊያ ላይ ተሰማርተው ፎቅ እየገነቡ ያሉ የቡድኑ አመራሮች መኖራቸውን መስክረዋል። የመከላከያ ሠራዊቱ እየወሰደ ባለው እርምጃ አብዛኞቹ መደምሰሳቸውን፣ ቀሪዎቹ ደግሞ እጃቸውን ለመስጠት አጋጣሚ እየጠበቁ እንደሚገኙ ምርኮኞቹን ጠቅሶ ዘግቧል።
“ሰራ ሰራ አድርጌ ልመለስ” እያሉ ወደ ጫካ ተጠራርተውና የመሸኛ ፓርቲ እተደረገላቸው የሚያቀኑ መኖራቸውን ገልጸን መዘገባችን ይታወሳል። የሻሸመኔውን ምስክር ጠቅሰን ባሰፈርነው ዘገባ “በንጹሃን ደምና ህይወት፣ በህጻናት፣ በአዛውንቶችና ሴቶች መፈናቀል የሚነግዱ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የዘመኑ ታጋዮች፣ አክቲቪስቶች፣ ፖለቲከኞች፣ ሁለት ቦታ የሚጫወቱ የመንግስት ሃላፊዎች፣ የነዚህ ሁሉ ሚስቶች፣ ልጆች፣ ወዳጆችና ስራቸውን የሚያውቁ ሁሉ በየትኛውም ጊዜ ከፍርድ እንደማያመልጡ የምናውቅ ዕናውቃለን። አማኞች ሁሉ የጽድቅ ፍርድ በእነዚህ መዓተኞች ላይ እንዲወጣባቸው ያለቅሳሉና ፍርድ ሊበየን ግድ ነው” ሲሉ ዜናውን ያቀበሉን መናገራቸው ይታወሳል።