ያለገደብና በገደብ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች አሉ ከእነኚህ ውስጥ ያለ ገደብ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች‼️
1. ተቀጣሪ ሠራተኛው ሲታመም አሠሪው ለሠራተኛው ህክምና አገልግሎት የከፈለለት ገንዘብ፤
2. የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወይም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቦርድ አባል ወይም ፀሐፊ እንዲሁም የፌደራልና
የክልል መንግሥታት ወይም የከተማ አስተዳደሮች በሚያቋቁሟቸው የጥናት ቡድኖች አባል ወይም ፀሐፊ በመሆን የሚከፈል አበል፤
3. በመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ እና በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ከግብር ነፃ የተደረገ የጡረታ ገቢ፤
4. በዓለም ዐቀፍ ስምምነት መሠረት ከግብር ነፃ የሆነ የገቢ መጠን፤
5. በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በተደረገ ስምምነት መሠረት ማናቸውም ገቢ ከግብር ነፃ የሚሆነው፡- ስምምነቱ የተደረገው ለመንግሥት የገንዘብ፣ የቴክኒክ፣ ሰብአዊ ወይም አስተዳደራዊ እርዳታ ለማቅረብ የሆነ እንደሆነ እና ከግብር ነፃ ማድረግ የሚያስችለውን አንቀጽ በሚመለከት ሚኒስትሩ መስማማቱን በጽሁፍ ሲገልጽ
6. በማንኛውም መስክ ለላቀ የሥራ ክንውን የሚሰጥ ሽልማት፣
👉 አንድን ቴክኖሎጅ ለማሻሻል፣ አዲስ የፈጠራ ስራ በመስራት ወይም ወጪን ለመቀነስ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ስራ ላይ በማዋል የሚሰጥ ሽልማት
👉 በአለም አቀፍ ደረጃ በሚደረግ ውድድር አገርን ወክሎ ወይም በሀገር አቀፍ ደረጃ በህግ በተቋቋመ ድርጅት በሚደረግ ማንኛውም ውድድር የሚሰጥ ሽልማት
👉 በፌደራል፣ በክልል፣ በአዲስ አበባ እና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር መንግስት የላቀ የስራ ክንውን ላስመዘገበ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት የሚሰጥ ሽልማት ሲሆን ሽልማቱ ከገቢ ግብር ነጻ ሊሆን የሚችለው ከፈጠራ ስራው ጋር ግንኙነት ያለው የመንግስት አካል ለፈጠራ ስራው እውቅና የተሰጠው ወይም የፈጠራ መብት ሲኖረው ነው
7. በተቀጣሪው ላይ በደረሰ ጉዳት ወይም በሌላ ሰው ሞት ምክንያት የሚከፈል ካሳ፤
8. ስጦታው የመቀጠር፣ የኪራይ ወይም የንግድ ሥራ ገቢ ካልሆነ በስተቀር በስጦታ ወይም በውርስ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብ ወይም ሀብት፤
9. በትምህርት ተቋም ውስጥ ትምህርትን በነፃ ለመከታተል የሚፈፀም ክፍያ፤
10. ለቀለብ ወይም ለህፃናት ድጋፍ የሚሰጡ ክፍያዎች፤
11. ድርጅቱ ከተቋቋመበት ዓላማ ጋር የማይገናኝ የንግድ ሥራ ገቢን ሳይጨምር ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት የሚያገኘው ገቢ፤
12. ገንዘብ በሚቆጠርበት ጊዜ ለሚደርሰው ጉድለት ማካካሻ በሚሆን መጠን ብቻ ቀጣሪው ለተቀጣሪው የሚከፍለው እና ለዚሁ ዓላማ መዋሉ የተረጋገጠ የጥሬ ገንዘብ ማካካሻ ክፍያ፤
13. በኢትዮጵያ ፀንቶ በሚሰራበት ሕግ መሠረት በተለይ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረገ ገቢ፤
14. ለመኖሪያ ቤት ሠራተኞች የሚከፈል ደመወዝ፤
15. በነዳጅ ሥራ ላይ የተሰማራ ሥራ ተቋራጭ ለንዑስ ሥራ ተቋራጮች የሚፈፅመው ክፍያ፡፡
16. ለኢኮኖሚ፣ ለአስተዳደራዊ ወይም ለማህበራዊ ምክንያቶች አንድን ገቢ ከገቢ ግብር ነፃ ሊያደርግ እንደሚችል ባመለከተው መሠረት የሚከተሉት ገቢዎች ከገቢ ግብር ነፃ ናቸው፤
– በወጪ ንግድ ሥራ ላይ የተሠማሩ ባለሀብቶች ለእውቀት ሽግግር ከውጭ ሀገር ለሚያስመጧቸው ባለሙያዎች ከአምስት ዓመት ላልበለጠ ጊዜ የሚከፈላቸው ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ፤
– በማንኛውም የአስራ ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ለአንድ ቀጣሪ ሳያቋርጥም ሆነ በተደጋጋሚ ከሠላሳ ቀናት ላልበለጠ ጊዜ ያገለገለ ማንኛውም ባለሙያ ያልሆነ ተቀጣሪ የሚያገኘው ገቢ፤ሆኖም በአስራ ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ አንድ ሰው በተደጋጋሚ ለአንድ ቀጣሪ የሰጠው አገልግሎት ሲደመር ከአንድ ወር የሚበልጥ ከሆነ ተቀጣሪው የሚከፍለው ግብር የሚታሰበው በመጨረሻው ቅጥር ባገኘው ገቢ ላይ ብቻ ይሆናል ፡፡
– “ባለሙያ ያልሆነ ተቀጣሪ” ማለት መደበኛ የሙያ ሥልጠና ያልወሰደ ልዩ ሙያ በሚጠይቁ ማሽኖችና መሣሪያዎች የማይጠቀም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በጠቅላላው ከ30 ቀናት ለማይበልጥ ጊዜ የተቀጠረ ግለሰብ ነው፡፡
– ከግብር ነጻ የተደረገው አሠሪው ሠራተኛው ሲታመም ለሠራተኛው ህክምና አገልግሎት የከፈለለት ገንዘብ በሠራተኞች የጤና መድን ዐቅድ መሠረት አሠሪው ለሠራተኞች ጥቅም የሚከፍለውን አረቦን ይጨምራል ፡፡
– ለኮንስትራሽን ማሽነሪ ኦፕሬተሮች የሚከፈለው ውሎ አበል ከ25ኪ.ሜ. ባነሰ ወይም በበለጠ ርቀት ቢሆንም የተከፈለው የውሎ አበል ከግብር ነፃ ይሆናል፡፡
– የመንግስት መስራያ ቤት ለተሿሚዎች እና ለተቀጣሪዎች ከመደበኛ የስራ ቦታቸው ውጭ ከ 25 ኪ.ሜ. በላይ ርቀው በመሄድ ለሚያከናውኑት ሥራ የሚከፈል የቀን ውሎ አበል ሙሉ በሙሉ ከግብር ነፃ ነው ፡፡
ምንጭ የገቢዎች ሚኒስቴር
ሐምሌ 13 ቀን 2016 ዓም
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring