ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽኑሀምሌ 17/2016 ዓ.ም ይካሄዳል ተብሎ ከሚጠበቀው ጉባኤ ራሱን ስለማገለሉ የሚመለከት ይፋዊ መግለጫ አውጥቷል።
ድርጅቱ በቀጣይ ትግል ይስተካከላል በሚል ከማእከላዊ ኮሚቴ ፣ ከቁጥጥር ኮሚሽን ፣ ከአባላት የተውጣጣ 9 አባላት ያሉት የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ተቋቁሞ እንደነበር አመልክቷል።
ይሁን እንጂ የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴና የቁጥጥር ኮሚሽን ባካሄዱት ግልፅ መግባባት ስራቸው ቢጀምሩም ከተቀመጠው የጋራ አሰራር ውጪ ኢ-ዴሞክራሲያዊ የሆነ አሰራር መስፈቱን ችግሩ እርማት እንዲወሰድበት የቀረበውም ጥያቄ ተቀባይነትና ሰሚ እንዳላገኘ ጠቁሟል።
” የህወሓት 14ኛው ጉባኤ ዝግጅት ሂደት የበላይነት አለኝ በሚል ሃይል ተጠልፎ ወደ አደገኛ ሁኔታ እያመራ ነው ” ያለው ኮሚሽኑ ግልፅነትና ዴሞክራሲያውነት የጎደለው አካሄድ የሚያስከትለው አደገኛ መዘዝ በመረዳት ኮሚሽኑ ከጉባኤው ራሱ ማግለሉም አሳውቋል።
በዚሁ መሰረት ፦
1ኛ. በጉባኤው ዝግጅት እንዲሳተፉ የተወከሉ የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት ከዝግጅት አባልነታቸው እንዲነሱ መደረጉን አመልክቷል።
2ኛ. የቁጥጥር ኮሚሽኑ አካሄድ ወደ ጎን በመተው አደገኛ አካሄድ በመከተል ጉባኤ አካሂዳለሁ የሚለው ሃይል ወደ ሙሉ መተማመን እስኪደረስ ድረስ ማእከላዊ ኮሚቴ ሃላፍነት ወስዶ ከድርጊቱ እንዲያቆመው ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን በጥብቅ አስጠንቅቋል።
3ኛ. ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽኑ የሚያቀርበው ጥያቄና አቋም ወደ ጎን በመተው የጉባኤው ዝግጅት ከቀጠለ በዚሁ ሂደት ለሚከተለው ማንኛውም አደጋ ሃላፊነት የሚወስደው ራሱ ጉባኤ አካሂዳሎህ የሚለው አመራር መሆኑን ሊታወቅ ይገባል ብሏል።
ትላንትና የህወሓት የቁጥጥር ኮሚሽን ” ህወሓት በሁለት ኔትወርክ ተከፍሎ እየታመሰ ነው ” ማለቱ ይታወሳል።
@tikvahethiopia