ክቡር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች ታላቅ ሀገር በመሆኗ ማንም በማንም ላይ ጫና ፈጥሮ መኖር የሚችልበት ሀገር አይደለችም ያሉት በተቋሙ የ2016 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ግምገማ ላይ ነው።
የሀገራችንን ህዝብ ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅና ለሕገ-መንግስቱ ዘብ ለመቆም እንደ መለዮ ለባሽ በገባነው ቃል መሠረት በቁርጠኝነት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል ክቡር ኮሚሽነር ጀነራሉ።
በበጀት ዓመቱ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ገቢና ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በመያዝ እና ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር እና ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ከመቆጣጠር አንፃር ውጤታማ ሥራዎችን መስራቱን አንስተዋል።
ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል አያይዘውም የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ከፌደራልና ከክልል ፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ አሽባሪዎችንና ፅንፈኞችን በመቆጣጠርና አኩይ ዓላማቸውን በማክሸፍ አንፃር ትላልቅ ሥራዎችን ያከናወነበት ዓመት ነበር ብለዋል።
የኦፕሬሽን አቅም ለማሳደግ አመራሩንና አባሉን ጭምር በማሰልጠን ረገድ ከፍተኛ ሥራ የተሠራ ሲሆን በርካታ ሰልጣኞች በሥልጠና ውስጥ እንዲያልፉ በመደረጉ ኦፕሬሽን ላይ ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን አንስተው ስልጠናው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
በተመሳሳይ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ሀገራችንን ለማፍረስና ችግር ውስጥ ለመክተት የሚንቀሳቀሱ አሸባሪዎችና ፅንፈኛ ኃይሎችን በመቆጣጠር እና ዓላማቸውን በማክሸፍ በሕግ ተጣያቂ እንዲሆኑ የተለያዩ ችግሮችን በቁርጠኝነት ተሻግሮ ተጠያቂ እንዲሆኑ አድርጓል። ይህም የፖሊስ የምርመራ አቅም ምን ያህል እያደገ እንደመጣ ያሳየና ወንጀለኞች ይቺን ሀገር ማፍረስ እንደማይችሉ ያረጋገጠ ነው ብለዋል ክብር ኮሚሽነር ጀነራሉ።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ለከፍተኛ አመራሮቹ ቀርቦ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል በቀረበው ዕቅድ ላይ አንድ በአንድ ትንታኔ ከሰጡ በኋላ በዕቅዱ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ ከሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በየደረጃው ያለው አመራር ተፈራርሞ ወደ ስራ እንዲገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
‚‘ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች ታላቅ ሀገር በመሆኗ ማንም በማንም ላይ ጫና ፈጥሮ መኖር የሚችልበት ሀገር አይደለችም።“ ክቡር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል

Ena