በካፋ ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በካፋ ዞን በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተመላክቷል፡፡
በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ሚዲዮ ጎምበራ ቀበሌ ትናንት ምሽት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ የሞት፣ በአንድ ሰው ላይ የአካል ጉዳት እንዲሁም 24 የአከባቢው ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡።
አደጋው በተከሰተበት አከባቢ ከጠሎ ወደ ቦንጋ የሚያስኬድ አስፓልት መንገድ ላይ በናዳ ተዘግተው መጠነኛ ጉዳት የደረሰ ቢሆንም የአከባቢው አስተዳደር ከነዋሪዎች ጋር ተረባርበው መንገዱ አሁን ለትራፊክ ክፍት መሆኑን ነው የክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ለማ መሰለ (ዶ/ር) የገለጹት።
ኮሚሽነሩ ለክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን በሰጡት መግለጫ በአደጋው ጉዳት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን በአንድ ጊዜያዊ መጠለያ በማቆየት የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ስራው በዞኑና በወረዳው መዋቅር እየተከናወነ መሆኑ ነው የጠቆሙት።
የዝናቡ ሁኔታ ቀጣይነት ያለው በመሆኑ ቀድመ ማስጠንቀቂያ በተሰጠባቸው የክልሉ አከባቢዎች ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያሳሰቡት ዶ/ር ለማ በነዚህ ቦታዎች ያሉ የህብረሰብ ክፍሎች የአከባቢው አስተዳደር አካላት ወደ ሚያዘጋጁት ጊዜያዊ መጠለያ መግባት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring