” በኮሚቴው ስራ ውስጥ የሚታዩ ጣልቃ የመግባት ፣ ከፕሮግራም ውጪ ስብሰባ መጥራት፣ ውሳኔዎችን መጠምዘዝ የመሳሳሉ ተግባራት እንዲታረሙ ለመስራት ብሞክርም አልተሳካም ” ብለዋል።
” የምታገልበት ድርጅት ዴሞክራሲያዊ ፣ ግልፅና አሳታፊ መሆኑ አምናለሁ ” ያሉት ምክትል ሰብሳቢው ” ሆኖም በኮሚቴው ስራ ውስጥ ልቋቋማቸው የማልችላቸው አካሄዶች እየታዘብኩ ነው ” ሲሉ አብራርተዋል።
” ይህንን ስርዓት የለሽ አካሄድ ከእምነቴ ፣ ከትግል አቋሜና ከሞራሌ የማይሄድ በመሆኑ ከሀምሌ 13/2016 ዓ.ም ጀምሮ ከሃላፊነቴና ከኮሚቴ አባልነቴ አግልያሎህ ” ብለዋል።
” የድርጅቱ አባልና አመራር ግልፅ እንዲሆንለት እስካሁን የገጠሙኝ እንቅፋቶችና ንቀት በመደበኛ ሚድያ ይፋ አደርጋለሁ ” ብለዋል።
አቶ ተስፋይ የትግራይ ልማት ማህበር ስራ አስፈፃሚም ናቸው።
@tikvahethiopia