የኢኮኖሚ ባለሙያው ዋሲሁን በላይ “ገንዘብ ማዳከምና ምንዛሬን በፍላጎትና አቅርቦት መመጠን ይለያያል” ይላሉ
ውሳኔው የማይጠበቅ ነው ብዬ መናገር አልችልም። ግን በዚህ ፍጥነት መሆኑ ለእኔ አስደጋጭ ነው በሚል አሳባቸውን ያጋራሉ
– በእርግጥ አሁን የተደረገው devaluate /ገንዘብ ማዳከም/ አይደለም። devaluation ማድረግ እና floating ይለያያል።
– devaluate የገንዘቡን የመግዛት አቅም በተወሰነ መልኩ በመንግስት ውሳኔ ማዳከም ማለት ነው። አሁን ግን እንደዛ አይደለም የተደረገው። አሁን የተደረገው በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ስርዓት / floating / ነው።
– የውጭ ምንዛሪ ተመን በ3 መልኩ ይመራል።
1. fixed exchange rate / በመንግስት ውሳኔ / መንግስት አንድ ዶላር በዚህ ያህል ብር ነው የሚወሰነው ብሎ ድርቅ ሲያደርግ በዛ ብር ብቻ ነው የሚወሰነው ሲል።
2. floating managing ኢትዮጵያ እስከ ዛሬ ስትመራበት የነበረው ነው። በመንግስት ውሳኔ አለው ግን በየቀኑ መንሸራተት ያለው ነው። በየቀኑ የሚምሸራተት ነው። በምዛሬው ላይ በየዕለቱ ለውጥ የሚታይበት ነው። መንግስት መነሻውን እያስቀመጠ ገበያው እየወሰነ ሲቆይ ነው።
3. floating በገበያው ላይ ባለው ፍላጎት እና አቅርቦት ገንዘብ ከዶላር አንጻር ሲመራ ነው። አሁን መንግስት የወሰነው በገበያው ላይ ባለው ፍላጎት እና አቅርቦት ገንዘብ ከዶላር አንጻር እንዲመራ ነው (floating exchange rate)።
– ብዙ floating እያደረጉ የሚመሩ ሀገራት አሉ ያደጉ ሀገራትን ጭምር።
– floating የሚመራው እንዴት ነው ? ብሔራዊ ባንክ 1 ዶላር በዚህ ብር ይመንዘር ማለት አይችልም። ለኢትዮጵያ ብር ያላቸው ፍላጎት ኢትዮጵያ ለውጭ ምንዛሬ ያላት ፍላጎት ዓለም አቀፍ ገበያው ላይ ያለው እንቅስቃሴ ከግምት ይገባል። ገበያው የዕለቱን ፍላጎት ይወስናል። በዕለቱ ዶላር በጣም ከተፈለገ ከፍ ይላል። ካልተፈለገ ዝቅ ይላል።
– floating ለገበያ በጣም መጥፎ ላይሆን ይችላል ግን በቂ የዶላር reserve ኢኮኖሚው መያዝ አለበት። floating በተጀመረ በጀንበር ውስጥ ገበያው ብዙ ሊለዋወጥ ይችላል። ፍላጎት ካለ ዶላር አሁን ካለው በእጥፍ ሆኖ ሊያድር ይችላል። ይህ ደግሞ ገበያውን ያናጋዋል። ስለዚህ ይሄን የሚያመጣጥን ብቂ የዶላር reserve በባንክ ቤቶች በብሄራዊ ባንክ ይዞ መገኘት ይገባል።
– floating ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ብቻ ነው ብሎ መናገር አይቻልም። የውጭ ጫና፣ ብድር ፣እርዳታ ፍለጋም ስላለበት ኢኮኖሚው ስለሚጠቀም ብቻ ሳይሆን የIMF ዓለም አቅፍ ተቋማትም ጫና ስላለ እሱን ለመቋቋምና በቀጣይ ትብብራቸውን ለማግኘት ሲባል ሊወሰን ይችላል።
– ገበያው በጣም shock / መናጋት የሚጠብቀው እንደሆነ ምንም ክርክር የሚያስፈልገው አይደለም። መጀመሪያ የሚሆነው import በጣም ውድ ያደርገዋል። floating ሲደረግ ገንዘብ devaluate መሆኑ / መዳከሙ አይቀርም። ይህ ማለት ወደ ጥቁር ገበያው ወዳለው ተመንና ከዛም ከፍ እያለ ነው የሚሄደው።
– ከባንክ ላይ 58 ብር ገዝተው / በጥቁር ገበያው ተመን ገዝተው ወደ ገበያው import ያደርጉ የነበሩ አሁን floating ከሆነ በጣም በከፍተኛ ገንዘብ 1 ዶላርን መግዛታቸው አይቀርም። በዚህም ከውጭ የገዙት ቁሳቁስ ሀገር ውስጥ ሲገባ ውድ መሆኑ አይቀርም። ይሄን መንግስትም የሚያምነው ነው።
– ኢትዮጵያ ውስጥ ሸቀጣሸቀጥ ብቻ ሳይሆን ለProduction የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች import ይደረጋሉ፤ ስለዚህ ውድ መሆናቸው አይቀርም።
– በፍጹም ደመወዝ አልጨምርም ‘ የሚለው ዜና አሁን ደመወዝ እጨምራለሁ እደጉማለሁ እያለ ነው። ‘ ከነዳጅ ድጎማ እራሴን አወጣለሁ ‘ ይል የነበረው ዜና አሁን መደጎሜን እቀጥላለሁ እያለ ነው። ስለዚህ import ቁሳቁስ ውድ እንደሚሆን ያሳያል።
– floating የተወሰኑ አካላትን ተጠቃሚ ሊያደርግ ይችላል። ሌሎችን ተጎጂ ሊያደርግ ይችላል። ለምሳሌ ፦ በ58 ብር ተመን ጊዜ ዶላር ይዘው የነበሩ ሰዎች ምንዛሬ ሲጨምር የሆኑ አካላት ተጠቃሚ መሆናቸው አይቀርም በግልባጩም እንደዛው ነው።
– ብዙ ነገሮች import ስለሚድሩግ ገበያው ላይ ተፅእኖ ማሳደሩም አይቀርም።
– የውጭ ቀጥተኛ investment ላይ ማሻሻያው ጥሩ ጎን ሊኖረው ይችላል። አንድ ዶላር ይዞ የመጣ የውጭ ባለሃብት በ58 ብር ይገዛ ነበር አሁን floating ከሆነ devaluate ከተደረገ ይዞት የሚመጣው ከፍ ያለ ይሆናል ምንዛሬው።
– በቀጣይ ጊዜ የውጭ ባላሃብቶች ወደ ገበያ ብስፋት እንዲገቡ ሊያደርጋቸው ይችላል።
– በዚህ ወቅት floating መደረጉ ግን በግሌ በጣም አስደንጋጭ ነው። በዚህ ፍጥነት ይሆናል ብዬ አልገምትኩም። “
tikvahethiopia
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring