በመጪው በጀት አመት ትልቅ ፈተና ሆኖ ያለወን የኑሮ ውድነትን ለመፍታት ምን ታስቧል፤
የአገሪቷ ኢኮኖሚን በተመለከተ በተለያዩ አካላት የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ነውና ኢኮኖሚው ያለበት ደረጃ እንዴት ይገለጻል፤
የአገሪቷን ሀብት አሟጥጦ ለመጠቀም መንግስት ምን እየሰራ ነው
በኢንዱስትሪ መስከ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ቢሰጥ፤
ሙስና ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፤ መንግስታዊ አገልገሎትን ማግኘት ያለሙስና የማይቻል እየሆነ ነው። ይህንን ችግር ስር የሰደደ ሙስና ለመፍታት ምን ታስቧል፤ በተደጋጋሚ ቃል ከመግባት ባለፈ ህዝብ ምን ይጠብቅ ፤
የቀጣይ በጀት አመት የዋጋ ግሽበት እንዳይፈጥር ምን ታቅዷል፤
የመንግስት ገቢን ለማሳደግ ምን ታቅዷል፤
ከሀገራዊ ምክክሩ በፊት መቅደም ያለበት መተማመን መፍጠር ነው። በአማራ ክልል በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሟል፤ የታሰሩ ዜጎችም አሉ። በዚህ ዙሪያ ምላሽ ቢሰጡን፤ ይሄ ባለበት ሁኔታ እንዴት ስለ ምክክር ኮሚሽን ልናወራ እንችላለን፤ መጀመሪያ እመነት መገንባት መቅደም አለበትና መ ንግስት በዚህ ዙሪያ ምን የወሰነው ጉዳይ አለ፤
አገራችን ከውጭ ጠላቶችና የውስጥ ባንዳዎች በጋራ የከፈቱብንን ጥቃት በመመከት አገራችን አንጸባራቂ ድሎችን እያስመዘገበች ቀጥላላች። ለዚህ ደግሞ የእርስዎ አመራር ትልቅ ድርሻ አለው። ከሰላም አንጻር ምን ለመስራት ታስቧል፤
የሙስና ችግርን ለመፍታት ምን ተግባራዊ እርምጃ ለመውሰድ ታስቦዋል፣ በሀገሪቱ የታጠቁ ሀይሎችን ወደ ሰላም ለመመለስ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ላይ ማብራሪያ ቢሰጥበት፤
በበጀት እጥረት ምክንያት በአዲስ የተዋቀሩ ክልሎች ለሰራተኞቻቸው ደሞዝ ለመክፈል እየተቸገሩ ነው እነዚህን ክልሎች መንግስት በቋሚነት ለመደገፍ ምን እየተሰራ ነው፣
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥብ
👉 ለውጡ ያስፈለገው ሰው ለመቀያየር አይደለም፤ ስብራቶቻችንን ለማከም ነው፤
👉 አንዱ ስብራታችን የነበረው የኢኮኖሚ ስብራት ነው፤ በአገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲዎቻችንን እዳን ቀንሰናል፤
👉 በማንኛውም ጉዳይ ብትመረምሩ ሙስናን ጨምሮ ታግለን ላመጣነው ፍሬ እውቅና የመስጠት ባህል የለንም፤
👉 ለውጡ በፖለቲካው መስክም ከኤርትራም ከኬንያም ከጫካም ያሉትን ጋብዟል፤
👉 የሰላም ችግር በአገራችን ውሎ ያደረ ስር የሰደደ በሽታ ነው፤
👉 ኢትዮጵያ ውስጥ መፈንቅለ መንግስት ጭራሽ አይሳካም፤
👉 አንድ እንሁን ሰብሰብ እንበል የጋራ አገር ነው ያለን፤
👉 በአማራም በኦሮሚያም ክልል ያለው ችግር በሁለት ተከፍሎ የሚታይ ነው፤
👉 አንደኛው ዱር ግባ የሚል ፕሮፖጋንዳ ሰለባ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ ጥራኝ ዱሩ የሚል ነው፤
👉 አማራ ኦሮሚያ ትግራይ ሰላም ካልሆነ የመጨረሻ ተጎጂ እኛ ነን፤ ያሰብነውን መስራት አንችልምና፤
👉 በፕሪቶሪያ ስምምነት ምክንያት ተኩስ ቆሟል፤ የሚሞት ሰው ቆሟል፤ የታሰሩ ተፈተዋል፤ የቆሰሉ ታክመዋል፤ ከስራ የታገዱ ስራ ይዘዋል፤ የተለያዩ ቤተሰቦች ተገናኝተዋል፤
👉 የትግራይ ህዝብ ያገኘው እፎይታ የእኛም እፎይታ ነው፤
👉 በራያና ጸለምት የተፈናቀሉ ሰዎች እየተመለሱ ነው፤
👉 በትግረይ ክልላዊ ሽግግር መንግስት በህወሓት ዋና ዋና መሪዎች ላይ እምነት አለኝ፤ ችግሩ በሰላም እንዲፈታ ፍላጎት አላቸው፤
👉 አሁንም ግን እልህኘነትና ቁጣ ያላቸው አሉ፤ ይሄ አካሄድ ይጎዳል፤
👉 እኛ አማራም በኦሮሚያም በትግራይም ግጭት አንፈልግም፤