ዛሬ ከረፋዱ 4:00 ሰዓት አካባቢ፤ በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ ሰዎች ሕይወት አልፏል።
የወረዳው ዋና አስተዳደር ፥ እሰካሁን በተደረገው ፍለጋ ከ 20 በላይ አስከሬን መገኘቱን አመልክቷል።
የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ተገልጿል።
በስፍራው ለነፍስ አድን ተግባር የተሰበሰቡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የአካባቢው ነዋሪዎች የአደጋው ሰለባ መሆናቸውን ተሰምቷል።
በአደጋው ሰለባ ከሆኑት ሰዎች መካከል የወረዳው ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ሴቶችና ሕፃናት እንደሚገኙ ተገልጿል።
በአሁኑ ሰዓት የአስክሬን ፍለጋና የነፍስ አድን ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ገዜ ጎፋ ወረዳ