የማሊ መንግስት ሽብርተኝነትን ለመመከት ድጋፍ ይደረግላቸው ዘንድ ያቀረበውን ግብዣ ተከትሎ በሃገሪቱ የተሰማራው የሩሲያው ዋግነር ላይ የቱዋሬግ ቡድን በተደጋጋሚ ያሳየው የጥቃት እንቅስቃሴ ፈረንሳይ ባህል ቀጣና ባለፉት አስርት ዓመታት ያልተሳካላትን የጣልቃ ገብነት ጥረት ተከትሎ ይህን ታጣቂ ቡድን በተዘዋዋሪ የመደገፍና የማፈርጠም ተግባር መከናወኑን ያመላክታል ተብሏል።
ዋግነር ላይ ከሰሞኑ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በሩሲያ ፓርላማ ‘State Duma’ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር አሌክሲ ቼፓ በጥቃቱ ተጠያቂ ያሏቸውን አካላት ጠቅሰዋል። በዚህም “በዋግነር ፒ.ኤም.ሲ. ተዋጊዎች ላይ ማሊ ውስጥ ጥቃት ያደረሱት የቱዋሬግ አሸባሪዎች በፈረንሳይ እና በዩናይትድ ስቴትስ የሚደገፉናና የሚታዘዙ ናቸው። ሩሲያ ለእነዚህ አገሮች ምላሹን መስጠት አለባት።” ብለዋል።
የዋግነር ወታደሮች ጥቃቱ የተሰነዘረባቸው ከአሸባሪው ቱዋሬግ ቡድን ጋር ውጊያ ለሚያደርገው የሀገሪቱ ጦር እገዛ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ በነበረበት ወቅት ነው።
በወቅቱ የነበረው የአሸዋ ማዕበል የዋግነር የጦር ጄቶች ስራ ላይ ለመዋል አዘግይቷቸዋል። በስራ ላይ የነበረች አንዲት የዋግነር ሄሊኮፕተር በተገንጣዮቹ የቱዋሬግ አሸባሪዎች ተመትታለች ተብሏል።
የጥቃቱን ዝርዝር አስመልክቶ የወጡ ሪፖርቶች እንደሚሉት “የዋግነር ጦር የቱዋሬግ አማፂያን ወደተያዙ ጠንካራና ዋነኛ ማዕከል ወደሆኑ የጎሳ ግዛቶች ዘልቀው በመግባት አማፂ ቡድኑን ወደ አልጄሪያ ድንበር የማሳደድ ዘመቻ ላይ ለደፈጣ በተዘጋጀ የጥቃት ወጥመድ መጋለጡንና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችም ለከፍተኛ ጥቃት ተጋልጠዋል።
በጥቃቱ 50 የሚጠጉ የዋግነር ወታደሮች መሞታቸው የታወቀ ሲሆን፣ ከተረፉት መካከል የሆነው አንድ የዋግነር እና ሌሎች የማሊ ወታደሮች በቡድኑ ተይዘው ተወስደዋል።
አንዳንድ ዘገባዎች ደግሞ የቀድሞው የዋግነር አዛዥ የፕሪጎዢን Prigozhin ተተኪ መሞቱን ይናገራሉ። በሌላ በኩል የዋግነር ጦር ዘጋቢው ቦሪስ ሮዝሂን ስለ እስረኞቹ ሲናገር “ከእስረኞቹ መካከል ታዋቂው የፕሪጎዢን ተተኪ አዛዥ ይገኝበት ነበር። ነገር ግን ቀደም ሲል በእስረኛ ልውውጥ ሊመለስ ችሏል ነው ያለው። ይሁንና በዚህ ዙሪያ የተገኘ ማረጋገጫ ለጊዜው የለም።
ከተገደሉት መካከል የ GRAY ZONE ቴሌግራም ቻናል አስተዳዳሪው ኒኪታ ወይም “ቤሊ” ይገኝበታል። ይህ ጥቃት የማሊ መንግስት የአሸባሪ ቡድኖችን ለመደምሰስ ሲያደርግ በቆየው ስኬታማ ዘመቻ ላይ ያጋጠመ ከፍተኛ ጥቃት ነው የተባለ ሲሆን፣ በተያያዙ ትንተናዎችም ሩሲያ በምዕራብ አፍሪካ አካባቢዎች የጀመረችው የፀረ ሽብር ዘመቻዋን ለማስቀጠል አዲስና መጠነ ሰፊ ግብአት በማዘጋጀት ሊሆን ይገባል የሚሉት በጉልህ ከሚሰነዘሩት ውስጥ ሆነዋል። ምዕራባዊያኑ ሀገራት ቀደም ባሉ አመታት አሸባሪ ይሉት የነበረውን የቱዋሬግ ቡድን የሩሲያው ዋግነር በአካባቢው መሰማራቱን ተከትሎ በወርሃ ሐምሌ 2022 ላይ "ቱዋሬግ ‘ፅንፈኛ አማፂዎች’ እንደሆኑ አድርገው መግለፅ መጀመራቸው ይታወሳል። በዚሁ ወርሃ ሐምሌ 2022፡ “የአልቃይዳው የማሊ ቅርንጫፍ በሩሲያ ላይ ይፋዊ ጦርነት አውጀናል” ማለቱም አይዘነጋም። በመቀጠል በወርሃ ግንቦት 2023 ታዋቂው Politico እንዳስነበበው “አሜሪካ በዋግነር ላይ የተቀናጀ hybrid ጦርነት ለማካሄድ ማቀዳቸውን ከአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት መስማቱን ዘግቦ ነበር - ፖለቲኮ።
የቱዋሬግ ታጣቂዎች በአሁኑ ጥቃት በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን የዋግነር ወታደሮች ለዩክሬን አሳልፈው እንደሚሰጡ እና ይህም ከዩክሬይን ጋር ላላቸው አጋርነት ማሳያ ነው ሲሉ አስታውቀዋል። በምላሹም ዩክሬናውያን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ማሊ ለሚገኙት ቱዋሬጎች ለመላክ ዝግጁ መሆናቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው። በነዚህና በመሰል ተጨባጮች ሳቢያ የሩሲያ መንግስት መንግስታዊ ካልሆኑ ኃይሎች ከምዕራባውያን አጋሮቻቸው ጋር የፈጥሩባትን የጥቃት ትብብር በማገናዘብ በሳህል ቀጣና ዘመቻዋ የሚገጥማትን ውስብስብ ተግዳሮት አቅልላ መመልከት የለባትም እየተባለ ይገኛል - ሞስኮ ማሊ ውስጥ ለዋግነር የሰጠችውን ተልእኮ እንደማትተወው ሁሉ የዘመቻውን ክብደት የሚሸከም አቅም በመጨመር ሊሆን ይገባል በሚለው የምክረ ሐሳብ አፅንኦት።
Es
leman Abay የዓባይልጅ