ልጆችን ስለ ጾታዊ ጉዳዮች የማስተማር እና ያለማስተማር ጉዳይ ብዙዎችን ያከራከረ ጉዳይ ነው::
የተለያዩ ጥናቶች : ልጆች እድሜያቸውን እና የማገናዘብ ደረጃቸውን መሰረት ያደረገ ጾታዊ ትምህርት ቢሰጣቸው የተሻለ ነው ይላሉ:: ለዚህም እንደ ምክንያት የሚቀርበው: ይህን መረጃ ከወላጆቻቸው ካላገኙት ሌሎች የመረጃ ምንጮችን (ማለትም ከአቻዎቻቸው፣ ከበይነመረብ..) ማወቃቸው አይቀርም: ከነዚህ ምንጮች የሚገኙ መረጃዎች ደግሞ ላፈነገጡ ዝንባሌዎች ሊዳርጓቸው ይችላል የሚል ነው:: ስለ ጾታዊ ጉዳዮች አስቀድመው ማወቃቸው ራሳቸውን ከጥቃቶች እንዴት መከላከል እንደሚችሉ ያግዛቸዋል የሚል አመክንዮም የሚያቀርቡ አሉ::
**
የልጆች የአስተሳሰብ እና የማገናዘብ ችሎታ ልክ እንደ አካላዊ እድገት ሁሉ በእድሜ ሂደት የሚገነባ ነው::
🔹ከ 2-7 አመታቸው ድረስ ያለው Preoperational stage ይባላል:: በዚህ እድሜያቸው:: በአመክንዮ የማሰብ እና ውስብስብ ነገሮችን የመገንዘብ ችሎታው አይኖራቸውም፤ ሁኔታዎችን በራሳቸው አረዳድ ከመመዘን በዘለለ ሌሎች እንዴት ይቃኙታል ብለው አያገናዝቡም:: egocentric ናቸው::
ነገሮችን የሚማሩት በትዕምርት(Symbolic representation) ነው::
ስለዚህም በዚህ እድሜ ክልል ላይ ለሚገኙ ልጆች ነገሮችን በጨዋታ አስታኮ ማስተማር የተሻለ ነው::
በዚህም መሰረት:-
▪️ህጻናት ከእናቶች እንደሚወለዱ
▪️ወንዶች እና ሴቶች በጾታዊ አካሎቻቸው እንደሚለያዩ
▪️አካላዊ ስያሜዎችን በቀላል ቃል ማስረዳት
▪️የራስ አካል የግል እንደሆነና: ሌሎች በፍጹም ሊነኳቸው የማይገቡ አካሎች የትኞቹ እንደሆኑ
▪️ከቤተሰብ የሚደበቅ ሚስጥር መኖር እንደሌለበት ማስረዳት አስፈላጊ ነው::
🔹ከ7-11 አመታቸው ድረስ ያለው ጊዜ Concrete Operational stage ይባላል:: ምክንያታዊ የሚሆኑበት እና በአመክንዮ ማሰብ የሚጀምሩበት እድሜ ነው:: ምክንያታዊነታቸው ታድያ ለቁስ አካሎች ብቻ ነው:: ምናባዊ የሆኑ ጉዳዮችን በጥልቀጥ ለመመርመር ይቸገራሉ::
Inductive reasoning በብዛት ይጠቀማሉ:: ነገሮችን ከራስ ተሞክሮ በመነሳት ወደድምዳሜ ያመራሉ::
ማፈር እና ስለ ጾታዊ ጉዳዮች በመጠኑ ማሰብ የሚጀምሩበት እድሜ ነው::
በዚህ እድሜያቸው:-
▪️ስለ ወሲብ፣ እርግዝና እና ወሊድ
▪️ስለ ጉርምስና አካላዊ ለውጦች
▪️ስለ ወሲብ ጥቃት ምንነት/ በሚያውቁት ሰውም ሊደርስ እንደሚችል
▪️ጥቃት ቢደርስ የነሱ ጥፋት እንዳልሆነ እና መናገር እንዳለባቸው
▪️ ሰዎች ያለ አግባብ ሲደርሱባቸው እምቢ ማለት እንዳለባቸው፣ ከአሳቻ ስፍራ መራቅ እንዳለባቸው ማስረዳት ተገቢ ነው::
🔹ከ 11 አመታቸው በኋላ ያለው Formal Operational stage ይባላል:: Deductive reasoning ይጠቀማሉ:: ማለትም ከሰፊው አለም ተሞክሮ በመነሳት የራሳቸውን ባህርይ መገምገም ይችላሉ:: ምናባዊ ጉዳዮችን በጥልቀት መመርመር ይጀምራሉ::
ማንነት የሚገነባበት ወሳኝ እድሜ ነው:: ጠንካራ ማንነትን መገንባት ካልቻሉ ለአቻ ግፊት ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ::
የጉርምስና እድሜ እንደመሆኑ በአካል ላይ የሚታዩ ለውጦች አሉ:: ጾታዊ ፍላጎታቸውም ይጨምራል:: በተለያዩ ምክንያቶች(ተታለው፣ በስሜታዊነት፣ በአቻ ግፊት..) ለጾታዊ ጥቃቶች ሊጋለጡ ይችላሉ:: ታዲያ በዚህ እድሜያቸው እንቁላል መለቀቅ ስለሚጀምር እርግዝና ሊፈጠር ይችላል:: ስለዚህ ውይይታችን እነዚህን ጉዳዮች ያቀፈ መሆን ይኖርበታል::
ይህን ጽሁፍ ሳዘጋጅ Kaplan and Sadocks comprehensive textbook of Psychatry እና kelela guide ን በዋቢነት ተጠቅሜያለሁ::
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring