በትህነግ ውስጥ የተፈጠረው አለመግባባት ወደ መሰንጠቅ ደረጃ መድረሱ ይፋ ሆኖ ስጋቱ ባየለበት በአሁኑ ወቅት ” የህዝብ ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ላለልተወሰነ ጊዜ የድጋፍም ይሁን የተቋውሞ ሰልፍ ማድረግ ተከልክሏል ” ሲሉ የቀድሞ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ አስታወቁ። “ፖለቲካዊ አለመግባባት ወደ ማንኛውም የፀጥታ አደጋ እንዲሸጋገር አንፈቅድም” ብለዋል። ከሌሎቹ ታጣቂ ወገኖች የተሰማ ነገር የለም። አዲስ አበባ ያሉ የክልሉ ተቃዋሚ አመራሮች መቀዳደም ሊኖር እንደሚችል እያስታወቁ ነው።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት የቀድሞ ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ ጉዳዩን አስ፣ም እልክቶ በሰጡይት መግለጫ ” ፓለቲካዊ አለመግባባት ወደ ማንኛውም የፀጥታ አደጋ እንዲሸጋገር አንፈቅድም ” በሚል ሲያስጠነቅቁ ተሰምተዋል።
” የህዝብ ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ላለልተወሰነ ጊዜ የድጋፍም ይሁን የተቋውሞ ሰልፍ ማድረግ ተከልክሏል ” ያሉት ጀነራል ታደሰ ወረደ ” ፓለቲካዊ ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፈታት አለበት ” ብለዋል። እሳቸው ይህን ቢሉም በእነ ዶ/ር ደብረጽዮን የሚመራው አንደኛው ክንፍ ጉቤውን ለማካሄድ ከየአካባቢው ተወክለዋል ያላቸውን ክፍሎች የተወሰኑ ሰዎች ሲሸኙዋቸው የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ገጾች እያሰራጩ ነው።
ከዚህ ቀደም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፤ በቀላል እና ከባባድ ወንጀሎች ተሳትፈዋል ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የማዋል ኦፕሬሽን መጀመሩ አንስተው ” የህግ የበላይነት ለማስከበር የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ” ሲሉ ተደምጠዋል። ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረዳ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች መታገዳቸውን ባወሱበት መግለጫ የህግ የበላይነትን ለማስከበር የተጀመረው ርምጃ እንደሚቀጥል ማስታወቃቸው ለበርካቶች እንግዳ ሆኖባቸዋል።
የዘንድሮ የአሸንዳ በዓል አከባበርና የህወሓት ጉባኤ ከመካሄድ ጋር ተያይዞ የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ተገቢ እና ጥብቅ የፀጥታ ስራ ይሰራል ሲሉም ተናግረዋል።
“በህወሓት አመራሮች መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ እና እየከረረ መሄዱ በርካቶችን ያሳሰበ ጉዳይ ሆኗል። ሁኔታው የፀጥታ ስጋት ደቅኗል የሚሉ አልጠፉም” ሲሉ ሁኔታውን የሚከታተሉ እየወተወቱ ባለበት ወቅት ለጸጥታ ሲባል የተሰጠው ማሳሰቢያ በሁለት ጎራ ታጣቂዎችን መሳሪያ እንዳያማዝዝ የማድረግ አቅም ማን እንዳለው ግልጽ ባለመሆኑ ስጋት የሚቀንስ አልሆነም።
ከዚህ ይልቅ ሁሉም ሃይሎች ለትግራይ ምስኪን ህዝብ ሲሉ ቢቻል ራሳቸውን ከሃላፊነት በማውረድ ለተተኪ ሃይሎች እንዲያስረከቡ፣ ካልቻሉም ህዝብ ውሳኔውን እስኪሰጥ ድረስ ልዩነታቸውን በንግግር ቢፈቱ እንደሚሻል ጠቁመዋል።
ሌ/ጄነራል ታደሰ ግን ፓለቲካዊ ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፈታት እንዳለበት ፤ ማንኛውም ልዩነት ወደ ፀጥታ አደጋ እንዲሸጋገር የጸጥታ አካሉ እንደማይፈቅድ ማስጠንቀቃቸው ባይከፋም ውጤቱን የሚጠራጠሩ የፌደራሉ መንግስት አዲስ አበባ ጠርቶ ጉዳዩን አሸማግሎ ለመቋጨት ቢሞክር እንደሚሻልም የጠቆሙ አሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ምርጫ ቦርድ ትህነግ ኦኢኦያካሂድ ያሰበውን ጉባኤ እንደማይቀበል ገልጾ መግለጫ አሰራጭቷል።
” ጠቅላላ ጉባኤው ከቦርዱ ፍቃድ ውጭ ከተካሄደ ቦርዱ ለዚህ ጉባኤም ሆነ በጉባኤዎቹ ላይ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች በሙሉ ዕውቅና አይሰጥም “- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከህወሓት ጉባኤ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ለድርጅቱ ደብዳቤ ጽፏል።
ቦርዱ ፥ ነሐሴ 3/2016 ዓ/ም ለፓርቲው በጻፈው ደብዳቤ ፖርቲው በልዩ ሁኔታ መመዝገቡን እና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትም እንደሰጠው አስታውሷል።
ፓርቲው የቦርዱ ደብዳቤ እና የምስክር ወረቀት ከደረሰው ቀን ጀምሮ የሚተዳደረው የኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011ና ይህን አዋጅ ባሻሻለው አዋጅ ቁጥር 1332/2016 እንዲሁም እነዚህን አዋጆች መሰረት ተደርገው በወጡ መመሪያዎችና የቦርዱ ውሳኔዎች መሰረት እንደሆነ አስገንዝቧል።
ቦርዱ ውሳኔ የሰጠባቸውና በደብዳቤ ከገለፃቸው በፓርቲው መተግበር ካለባቸው ተግባራት መካከል ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ከማድረጉ ከ21 ቀን በፊት ለቦርዱ ማሳወቅና ፖርቲው በሚያደርገው ጠቅላላ ጉባኤ የቦርዱ ታዛቢዎች መገኘት በዋናነት የተገለፁ ግዴታዎች እንደሆኑ አመልክቷል።
ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት ፖርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ሊያደርግ መሆኑን ቦርዱ በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን እየተዘገበ መሆኑ መመልከቱን ገልጿል። በዚህም ቦርዱ ” ለአንድ ጠቅላላ ጉባኤ መደረግ አስፈላጊ የሆኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እንዲያውቅ ባልተደረገበት፣ ባልተከታተለበትና ባላረጋገጠበት እንዲሁም የቦርዱ ታዛቢዎች ባልተገኙበት ተጠራ የተባለው ጠቅላላ ጉባኤ ሊካሄድ አይችልም ” ሲል አሳውቋል።
ጠቅላላ ጉባኤው ከቦርዱ ፍቃድ ውጭ ከተካሄደ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዚህ ጉባኤም ሆነ በጉባኤዎቹ ላይ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች በሙሉ ዕውቅና የማይሰጥ መሆኑን ለህወሓት በጻፈው ደብዳቤ ላይ ገልጿል።