አንድ በድለላ ስራ ላይ የተሰማራ ግለሰብ የክብርት ከንቲባ ታናሽ ወንድም እና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ነኝ በማለት ከአራት ግለሰቦች ላይ ከ900 ሺ ብር በላይ ያታለለን ተጠርጣሪ ከግብረ አበሮቹ ጋር ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ተጠርጣሪው ግለሰብ ታደለ ጌታነህ ይባላል፡፡ ሆኖም ስሙ ታደለ አቤቤ እንደሚባል ሐሰተኛ መታወቂያ አሰርቶና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የክብርት አዳነች አቤቤ ታናሽ ወንድምና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ነኝ በማለት ሰዎችን በሀሰት ጉዳያችሁን እጨርስላችኋለው ብሎ ከተዋወቀ በኋላ ከአራት ግለሰቦች ላይ 970 ሺብር በማታለሉ ተጠርጣሪውን ጨምሮ ሁለት ግብረ አበሮቹን ይዞ ምርመራው መቀጠሉን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የግል ተበዳይ አቶ ልዑል ኪሮስን የክብርት ከንቲባ ወንድም እንደሆነና መንግስት ለቤት መስሪያ 140 ካሬ ሜትር ቦታ ስለሰጠው ለሊዝ የሚክፍለው 800 ሺ ብር እንዲያበድሩት ይጠይቃቸዋል፡፡
የግል ተበዳይም የተባሉትን በማመን 600 ሺ ብሩን አስናቀ ጌታነህ ቀሪውን 200 ሺብር ደግሞ በላይ ጣሰው በተባሉት ግብራበሮቹ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ በነገራቸው መሰረት ብሩን ገቢ ያደርጋሉ፡፡ በተመሳሳይ የማታለያ ዘዴ አቶ ፈለቀ ሃይሉ የተባሉትን ግለሰብ በመቅረብ ቤት ለመገንባት 4ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው እና 500ሺ ብር ብድር እንዲሰጡት ጠይቆ 105 ሺ ብር መቀበሉን በማስረጃ ማረጋገጡን ፖሊስ ገልፆል፡፡
በተመሳሳይ አዳማ ከተማ የተዋወቀቃቸውን አቶ ለገሰ ሲሳይን ደግሞ የከንቲባዋ ወንድም ስለሆነኩ በቀላሉ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ መሬት አሰጥሃለሁኝ ብሎ 10 ሺ ብር የወሰደ ሲሆን እንዲሁም ለቤተሰባቸው ፓስፖርት ለማውጣት ኢሚግሬሽን ያገኛቸውን አቶ ፈለቀ ዝናቡን የክብርት ከንቲባ ወንድም ነኝ በተጨማሪም እኔም ዳኛ ነኝ ምናልባት ያለ አግባብ የሚያጉላሉህ ካሉ አሳውቀኝ ሰብስቤ አሳስራቸዋለሁኝ የሚል የማታለያ ቃል በመናገር ጉዳያቸው በፍጥነት እንዲያልቅል 80ሺ ብር እንዲሰጠው ጠይቆ 10 ሺ ብር አታሎ መውሰዱን አዲስ አበባ ፖሊስ ባሰባሰበው ማስረጃ መረጋገጡን አስታውቋል፡፡
ግለሰቡ ከክብር ከንቲባ ጋር ምንም አይነት ዝምድና የሌለውና በድለላ ስራ የተሰማራ መሆኑን ፖሊስ አስታውቆ ግለሰቡን ጨምሮ በዚህ ወንጀል ተሳትፎ ያላቸው ሦስት ተጠርጣዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን መቀጠሉን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን እናውቃለን ዘመድ ነን በማለት የማታለል ወንጀል የሚፈፅሙ አታላዮች እንዳሉና የመንግስት የስራ ሐላፊዎች ዘመድ ቢሆኑም እንኳን ከህግና ከአሰራር ስርዓት ውጭ አለአግባብ የሚሰጥ አገልግሎት አለመኖሩን እንዲሁም የመንግስት አገልግሎት ተገቢ ባልሆነ መንገድ ወይም በአቋራጭ ለማግኘት የሚደረጉ ማንኛውም ህገወጥ ተግባር ላልተገባ ወጪ የሚዳርግ መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ድርጊቱን እንዲከላከል እና በዚህ ህገ ወጥ ድርጊት የሚሳተፉ ግለሰቦችን ህብረተሰቡ የማጋለጥ ሐላፊነት እንዳለበት አዲስ አበባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring