” ህወሓት 50 ዓመታታት ያስመዘገበ እንደ አዲስ መመዝገብ የሌለበት አንጋፋ የፓለቲካ ድርጅት ነው ” – ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)
የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ዛሬ ባለፈው እሁድ መግለጫ ሲሰጡ ” ትህነግ 50 ዓመታታት ያስመዘገበ እንደ አዲስ መመዝገብ የሌለበት አንጋፋ የፓለቲካ ድርጅት ነው ” ብለዋል።
ሊቀመንበሩ ፤ ” የህወሓት ህጋዊነት የመመለስ ጉዳይ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ጎን ለጎን እንጂ አሁን የተጀመረ አይደለም ” ያሉ ሲሆን ” የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሁለቱ ተፈራራሚዎች እርስ በራሳቸው እውቅና እንደሚሰጣጡ ይደነግጋል ” ብለዋል።
የህወሓት ህጋዊነትን ለመመለስ የተካሄደ በርካታ ውይይቶችን ተከትሎ ድርጅቱና ሌሎች የሚያካትት አዲስ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ የሚመለከት የተሻሻለ አዋጅ እስከ ማውጣት መደረሱ አብራርተዋል።
” የተሻሻለው በአመፅ ድርጊት የተሳተፉ የፓለቲካ ፓርቲዎች መልሶ ስለ መመዝገብ የሚመለከት አዋጅ ህወሓት ወደ ቀደመው እውቅናዋ ሊመልስ አይችልም ” ያሉት ደብረፅዮን (ዶ/ር) ፥ ” ስለሆነም ህወሓት ወደ ነባር እውቅናው ይመለሳል እንጂ እንደ አዲስ አይመዘገብም ” ሲሉ ተደምጠዋል።
” ህወሓት እንደ አዲስ መመዝገብ ማለት የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ማፍረስ ማለት ነው ” በማለትም ተናግረዋል።
” የአፍሪካ ህብረት ታዛቢዎች በተገኙበት ህወሓት ወደ ነባሩ እውቅና ለመመለስ ነው ስምምነት የተደረሰው ” ሲሉ ገልፀዋል።
ሊቀመንበሩ ህወሓት ጉባኤ ስለሚያካሂድበት ጊዜ ቁርጥ ያለ ቀንና ቦታ በመግለጫቸው አልጠቆሙም።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ፥ ከቀናት በፊት ለህወሓት ” በልዩ ሁኔታ ” ሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ መስጠቱ ይታወሳል።
ቦርዱ ነሀሴ 3 ባወጣው መግለጫ ድርጅቱ በልዩ ሁኔታ መመዝገቡን የሚገልጸው ድብደቤ ከደረሰው ቀን አንስቶ ባሉት 6 ወራት የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ ያዛል።
ህወሓት ግን ነሀሴ 4/2016 ዓ.ም ” የተሰጠኝ የምዝገባ ውሳኔ ከተካሄዱት የሁለትዮሽ ወይይቶችና መግባባት ወጪ ነው ስለሆነ ወደ ነባሩ እውቅናዬ የማይመልስ ውሳኔ አልቀበልም ” ብሎ መግለጫ አውጥቷል።
ዛሬ ደግሞ የድርጅቱ ሊቀመነንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፤ ” ህወሓት 50 ዓመታታት ያስመዘገበ እንደ አዲስ መመዝገብ የሌለበት አንጋፋ የፓለቲካ ድርጅት ነው፤ ህጋዊ ሰውነታችን ይመለሳል እንጂ እንደ አዲስ አንመዘገብብም ” ብለዋል። ሲል ቲክቫህ ከንግግራቸው ቀንጭቦ የሰራው ዜና ያስረዳል።