የውጭ ምንዛሬ የሚገዙት አካላት 56 ብር ለምንዛሬው ይከፍሉና 50 ብር ጉቦ ይሰጣሉ። ታክስ ሲጨመርበት ምንዛሬው በህጋዊ መንገድ ተገዛ የተባለበት ዋጋ ከጥቁር ገበያው ይበልጣል። አሰራሩን በደንብ እንደሚያውቁት የሚናገሩት አቶ ኤርሚያስ በአገሪቱ የዋጋ ንረት ላይ ዋና ጥላ የሆነውን ይህን ትብትብ አዲሱ ሪፎርም እንዳስቀረው ይገልጻሉ። በደላላና በጥቁር ገበያተኞች የሚመራው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አሁን ላይ ነጻ ወጥቷል። መንግስትም ያውላችሁ ብሎ ወጥቷል። አሁን ላይ ያለው ትርምስ ካለማወቅ የሚመነጭ ስለሆ ነ ባጭር ጊዜ የጥቁር ገበያው እንደሚወርድ ተንብየዋል።
“ያስቃል” ብለው ነው ምክራቸውን የለገሱት። ያሳቃቸው የአረዳዱ ችግር ተራ የመርካቶ ነጋዴንና ባንኮችን አንድ አይነት ስሌት እንዲያሰሉ ማስቻሉ ነው። የዶላር የጥቁር ገበያ መውረድ ሳይታበል የተፈታ ሃቅ መሆኑን አመልክተው ” ይልቁኑ በጥቁር ገበያ ዶላር በ120 ብር ሂሳብ ገዝታችሁ ያከማቻችሁ አውጡና ሳይመሽ ሽጡ” ሲሉ አቶ ኤርሚያ አመልጋ መክረዋል።
እንግሊዝኛ፣ አረብኛ፣ ስዋሊህና አማርኛን አቀላጥፈው የሚናገሩት አቶ ኤርሚያስ በአሜሪካን አገር ኢኮኖሚ ያጠኑት አቶ ኤርሚያስ በዘርፉ ብቁ ባለሙያ ናቸው። ሰሞኑን ብሄራዊ ባንክ ያፋ ያደረገውን ሪፎርም አስመልክተው ” መርዶ አይደልም። እርምጃው ታሞ ኮማ ውስጥ ላለው ኢኮኖሚ መድሃኒት እንጂ” ሲሉ ሟርት የሚያሰሙትን ይነቅፋሉ። ይህን የሰሙ የመንግስት ሚዲያዎች አስለቺ የርስ በርስ ወሪያቸውን አቁመው እንዲህ ያሉትን ባለሙያዎች በማቅርበ ከሚነቅፉ ወገኖች ጋር ለምን አያከራክሯቸውም ሲሉ እየተየቁ ነው።
የኢትዮጵያን የአሁኑን የኢኮኖሚ አቅም ከካንሰር ህመም ጋር በማመሳሰል አስተያየታቸውን ለሸገር ሬዴዮ የሰጡት አቶ ኤርሚያስ ” ካንሰር መድሃኒቱ መርዝ ነው። የሚገለው ካንሰር የጎዳወንም ያልጎዳውንም ሴል ነው። ጤናማውን ሴል ይገላል በሚል መድሃኒቱን አልወስድም ማለት አይቻልም። ምክንያቱም አማርጩ ሞት ብቻ ነው” ብለዋል።
አሁን መንግስት የወሰደው የፖሊሲ ለውጥ ላለፉት ሃያ ዓመታት ደጋግመው ሲያነሱት የነበረው ጉዳይ እንደሆነ ያመለከቱት አቶ ኤርሚያስ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በጥቁር ገበያና መርካቶ ነጋዴዎች ሲነዳ እንደነበር፣ አገሪቱ ጥቂቶችንና ባንኮችን ብቻ ተጠቃሚ ያደረገ ቁጥጥር ላይ የተቸነከረ አሰራር ትከተል ስለነበር የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለሞት መዳረጉን በገሃድ አስታውቀዋል።
የዝቅተኛ ኑሮ ያላቸውና አነስተኛ ደሞዝ ተከፋዮች ጉዳት እንደሚያጋጥማቸው፣ ለዚህም መንግስት እንዳለው ድጎማ እንደሚያስፈልግ ያወሱት አቶ ኤርሚያስ፣ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ከሞት ለማዳን ሃኪሞች የሚወስዱትን እርምጃ መውሰድ ግድ መሆኑን ገልጸዋል። ራሱን የሳተና ወደ ሞት ያመራ ሰው ልቡ እንዲሰራ የኤለኢክትሪክ ንዝረት እንደሚሰጠው ሁሉ የኢትዮጵያም ኢኮኖሚ የንዝረት ህክምና ያስፈልገዋል ብለዋል። እሱም አሁን ይፋ የሆነው ፖሊሲ ነው።
ጠያቂያቸውን “በአመክንዮና በቁጥር እንነጋገር” እያሉ በአነስተኛ ምስሌዎች አስተያየታቸውን የሰጡት ታዋቂው የቢዝነስ ሰው፣ ቀደም ሲል ባንክ ዶላርን በ58 ብር ሂሳብ ከባንክ የሚገዙ ነጋዴዎች 100 ሺ ዶላር ቢወስዱ፣ የሚያስገቡት የ500 ሺህ ዶላር እንደሆነ በምሳሌ አስረድተው፣ ከባንክ የሚወሰደው ምንዛሬ የይስሙላ ማሳያና ህጋዊ የመምስል አካሄድ እንደሆነ ገልጸዋል። አክለውም ገበያው የሚሰላው በጥቁር ገበያ እንደሆነ፣ ገዢውችም የሚገዙት በዚያው ስሌት በመሆኑ ለዋጋ ንረት መጋለጣቸውን አስታውቀዋል።
ለስራውና ለአሰራሩ ቅርብ መሆናቸውን፣ መረጃም እንዳላቸው የሚገልጹት አቶ ኤርሚያስ ከባንክ በ58 ብር ሂሳብ የሚገዛው ዶላር ከታክስና ከተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎች ጋር ሲሰላ ከቱር ገበያው ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ ገልጸዋል። ሂሳቡን አስልተው ባንኮች የሚሸጡት ጥቁር ገበያ ካለውም ሊበልጥ እንደሚችል በማመልከት መንግስት ይፋ ያደረገው አዲሱ ፖሊሲ ይህን ያስቀራል።
ምንዛሬውን የሚያመታጥነው ሃብት / ዶላር ከየት ይመጣል
በወራት ውስጥ የጥቁር ገበያውና ይህጋዊ የምንዛሬ መጠን ተቀራራቢ እንደሚሆን፣ የመጫወቺያ መድረኩ አስከ 90 ብር ሊሆን እንደሚችል ማሳያዎችን አንስተው አስረድተዋል። ” ዶላሩ ከየት ይመጣል” ለሚለው ጥያቄ የዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ድርጅትና በስሩ ያሉ ተቋማት ከሚለቁት ይፋ የሆነ የምንዛሬ መተን ውጪ
- መንግስት ባንኮች ከሬሚታንስ ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሬ ቀደም ሲል ይወስድ የነበረውን ሃምሳ ከመቶ አሁን “ትቻለሁ። ተጠቀሙበት ብሏል” ያሉት አቶ ኤርሚያስ ይህ ብር 3 ቢሊዮን የሚልቅ ሲሆን በቀን 83 ሚሊዮን አካባቢ ነው። ይህ ገንዘብ ፖሊሲው ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ባንኮች እጅ ነው።
- ኤክስፖርት የሚያደርጉ ነጋዴዎች ከሚያገኙት ምንዛሬ በተመሳሳይ መንግስት ይወስድ የነበረውን 50 ከመቶ አቁሟል። በዚህም ከፍተኛ መተን ያለው ምንዛሬ ባንኮች እጅ ይቀራል።
- መንግስት ፍራንኮ ቫሉታም በመፍቀዱ 3 ቢልዮን የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ ወደ ባንኮች ቋት ይገባል። ሰዎች በራሳቸው ገንዘብ የፈለጉትን ዕቃ ከውጭ ማስገባት ስለሚችሉ ይህ ትራንዝ አክሺን በባንኮች ስር የሚዘዋወር በመሆኑ ለባንኮች ገቢ ነው።
- የግል የውጭ ምንዛሬ የሂሳብ ደብተር ማውጣት በመፈቀዱ ሰዎች ዶላራቸውን በራሳቸው አካውንት ማስቀመጥ መቻላቸው፣ ሲፈልጉም ዶላራቸውን ማውታት ስለሚችሉ የጥቁር ገበያውን እንደሚያመናምነው የጠቆሙት አቶ ኤርሚያስ ከ3 ቢሊዮን በላይ የውጭ ገንዘብ በዚህ መልኩ ባንኮች እጅ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ሌሎችን ሳያካትት በእነዚህና በሌሎች ፖሊሲው ክፍት ባደረጋቸው አሰራሮች የተነሳ ባንኮች በትንሹ ከዘጠኝ ቢሊዮን በላይ የውጭ ምንዛሬ ያገኛሉ። ይህን ምንዛሬ በመሸጥ ይተርፋሉ።
አቶ ኤርሚያስ እንደሚሉት ባንኮች ስላልገባቸው ልክ የመርካቶ ነጋዴ እንደሚያደርጉት አሁን ላይ ምንዛሬውን ይዘዋል። ኤልሲም አንከፍትም የሚሉም አሉ። እየዋለ ሲያድር ግን የአመለካካት ለውጥ መምጣቱ አይቀሬ ነው።
ዓለም ዓቀፉ የተገንዘብ ተቋም የለቀቀውና እየደር የሚለቀው ሃብት መንግስት ሲያሰራጨው የጥቁር ገበያው ዋጋ ከባንክ ምንዛሬ ጋር ብዙም እንደማይራራቅ አቶ ኤርሚያስ ገልጸዋል። በንዝረት ላይ ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዓለም ቀውስ ሳቢያ ማደበሪያ፣ ነዳጅ፣ መድሃኒት የመሳሰሉት ዋና ግብአቶች በመወደዳቸው ሳቢያ ይባስ መጨናነቁን ገልጸዋል። ትክክለኛው መድሃኒት አሁን የተጀመረው የፖሊሲ ለውጥ የተሻለ ለውጥ እንደሚያመጣ እምነታቸውን ገልጸዋል። ቃለ ምልልሳቸውን ያድምጡ