በአትሌት ሰለሞን ባረጋ፣ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እና አትሌት በሪሁ አረጋዊ በተሳተፉበት ውድድር ኡጋንዳዊው ቺፕቴጊ በአጨራረስ ብልጠት የወርቅ ሜዳሊያውን በኦሊምፒክ ሪኮርድ አጅቦ ተረክቧል። በሪሁን አረጋዊ መጨረሻ ላይ የአነሳስ ስህተት ቢፈጽምም በሰኮንዶች ተቀድሞ ሁለተኛ በመሆን ለአገሩ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል። የተቀሩት ሆኗል። ስድስተኛና ሰባተኛ ሆነው ጨርሰዋል። ሰዓታቸውን ከሰንጠረዡ ይመልከቱ
የዓለም ባለክብረወሰኑ ዮሹዋ ቺፕቴጊ የኦሊምፒክን የአስር ሺህ ሜርት ክብር ደርቧል። በድንቅ ሩጫው ክብሩን የወሰደው ይህ አትሌት በ2008 ቀነኒሳ ይዞት የነበረውን ሪኮርድ 26:43.14 በመግባት በ18 ሰኮንዶች አሻሽሏል።

ለወትሮው በተመሳሳይ አቋም ላይ የሚገኙ አትሌቶችን በማሰለፍ የምትታወቀው ኢትዮጵያ እየተቀባበሉ ውድድሩን ለመቆጣጠር ጥረት ሲያደርጉ ከመታየታቸው ውጪ መስመር ከመተበቅና አጨራረስ ላይ ከየት እንደሚነሱ ለይቶ ያለማወቅ ችግር ታይቶባቸዋል። አጨራረስን ለማሳመር አስቀድመው መነገድ ባለማመቻቸታቸው ሲደነቃቀፉ ታይተዋል።
አሸናፊው ቺፕቴጊ በመሮጫው መም ላይ ራሱን አመቻችቶ በግምት ከ2500 ሜትር አካባቢ ሲነሳ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ አቅሙን ስለቸረሰ ፍጥነት ጨምሮ ሊከተል እንዳልታየ ለማየት ተችሏል።
ከተመረጠው የውድድር ታክቲክ እንደታየው ሰለሞን ባረጋ ነበር አጨራረስ ላይ ቅድሚያ የተሰጠው። ቺፕቴጊ ሲነሳ መከተል ያልቻለውና አምስት ዙር ሲቀር ሩጫውን ሲያከር የነበረው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እየዞረ ሰለሞን ባረጋን ሲመለከት የነበረውም ለዚሁ ነው። ስልቱ በተወዳዳሪዎቹ አቅም መሰረት የተመረጠ ቢሆንም፣ አትሌቶቻችን አጨራረስ ላይ አልቻሉም።
ሁለተኛ የወጣው በሪሁ አረጋዊ ወታ ገባ ማለቱን ትቶ በተመሳሳይ ቴንፖ ዝም ብሎ አንደናውን አትሌት እየተከተለ ቢሮጥ ኖሮ ወርቅ ማግኘት የሚያስችል ጉልበት እንደነበረው መጨረሻ ላይ ሰባት አትሌቶችን በሰባ አምስት ሜትር ርቀት መቅደሙ ምስክር ነው። አስቀድሞ የተመቻቸ ቦታ አለመያዙ ዋጋ አስከፍሎታል።
ውድድሩን የሜከታተሉት የቴክኒክ ሰዎችና አሰልጣኞቹ ውድድሩ ሊጠናቀቅ ሲቃረብ በአንድ መስመር መታጀላቸውን ሲያዩ፣ ሰለሞን ባረጋ መድከሙን ሲያስተውሉ ለምን ማስተካከያ ምክር እንዳልለገሱ ግልጽ አይደለም።
ውጤቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ድንቅ ቢሆንም፣ በአስር ሺህ ሜትር እነ ሃይሌ፣ ቀነኒሳ፣ ስለሺ በቅርብ ሲንሳፈፉ ባየንበት ዓይናችን ተተኪ ዓለማየታችን “አሰልጣኞቻችን የሚችሉት በተፈጥሮ የታደሉትን አትሌቶች ብቻ ነው እንዴ? ” የሚል ጥያቄ ያስነሳል።
የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ ሦስቱም አትሌቶች ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል
በ2024 ፓሪስ ኦሊምፒክ በ5ሺ ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ፣ እና እጅጋየሁ ታዬና መዲና ኢሳ ለፍፃሜ ውድድር አልፈዋል።
የርቀቱ የአለምና የኦሊምፒክ ቻምፒዮኖች፣ የክብረወሰን ባለቤቶች በተሳተፉበት በመጀመሪያው ዙር የማጣሪያ ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ እና እጅጋየሁ ታዬ 5ኛ እና 6ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።
በሁለተኛ ምድብ የተሳተፈችው ወጣቷ አትሌት መዲና ኢሳ 2ኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ በፍፃሜ የምትፋለም ሦስተኛዋ ኢትዮጵያዊት ሆናለች።
የ5 ሺህ ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር የፊታችን ሰኞ ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም ምሽት 4:10 ሰዓት ይካሄዳል።
በ800 ሜትር ሴቶች ማጣርያ አትሌት ወርቅነሽ መሰለ እና አትሌት ፅጌ ዱጉማ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፈዋል።
አትሌት ሀብታም አለሙ በማጣሪያ ውድድሩ 2:02.19 በሆነ ሰዓት ሰባተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችላለች። በቀጣይ “repêchage ” በተባለው የአለም አትሌቲክስ አዲስ ህግ ሌላ ውድድር የምታደርግ ይሆናል።