መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገው የቦይንግ የአፍሪካ ጽኅፈት ቤት ቢሮ በመጪው ጥቅምት ሥራ እንደሚጀምር የኩባንያው የአፍሪካ ጽህፈት ቤት ዋና ኃላፊ ሄኖክ ተፈራ ገለጹ። አቶ ሄኖክ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ሲሰሩ የውጭ አገራት ሚዲያዎች ኢትዮጵያ ላይ ከፍተውት የነበረውን ዘመቻ አደባባይ በመጣት ሲያሳጡና በጽናት እውነትን ይዘው በማሳፈር የሚታወቁ ዲፕሎማት ነበሩ።
የአሜሪካው ግዙፍ የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ በቅርቡ የአፍሪካ ዋና ጽህፈት ቤቱን በአዲስ አበባ ለመክፈት በሂደት ላይ እንደነበር መግለጹ ይታወሳል።
ይህንንም ተከትሎ በመጪው ጥቅምት የኩባንያው ቢሮ ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር ነው የቦይንግ የአፍሪካ ጽኅፈት ቤት ስራውን እንደሚጀመር ዋና ኃላፊ ሄኖክ ተፈራ የተናገሩት ለኢዜአ ነው።
ቦይንግ የአፍሪካ ዋና ጽህፈት ቤቱን በአዲስ አበባ የከፈተው ኢትዮጵያ በአቬይሽን ዘርፍ እያስመዘገበች ያለውን ስኬታማ ሥራ ከግምት በማስገባትና አገሪቱ የአፍሪካ የአቪዬሽን ማዕከል እየሆነች መምጣቷን ተከትሎ መሆኑንም ተናግረዋል።
የቦይንግ ኩባንያ የአፍሪካ ጽህፈት ቤት ዋና ቢሮውን በአዲስ አበባ መከፈቱ የቦይንግ ኩባንያ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በተለያዩ ዘርፎች ያሉትን ትብብሮች ይበልጥ ለማጠናከርና ለማስፋት እንደሚያስችልም አስረድተዋል።
ያም ብቻ ሳይሆን የቢሮው መከፈት ኢትዮጵያ የአፍሪካ የአቪዬሽን ማዕከልነቷን አጠናክራ ለማስቀጠል ተጨማሪ እድል እንደሚፈጥርላትም ነው ያብራሩት።
በቀጣይ ቦይንግ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በተመተባበር በተለይም የአውሮፕላን ክፍሎች/እቃዎች በጋራ ለማምረት የሚያስችል ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችሉ ሥራዎች ላይ ትኩረት የሚደረግ መሆኑን ጠቁመዋል።