ኢትዮጵያ ላይ በተለያዩ ወቅቶች ወነጀል ተሰርቷል። ቀደም ባሉ ዓመታት እንደ ዛሬው የማህበራዊ ሚዲያ መድረኩና ሚዲያው ዝግ ስለነበሩ ታፍኖ እንጂ እጅግ ዘገናኝ ወንጀሎችና ክህደቶች ተድፈጽመዋል። ዛሬ የፓሪስ ኦሊምፒክ ውጤትን ተንተርሶ የተነሳው ተቃውሞና፣ ውድድሩ ከመጀመሩ እፊት በቅብብል የተጀመረው የተጠና አድማ አሁን ባለው ጩኸት መፍትሄ አያገኝም። አትሌቲክሱን ለመታደግ ከተፈለገ ግን የተወሰኑ ነጥቦችን በድፍረት፣ ስምና ዝናን ሳንፈራ፣ አፈራርቶ መነጋገር ግድ ነው።
መጠቆሚያ
- ውጤት ተበላሽቷል። የማን ጥፋት ነው? ማን ነው ተጠያቂው? ኦሊምፒክ ኮሚቴ ወይስ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን?
- ውድድሮቹ ሁሉ የቡድን ስራ አይታይባቸውም። ያልተመጣጠነ አቅም ያላቸው ተወዳዳሪዎች ነበሩ የቀረቡት። የማን ጥፋት ነው?
- የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ከሪዮ ኦሊምፒክ ጀምሮ ብሄራዊ የኤቨንት አሰልታኝ የለውም። የብሄራዊ ቡድን የኢቨንት አስልጣኞች የመመደብ ሃላፊነት የማን ነው? ካልተመደበ ለምን? የብሄራዊ ቡድን አስለጣኝ አያስፈልግም የሚለው አስተምህሮት የእነማን ነበር? አትሌቶች ነሳ ይለቀቁ በሚል መግለጫና ትንታኔ ሲሰጡና ስማቸውን ተጠቅመው ሲፈላሰፉ የነበሩትና “አትሌቲክስ እንደ እግር ኩስ የቡድን ስራ አይደለም። በግል ብቃት ላይ የተነሰረተ ስፖርት ነው” በሚል በብሄራዊ ቡድን ተይዞ መስለጠንን የእስር ያህል ሲያወግዙ የነበሩት ዛሬ ለምን ወቅ2አሽ ሆኑ? ሚዲያውስ ለምን ቆም ብሎ አይጠይቅም?
- ኦሊምፒክ ኮሚቴና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አንድ አይነት አደረጃጀትና ሃላፊነት አላቸው? ማን በምን ጥፋት ነው ሊጠየቅ የሚችለው?
- ያለ ስራቸው ወደ ፓሪስ የሄዱ ሰዎች ጉዳይ ተጣርቶ የሚሆነው እስኪሆን ልለፈውና ለመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ፓሪስ ቢሄድ አትሌቶቹ እንዳይሮጡ፣ ሮጠው እንዳያሸንፉ፣ አሸንፈው እንዳይጨፍሩ እንዴት እንቅፋት ይሆናል?
ትችትና ወቀሳን በተመለከተ
- ከማራቶንና ከስምንት መቶ ሜትር ውድድር ውጪ የታየውን (የሶስት ሺህ መሰናክልን አይጨምርም) ባለክንፉ መልዓክ ይዟቸው ፓሪስ ቢሄድ የማሸነፍ አቅምና ትጋት ያሳዩ ነበር? እንዲህ ያለ የተዘባረቀ ቡድን ያቀረበው ማን ነው? ህዝብ ነው? የክልል ፕሬዚዳንቶች ናቸው? ማን ነው? ወቀሳው ይህን ሳይለይ ነው የሚዘነበው። የሚመለከታቸው ወነበሩ ላይ ያሉ አስለቃሽ ሆነው ፍትህ ሲተይቁም እየታየ ነው። ይህ ምን ማለት ነው?
1 – ለምሳሌ ገዛከኝ አበራ የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንትና የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነው። አራት ዓመት ምስ ሲሰራ ቆይቶ ነው ዛሬ ፍትህ ጠያቂ፣ አልቅሶ አስለቃሽ ሆኖ ብቅ ያለው? ቡድኑ ወደ ፓሪስ ሊሄድ ሲል ” የቃም ችግር አለ። ዋጋ የለውም” የሚለው ምን አስቦ ነው? አስቀድሞ ምን ስለታየው? ደግሞስ ግምገማው ትክክል ከሆነ አስቀድሞ ራሱን ከተተያቂነት ለምን ነጻ ለማድረግ አልወሰነም? ሚዲያውስ ለምን ይህ አይተይቅም?
2- ሃይሌ የፌዴሬሽኑ መሪ ነበር። ድንገት ለቀቀ። ለምን ለምን ለቀቀ? የለቀቀበትን ዝርዝር ምክንያት አስረግጦ የጠየቀ ሚዲያ አለ? ሲፈልግ ጥሎ እየሄደ ሲፈልግ በአናት እየመጣ ውድድር ሊጀመር ሲል ቡድኑን የሚረብሽ አስተያየት ለመስጠት ለምን ፈለገ? የመረጠው ጊዜ በቡድኑ የስነ ልቦና ግንባታ ላይ ጫና እንደሚያሳድር ጠፍቶት ይሁን? የኦሊምፒክ ኮሚቴ ውስጥ የመመረጥና ያለመመረጥ ጉዳይ ከሆነ ይህንኑ ፍላጎቱንና መብቱን እንዳለው በህግ አግባብ ለምን አይስፈጽምም?
ያለ እውቀት ዘለፋ ነገም ውርደትን ይጋብዛል
ሁለት አካላት በገሃድ አሉ። አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ኦሊምፒክ። በአካል ውድድር ስፍራ ለተወሰኑ ቀናት በመገኘት እንደታዘብኩት፣ ከአንዳንዶች ጋርም እንደተነጋገርኩት ከሆነ ውድድሩን አስመልክቶ የተነሱና በቅብብል የተሰራጩ ወቀሳዎች አድራሻቸው የተምታታ ነው። የሚወቅሰውን አካል በምክንያት ለይቶ አያሳይም። አሸብር በፌዴሬሽን ምትክ ይወቀጣል። ደራቱ በኦሊምፒክ ምትክ ትወቀሳለች። አቅም አልባ ቡድን ያዘጋጁ፣ የቀድሞውን ጥብቅ ቁጥጥርና ወጥ አሰራር ያፈረሱ ወገኖች ያለ አንዳች ስጋት ሁለቱንም ደብዳቢና አሸማቃቂ ሆነዋል። ለውጥ ጠያቂም ናቸው። ይህ ስልጣን ፍለጋ እንጂ ለአገር መቆርቆር እንዴት ሊባል ይችላል?
ስጠቀልለው
አሸብርን በተመለከተ ከስፖርቱ አካባቢ የሚርቅበትን መንገድ በጥበብ ማፈላለግ እንደሚበጅ ጠቁሜ አልፈዋለሁ። ከዚህ ውጪ መንግስት ጣልቅ እንዲገባ የሚጋብዙ ንግግሮችና ዘገባዎች አሸብርን ይጠቅማሉ እንጂ አይጎዱም። ህጋዊ መሸሸጊያ ነው የሚሆንለት። አሸብርን ለመወንጀል ከጉዳዩ ጋር የሚያያዝ መረጃ ሳይጠፋ እንደ ብረሃኑ አዴሎ አይነት የግል እስር ቤት የነበራቸውን ሰዎች በመጥቀስ ግፍ በተሰራባቸው ወገኖች ደምና ዕምባ መሳለቅ ግንንልክ ነው ብዬ አላስብም።
የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈሚን መንግስት አፍንጫውን ይዞ
1- ብሄራዊ ቡድኑ ለምን እንደፈረሰ ወይም የርቀቱ አሰልጣኝ ለምን እንዲቀር እንደተደረገና ሁሉም በግል አሰለጣኞቻቸው እንዲወከሉ የተደረገበት አሰራር በማን እንደጸደቀ፣ መቼ እንደጸደቀ
2- ወደ ፓሪስ የሄዱት አትሌቶችና አሰልጣኞች በማንና እንዴት እንደተመረጡ፣ ማን የመጨረሻ ምርጫ ዝርዝሩን እንዳቀረበና ለኦሊምፒክ እንዳስተላለፈ፣
3- ውድድሩ ቦታ ስላለው ወቅታዊ የዓየር ንብረት የህክምና ስታፉ መረጃ መስጠቱን፣ በተሰጠው መረጃ መሰረት ልምምድ መሰራቱን
4- የኢትዮያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በአትለቲክስ ፌዴሬሽን ስራ ላይ ጣልቃ የገባባቸው ጉዳዮች፣ ላሰራ ብሎ እንቅፋት የሆነበት አግባብ ዝርዝር
5- የቴክኒክ ክፍሉ አትሌቶች ሲንቀሳቀሱ መግለጫ የሰጠበት አብይ ምክንያት
6- የቴክኒክ ክፍሉና የቴክኒክ ክፍሉ ሰብሳቢ በዚህ ኦሊምፒክ ማስጀመሪያ ወቅት ያሰሙት አቤቱታ በስራ አስፈጻሚው ዘንዳ ተቀባይነት አለው? ከሌለው ለምን? ካለውስ ለምን
7- አትለት ጉድፋይ ሶስት ውድድር እንድታደርግ የወሰነው ፊዴሬሽኑ ወይስ ኦሊምፒክ? ከዚያም በላይ መበቱ ነገራት ወይስ በልዩ ሁኔታ? ሲኒየር አሰልታኞች ተተይቀዋል? ወይስ አስለታኟና የትዳር አጋሯ በራሱ ውሳኔ ወሰነ?
8- የአትሌት ማናጀሮች ውሳኔ፣ ጣልቃ ገብነት፣ ሙስና፣ እውቀት፣ እንዴት ይለካል? ያለው የግንኙነት አገባብ መርህን የተበቀ ነው ወይስ ለሳንቲም እያሉ ተወዳዳሪዎችን በተደራራቢ ውድድር ይማግዳሉ? ለመሆኑ አንድ አትሌት ስንት ውድድር እንዳደረገ በዳታ ተያዞ ይቀመጣል
አትሌቶች
1- በነጻነት የሚሰማቸውን እንዲናገሩ
2-ከምርጫ ጀምሮ በስልጠናና በውድድር ወቅት የተሰማቸውን ለያይተው እንዲናገሩ
3- ውጤታቸው ላይ ጫና ያሳደረው ዋና ጉዳይ ምን እንደሆነ እንዲናገሩ
4- እገሌ ወጣች፣ እገሌ ገባ ወዘተ በሚል፣ የገሌ አሰልጣኝ ተባረረ ወዘተ ዜናዎችን በግልጽ ምላሽ እንዲሰጡ ማድረግ
ሚዲያዎች
ከላይ ያሉት አሳቦች በሙሉ እንዳለ ሆነው ኦሊምፒክ ውድድር ላይ ያለ ቡድን ላይ በዚህ ደረጃ መዝመት ለምን እንድተፈለገ ቢገመግሙ፣ የሚጋለጥ ነገር ካለም በተባራሪ ሳይሆን በደንብ በማጣራት ለምን መስራት እንዳልተፈለገ ዞር ብለው ቢያዩ
የአንድን ሙሉ እውነት ቆርጦ ማቅረብ ውሸት እንደመዋሸት ስለሚቆጠር ከዚህ አንጻር ሲሰራጩ የነበሩ መረጃዎች በሙሉ ከመረጃ ግብአትነታቸው ውጪ መቼ፣ ለምን፣ እንዴት፣ በማን፣ ወዘተ ተሟልቶና ተመጣጥኖ ቀርቧል ማለት ይቻላል? ከዚህ አንጻር ሚዲያው ሃላፊነቱን ስለመወጣቱ በመረመር አቋምን በባለሙያ መነጽር ማሻሻል ተቃሚ ይሆናል። ሁላችንም !!
ይህ በወፍ በረር ያሰብኩትና በተናጠል መስልስ ቢፈለግላቸው ችግሩን አንጥሮ መፍትሄ ለማፈላለግ መንደርደሪያ ግብዓት ለማግኘት ይረዳል። ከዚህ ውጭ ግን በጅምላና ለራስ ፍላጎት ማሟያ የሚደረግ የደቦ ፍርድ ለተበላሸው ውጤት መድሃኒት ለማፈላለግ ስለማይረዳ በሚቀጥለውም ውድድር ተመሳሳይ ዕድል ከማፈስ አንድነም።
ማስታወሻ
በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ሲደርስ፣ ዓለም ዋንጫና ክሮስ ካንትሪ ላይ ቅጥፈት ያልተሰራበት ወቅት የለም። ግፍ ያልተሰራበት ጊዜ የለም። ሚድያው እንደ አሁኑ ክፍት ባለመሆኑ እንጂ ጉዱ ብዙ ነበር። ይህን ስል ግፍ ድሮም ነበርና የአሁኑ ከቁብ መቆተር የለበትም ለማለት አይደለም። ግን አዲስ እንዳልሆነ ለማመላከት ነው።
ቀነኒሳ ሰሞኑንን እንዳለው የጾታ ጥቃቱ በገፍ ነው። አትሌቶች ደም ተፍተው ከሚያገኙት ቁጭ ብለው 15 ከመቶ የሚዘርፉ ብዙ ነበሩ። ሁሉም ተረስቶ ዛሬ ዳግም ለመመለስ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲፈርድ እየጮሁና እያስጮሁ ውጤቱ እንዲበላሽ ድርሻ መውሰዳቸው ያስገርማል።
በነካካሁዋቸው ጉዳዮች በተቻለ መጠን በተከታታይ በዌብሳይቴ ላይ እጥፋለሁ። የተነሳው አዋራ ለማገናዘብ እንዳንችል፣ መመርመር እንዲሳነን አድርጓልና ስድብና ውግዘት እጠብቃለሁ። በጥቅሉ ሁሉንም ጉዳይ አተራምሰነዋል። ሳንጠራውና ግሩን ነቅሰን ሳናወጣ ርምጃ መውሰድ ማስተካከል እንደማንችል አውቀን ከቡናኙ አዋራ እንሽሽ!!
ዝግጅት ክፍሉ