የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ “ልዩ” ሲል የጠራውን የውጭ ምንዛሬ ጨረታ በነገው ዕለት እንደሚያካሂድ መግለጹን ተከትሎ ዛሬ የምንዛሬው ገበያ መፋዘዙን ታዛቢዎች አመለከቱ። ባንኩ እንደ አስፈላጊነቱ በቀጣይ ሳምንትም ተመሳሳይ ጨረታ እንደሚያወጣ አስታውቋል።
ፋልጎት ያላቸው ባንኮች የጨረታ መግዣ ዋጋቸውን በማቅረብ እንደሚችሉ የሚጋብዘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ማስታወቂያ፣ ጨረታው ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ እስከ 6 ሰዓት እኩለ ቀን እንደሆነ አመልክቷል።
የአሜሪካ ዶላር ለሚፈልጉ ባንኮች የወጣው የጨረታ ማስታወቂያ ባንኮቹ የሚፈልጉትን የዶላር መጠን፣ የሚገዙበትን ዋጋ ገለጸው እንዲያሳውቁ አድራሻ አስቀምጦ ነው የጋበዘው።
ጨረታው ከተጠናቀቀ በሁዋላ በተመሳሳይ ቀን አመሻሽ ላይ ይፋ እንደሚሆን ባንኩ ይፋ አድርጓል። አሸናፊዎች ያሸነፉትን ምንዛሬ ግዢ በተመሳሳይ ቀን እንደሚፈስሙም ማስታወቂያው አመልክቷል
ገበያው እየታየ ወይም እንደ ሁኔታ በቀጣይ ሳምንታት ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ሊከናውን እንደሚችል ማስታወቂያው ላይ ተጠቅሷል። ይህ በማስታወቂያው ውስጥ ያለው ቅድመ ማስታወቂያ፣ የጨለማውን ገበያ ግራ እንዳጋባ መረጃ ያላቸው አመልክተዋል።
ብሄራዊ ባንክ ጨረታ ማውታቱ ከተሰማ ወዲህ ዛሬ በውጭ ምንዛሬ ገበያ ዙሪያ መፋዘዝ እንደታየ ተተቃሚዎች ገልጸዋል። አንድ ዶላር 120 ብር ሂሳብ ለመሸጥ ሙከራ ቢኖርም በተባለው ዋጋ ፈላጊ እንዳልነበር ተጠቁሟል።
በየሰዓቱ የምንዛሬ ዋጋ ማሻቀቡን እየጠቀሱ መረጃ ሲያሰራጩ የነበሩ ሚዲያዎችና የማህበራዊ ሚዲያ የፊት ተዋንያኖች የገብያውን መፋዘዝ ተከትሎ እንደወትሯቸው መረጃ ሳይሰጡ ውለዋል።