የትዕግስት አንበሳነት፣ የሲፋን በቀል አገራቸውን ለሚወዱ ሁሉ እረፍት የሚነሳ ነበር። ሲፋን ሶስት ወርቅ ነጠቀችን። በጉብዝናዋ እየተደነቅን የገፏትን እየረገምን የተከታተልነው ውድድር በሁለት ምክንያቶች ትዕግስትን እንድናነግሳት ያስገድደናል። ሲፋን እንደ ዛሬ ሚዲያው አሸንና ሳይመርጥ ያገነውን ሁሉ የሚረጭ ባልሆነበት ዝግ ውቅት ሲሰራ የነበረውን አገራዊ ክህደት፣ ፍትህ አልባነትና ፖለቲካዊ ውስልትና ያመላከተ ነው።
እንደ ሲፋን ያሉ የከፋቸው በርካታ የኢትዮጵያ ልጆች በመኖራቸውና ከዚያም በላይ ስደቱ ሊበረክት ስለሚችል ስጋት የገባቸው ይህን ለመታገል ጠንካራ የአትሌቲክስ ማህበር አቋቁመው ነበር። ማን አፈረሰው? ለምን ፈረሰ? እንዴት ፈረሰ? የወቅቱ ባለስልጣናት ምን ብለው አስፈራተው እንዲፈርስ አደረጉት? ይህን ጉዳይ ሚዲያዎች እንዲያጠሩት ዝግጅት ክፍላችን ያሳሰባል። ዛሬ የተነሳው የጩኸት ማዕበል ምን አልባትም እዚያ ውስጥ የተደበቀ ጉዳይ ሊሆን ይችላልና።

ሲፋን የአውሮፓን የሚደብት ሙቀት ነዋሪ በመሆኗ ለምዳዋለች። ይህንንም እንደ አንድ የማሸነፊያ ግብአት ተጠቅማበታለች። ሃይሌ “የኢትዮጵያ አትሌቶች አይፈረድባቸውም ሙቀቱ እጅግ ሃይለኛ ነው። ወበቁም ከባድ ነው” ሲል በዋልታ ቲቪ በኩል እንደመሰከረው አየሩን ተቋቁማ የብር ሜዳሊያ ማግኘቷ ድንቅ ያደርጋታል። ሌላው ውድድሩን ከአመኔ ጋር በመነጋገር ለመቆጣጠርና ዋና ተፎካካሪ የሚባሉትን የኬንያ አትሌቶች ለማቃጠል ያደረገችው የተጠና ሩጫ ተሳክቶላታልና ይህም ሌላ ጀግነቷ ነው።
ትዕግስት አሰፋና አመኔ በሪሶ ሁለት ኪሎ ሜትር ተለያይተው የመጨረሻው መስመር ላይ ዳግም ተገኛኙ። አመኔን አቅፋ ትዕግስት ወርቁን ማጣቷን ነገረቻት። አመኔ ፊት ሃዘን፣ ትዕግስት ፊት ተመሳሳይ የፈለገግታ ቅሬታ አሳየች። ግን ሟርትን ያሸነፉ፣ የሽንፈት ዘመቻን የበጣጠሱ መሆናቸውን አሳዩ። በፓሪስ ከፈተኛ ሙቀት የሰሩት ታሪክ ድንቅ ነው።
ጀግኖቹ ውድድሩን የበተኑት ልክ 33 ኪሎ ሜትር ላይ ነበር። ቆረጣው የተጀመረው 31 ኪሎሜትር ላይ ነበር። ስድስት ሆነው አንድ ኪሎሜትር አካባቢ እንደተጓዙ አንደኛዋን ኬንያዊት ቆርጠው አምስት ሆኑ። ዋላዎቹ ወደ ፓሪስ እምብርት ሲቃረቡ የህዝብ ድምጽ ነዳጅ ሆነላቸው። የተስፋዬ ቶላ ወኔ ታወሳቸው።
እየተናበቡ፣ እየተንሾካሾኩ ውድድሩን ተቆጣጥረው ከፊታቸው የኢትዮጵያን ሰንደቅ የማንገስ ህልማቸውን ሰገሩ። ለኒዘርላንድ የምትሮጠው ወገናቸውና ሲፋን ሁለት ኬንያውያን እግር በእግር ተያይዘው እስከ 40 ኪሎ ሜትር ዘለቁ። አንዷ ጀግናችን አመኔ በሪሶ አርባኛው ኪሎ ሜትር ላይ ሽንጧን ያዛትና ለቀቀች። ትዕግስት አሰፋ ግን አከረረች ውድድሩ በሲፋንና ትግስት መካከል ሆነ። አንጀታሟ ሲፋን በለመደችው የአውሮፓ የበጋ እሳትና ወበቅ አልተበገረችም። ወርቁን ተረከበች። የወቅቱ አስተዳደሮች በፈጸሙባት ደባ አገሯን ጥላ የወጣችው ሲፋን ከኢትዮጵያ አገሯ ወርቅን ለሶስተኛ ጊዜ ነጥቃ ለኒዘርላንድ አስረከበች። በኢትዮጵያ አንበሳ ልጅ ቲኪ ገላና ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ነው የወሰደችው። እሷንና ሌሎቹን ጨምሮ እንደ ባዕድ ገፍታችሁ ላባረራችሁ ሁሉ እንኳን ደስ ያላችሁ። የታሪክ በለዕዳዎች!!
ነገሩ ልብ የሚሰብር፣ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዙሪያ ይሰሩ የነበሩ መረን የለቀቁ ድርጊቶች፣ ወንጀሎች፣ ማግለሎችና ፖለቲካዊ ጫና ሳቢያ ያጣናትን ሲፋንን በቁጭት አየናት። የወርቅ ሚዳሊያ ብቻ ሶስት ጊዜ ወስዳብናለች። ይህ ሁሉ የሚካሄድበት የኢትዮጵያ ስፖርት ቢጠና ዛሬ ከሚሰማው በላይ ጆሮን የሚቀድ፣ ልብን የሚያደማ፣ ህሊናን የሚሸነቁር ጉድ እንደሚሰማ ጥርጥር የለውም።
ውድድሩ ሊጠናቀቅ 15 ደቂቃ ግድም ሲቀር አምስቱ አትሌቶች በኢፍሊል ታውን ሲያልፉ ህዝብ የኢትዮጵያን ባንዲራ የያዙ ድምጻቸውን አሰሙ። ሲፋንን ለመቁረጥ የተነሳቸው ልዕልታችን አልሆነላትም። ሲፋን በአስር ሺህና አምስት ሺህ የብር ሜዳሊያዎችን ካፈሰች በሁዋላ የኦሊምፒክ ሪኮርድ ሰብራ የማራቶን ድልን ተቀዳጀች። ኒዘርላንድን አበራቻት።
Sifan Hassan of the Netherlands wins the women’s marathon after winning bronze in both the 5000m AND 10000m this week! She does it in an Olympic record time too.
A truly phenomenal feat of endurance running at these games.
ትዕግስት አሰፋባ አመኔ በሪሶ ሲፋን ሃሰን