ስካይ ስፖርት ያነጋገራቸው ኡናይ ኡምሪ ” አርሰናል ልቋል” ሲሉ ከጨዋታው በሁዋላ ተናግረዋል። መናገራቸው ብቻ ሳይሆን በተግባርም ቡድናቸው በሜዳው መከላከል መርጦ አድፍጦ በሞከራቸው ኳሶች ግብ ለማስቆጠር የሚያስችል ታክቲክ መምረጡ አርሰናልን ከመፍራት መሆኑንን የሚያረጋግጥ ነው።
አርሰናል አሁን አሁን ሁሉንም ቡድን በየትኛውም ሜዳ የማሸነፍ ስነ ልቦና መላበሱን ማሳየት የጀመረ ቡድን ነው። ተሰላፊዎቹ ብቻ ሳይሆኑ መቀመጫ ላይ ያሉት ተተኪዎች ሁሉ የሚአስፈሩ እየሆኑ ነው። በየዓመቱ ቡድኑ ጥልቅ እንዲሆን የተሳካ ዝውውር እያደረገ ሲሆን ማጽዳቱም በዛው መጠን የተሳካ ነው።
አሁን ላይ ለአርሰናል እየተሰጠ ያለው ግምት ከፍተኛ ነው። የሲቲ የመሃል ሜዳ ምሰሶ ፡ቡድቡ አሁን ላይ ከሲቲ ጋር ተስተካክሏል” ሲል ምስክርነት እንደተሰጠው ከውድድር ወደ ውድድር እየጎለበተ ሲሄድ አሁን ካለው በላይ አስቸጋሪ ቡድን እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። በዚህ ስነልቦና አስቶን ቪላን በሜዳው አሸንፎ ሶስት ነጥብ የወሰደው አርሰናል፣ የተከላካይ ወረዳ ሁለት ጊዜ ታልፎ ጎል ሊሆኑ የሚችሉ ጎሎችን ራያ በድንቅ ብቃት አድኗቸዋል። በዚህም የእለቱ ምርጥ ተጫዋች ሆኗል። ራምስዴልም እንደሚበለጥ አምኖ እንዲቀበል ተገዷል ሲሉ ኮሜንታተሮች ገልጸዋል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አስቶንቪላን በሜዳው 2 ለ 0 በማሸነፍ የፕሪሚየር ሊጉን ሁለተኛ ድል ሲያስመዘግብ የታየው ደስታ፣ በጨዋታ ወቅት ተጨዋቾቹ እየተነጋገሩ ስራቸውን ሲሰሩ ላስተዋላቸው የሆነ ነገር እንደሚፈልጉ አመላካች ነው።
ተቀይሮ የገባው ትሮሳርድ በ67ኛው ደቂቃ ግብ ሲያስቆጥር ያሳየው ስሜት “መቅመጥ አይገባኝም” አይነት ዕልህና ” እኔ ማለት እንዲህ ነኝ” ዓይነት ስሜት ያዘለ ይመስላል። ሁሌም ከመቀመጫ እየተነሳ ግብ የሚያስቆጥረው ትሮሳርድ ግብ ማስቆጠሩ ብቻ ሳይሆን ማርቲኔል 75 ደቂቅ ይህ ነው የሚባል ስራ ሲሰራ ካለመታየቱ ጋር ” ማን ቀድሞ ይሰለፍ” የሚለውን ተደጋጋሚ ጥያቄ እንደ አዲስ በማንሳት ሚዲያዎች ሲወቅጡት ነበር።
እንዲሸጥ ትኬት ተቆጥሮበታል የተባለው ፓርቴ በ77ኛው ደቂቃ ጎል ማሳረፉ ብቻ ሳይሆን፣ በእለቱ ከሬስ ጥሩ አለመሆን የተነሳ የነበረበትን ጫና ተቋቁሞ መሃሉን ለመቆጣጠር ያደረገው ጥረት ዓይን የሚገባ ነበር። መጥነኛ ችግሮች ያስተናገደው የራይስ ስራዉን በደንብ አለመስራትም ያመጣውም ችግር እንደሆነ ውድድሩ ላይ አስተያየት የሰጡ ሲገልጹ ነበር።
በቅድመ ጨዋታ የማሸነፍ ግምት የተሰጠው አርሰናል ኳስ ተቆጣጥሮ በመጫወት ብልጫ ቢወስድም ከወትሮው እንቅስቃሴያቸው አንሰው የታዩና ቀዝቃዛ የነበሩ ነበሩ።
በመጀመሪያው ሣምንት የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች አርሰናል ዎልቭስን 2 ለ 0 ሲረታ፣ አስቶንቪላ ዌስትሃምን 2 ለ 1 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡
በፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች፣ ብራይተን ማንቼስተር ዩናይትድን 2 ለ 1፣ ቶተንሃም ኤቨርተንን 4 ለ 0፣ ዌስትሃም ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 0፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ሳውዝ ሃምተንን 1 ለ 0፣ ፉልሃም ሌስተር ሲቲን 2 ለ 1 እንዲሁም ማንቼስተር ሲቲ ኢፕስዊች ታውንን 4 ለ 1 አሸንፈዋል፡፡
ማንችስተር አሁንም ቡድን አይመስልም። አዳዲስ ተጨዋቾች ስለበዙ ገና ጊዜ የሚፈልግ ይመስላል። ኤቨርቶን ብር እንደሌለው በመግለጹ ቡድኑንን ለማጠናከር የሚወስደው አንዳችም እርምጃ ስለሌለ ከዚህም ሊያሽቆለቁል እንደሚችል የእንግሊዝ ሚዲያዎች እየገለጹ ነው። ዛሬ “ከአሁን በሁዋላ ቼልሲ ተጫዋች መግዛት ማቇም አለበት” በሚል በስፋት የተተቸው ቼልሲ ከሜዳው ውጪ ከዎልቭስ፣ በርንማውዝ ከኒውካስትል፣ ሊቨርፑል ከብራንድፎር ዛሬ ከሰዓት በሁዋላ ይጫወታሉ።