በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ገበያ እንደሚወርድ ዘርፉን የሚያጠኑ አመለከቱ። ” ብር ንብረት ላይ ማስቅመጥ” በሚል በስፋት በሪል እስቴት ዘርፍ የተሰማሩ አብዛኞቹ አሁን ላይ ዕዳ መክፈል እንደተሳናቸውም ተሰምቷል።
ከገንዘብ መገሸብ ጋር በተያያዘ ነጋዴዎችና አስመጪዎች የነበሩ ወደ ሪል እስቴት ግንባታ መሰማራታቸውን የሚገልጹ የዜናው ባለቤቶች እንደሚሉት ከሆነ ከደንበኞች የሽያጩን ቅድሚያ ክፍያ 20 ከመቶ እየሰበሰቡ ስራውን ቢጀምሩ አሁን ላይ ያላሰቡት ገጥሟቸዋል።
ላለፉት ሁለት ዓመታት መንግስት ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ በመከተሉና ብድር አሰጣጥና አከፋፈል ላይ በጣለው አስገዳጅ ህግ መነሻ ከፍተኛ መጠን ያለው ብር ሰብስቧል። ብሄራዊ ባንክ እስከ 2.3 ትሪሊዮን ብር መሰብሰቡን ለአብነት የሚገልጹት እነዚህ ወገኖች፣ በሪል እስቴት ዘርፍ የተሰማሩት ነጋዴዎችና አስመጪዎች ያላሰቡት ገጥሟቸዋል።
በተለያዩ አግባቦች ባንክ ከሚቆጣጠረው መንገድ ውጪ ከፍተኛ ሃብት ሲዘዋወር እንደነበር ያስታወሱትና ሂደቱን የሚከታተሉ ለኢትዮሪቪው ሲያብራሩ የሪል እስቴት አልሚዎችን ያላሰቡት ገጥሟቸዋል። በጠበቁት ደረጃ ቤት የሚገዛና ክፍያ የሚፈጽም ድንበኞች እጥትረት አጋጥሟቸዋል። ይህንኑ ተከትሎ በአብዛኛው ሪል እስቴቶች ” በታላቅ ቅናሽ” የአዋጅ ማስታወቂያ ከፍተኛ ሃብት እያፈሰሱ መሆናቸውንም አመልክተዋል።
ባንኮች ያበደሩትን መሰብሰብ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥርና ህግ ስለተጣለባቸው አልሚዎቹ ብድራቸውን እንዲከፍሉ አበዳሪ ባንኮች ጫና ማሳደራቸውን ተከትሎ እዳቸውን ለመክፈል ቀደም ሲል የሰሰቡትን መሬት፣ ህንጻና ቤት ለመሸጥና ዕዳቸውን ለመክፈል ቢሞክሩም አሁን ላይ ገዢ ማግኘት አልቻሉም።
“ገንዘብህን ንብረት ላይ አስቀምጥ” በሚለው የአንድ ሰሞን መፈክር በዘረፋ፣ በሙስና፣ በትስር ብድር፣ ጤነኛ ባልሆኑ ተለያዩ አግባቦች ያገኙትን ገንዘብ ቋሚ ንብረት ላይ ያስቀመጡ “ከፍተኛ ባለሃብት” የሚባሉት ሳይቀሩ አሁን ላይ ብር የላቸውም። መልሰው ቋሚ ንብረታቸውን ለመሸጥና የሚንቀሳቀስ ገንዘብ ለመያዝ ቢፈልጉም ገዢ ማግኘት አልቻሉም። አበዳሪ ባንኮች ቁጥጥሩ ስለጠናባቸውና በፖሊሲ ስለታሰሩ ያበደሩትን ለመሰብሰብ በማሲያዣነት የያዙትን ንብረት ወደ መውረስ የሚዘዋወሩበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን መረጃውን ያካፈሉን ገልጸውልናል።
ቀደም ሲል የሪል እስቴት ላይ የተሰማሩ የውጭ ምንዛሬ በመሰብሰብ ስራ መሰማራታቸውን ገልጸን መዘገባችን ይታወሳል። በዚህ ዜና ሰፊ ትንታኔ ይዘን እንቀርባለን።