“ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ አትሌት ገዣኸኝ አበራ በፌዴሬሽኑ ውስጥ ከፍተኛ የአቅም እጥረት ችግር እንዳለ ጁላይ 17 በይፋ ሲናገር ግንባር ያደረገው ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ነበር። ይህን ያለው ኦሊምፒክ ሊጀመር ቀናቶች ሲቀሩት ነው። ስለ ውድድር የሚያውቅ፣ ለአንድ ተወዳዳሪ ስነ ልቦና ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ የሚረዳና ሮጦ ያሳለፈው ገዛሃኝ አበራ ስለ አቅም ማነስ ሲናገር እሱስ? ማራቶን ከመሮጡ ውጪ የት ሄዶ የገነባው አቅም ነው ያለው? የአቅሙ ጉዳይ ለጊዜው ይቁምና ለምንድን ነው ኦሊምፒክ ሲደርስ እየጠበቀ “የኢትዮጵያ ህዝብ ፍረድ” እያለ የሚጮኸው? ምንድን ነው ፍላጎቱ? ዕውነት የአቅም ችግር ካሳሰበው “እኔ አቅም የለኝም ብሎ መልቀቂያ በማስገባት ለምን ቀድሞ ምሳሌ አይሆንም? ነገሩ ሌላ ነው። ማን እንደሚጋልበው ይታወቃል”
ኦሊምፒክ፣ ዓለም ሻምፒዮናና ተመሳሳይ ታላላቅ ውድድሮች ሲቃረቡ ፍትጊያ አይጠፋም። ይህ ባህል ሆኖ የኖረው ሽኩቻ መነሻው “ተቆርቋሪነት የሚባል ታቤላ ያለው የሚደረብበት ነው። ሰሞኑን መልኩ ይቀያየር እንጂ የድራማው ሁሉ ማረፊያ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ከሃላፊነት የማስነሳት ወይም “መፈንቅለ ደራርቱ ቱሉ” ነው።
“አሁን ላይ የኢትዮጵያ አትሌቶች ውድድር ላይ ናቸው። ጥፋት እንኳን ቢኖር ለአንድ ሳምንት መታገስ እንዴት ያቅታል? ሚዲያዎችስ እንዴት ይህን በሃላፊነት ስሜት አያስቡም” ሲሉ የገለጹልን ከግብግቡ ጀርባ ስላለው የተደራጀ አካሄድ መረጃ ያላቸው ወገኖች ናቸው።
ውድድር እየተጠበቀ፣ ህዝብ ወርቅና ብር በሚናፍቅበት ወቅት ሆን ተብሎ የንትርክ ዜና የሚያሰሙት ሁሉ ምህላቸው “የኢትዮጵያ ህዝብ ፍረድ” ነው። ህዝብ ምን አውቆ ይፍረድ? ማን ትክክለኛውን መረጃ ይስጠው? አንዳንድ ሚዲያዎች የአንድ ሰው አፍ እስኪመስሉ ድረስ አጀንዳ ሰፋሪዎች ናቸው። አንዳንዶቹ ደግሞ የአንድ ወገን መረጃ ያለ አንዳች ማጣራት የሚያፈሱ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ የጉዳዩን ባለቤት ዘንግተው ያለ አንዳች ህጋዊ ማስረጃ “ወኪል ነን” የሚሉ ” ተበድለን” ሲሉ ለመከረኛ የላይክና የሼር ግብአት ሲባል መረጃው የሚያመጣው ጉዳትና ተዓማኒነት ሳይመዘኑ የሚረጩ ናቸው።
” እነማን፣ እንዴትና በምን መልኩ ተደራጅተው አትሌቶቹን በመረበሽና ውጤት ለማበላሸት እየሰሩ እንደሆነ ከውድድሩ በሁዋላ እንገልጸዋለን” የሚሉት ለጊዜው ስማቸውን እንዳይጠቀስ የጠየቁ ወገኖች፣ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነቷ ለማሰናበት የተጀመረው ዘመቻ ይሳካል ብለው እንደማያምኑም አመልክተዋል።
“ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገዣኸኝ አበራ በፌዴሬሽኑ ውስጥ ከፍተኛ የአቅም እጥረት ችግር እንዳለ ጁላይ 17 በይፋ ሲናገር ግንባር ያደረገው ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ነበር። ይህን ያለው ኦሊምፒክ ሊጀመር ቀናቶች ሲቀሩት ነው። ስለ ውድድር የሚያውቅ፣ ለአንድ ተወዳዳሪ ስነ ልቦና ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ የሚረዳና ሮጦ ያሳለፈው ገዛሃኝ አበራ ስለ አቅም ማነስ ሲናገር እሱስ? ማራቶን ከመሮጡ ውጪ የት ሄዶ የገነባው አቅም ነው ያለው? የአቅሙ ጉዳይ ለጊዜው ይቁምና ለምንድን ነው ኦሊምፒክ ሲደርስ እየጠበቀ “የኢትዮጵያ ህዝብ ፍረድ” እያለ የሚጮኸው? ምንድን ነው ፍላጎቱ? ዕውነት የአቅም ችግር ካሳሰበው “እኔ አቅም የለኝም ብሎ መልቀቂያ በማስገባት ለምን ቀድሞ ምሳሌ አይሆንም? ነገሩ ሌላ ነው። ማን እንደሚጋልበው ይታወቃል” የሚሉት ወገኖች ገዛኸኝ አበራ ፓሪስ ደርሶም የሰጠው መረጃ ስህተት ስለመሆኑ ያነሳሉ።
” ከኢትዮጵያ ህዝብ የሞራል ካሳ እጠብቃለሁ ” ይላል ገዛኸኝ አበራ ከፓሪስ። አክሎም “ህብረተሰቡ በቃ ሊል ይገባል” ሲል ይጣራል። ገዛኸኝ አበራ በዚህ አያበቃም። ” ከሀገሬ ህዝብ ከፍተኛ የሞራል ካሳ እፈልጋለሁ ፣ የኔ የሞራል ካሳ ደግሞ ህዝቡን ከእውነት ጋር ቆሞ የደረሰብኝን የተቀነባበረ ተንኮል እንዲቃወምና ለአትሌቶቻችን ፍትህ እንዲሰጥ ሲያደረግ ነው” በሚል ህዝብ ፌዴሬሽኑ ላይ በተለይም ስሟን ጠቅሶ አስቀድሞ በብቃት ስም ሲያወግዛት የነበረችውን ደራቱን ” አውርዱ” ይላል።
ይህን ለማለት መነሻው ፓሪስ ሲደርስ ስታዲዮም መግቢያ ፈቃድ ስላልተሰጠው ነው። “ገዛኸኝ አበራ የፌዴሬሽኑ ምክትል ሆኖ ሳለ ይህ ሊሆን አይገባም። ክብረ ነክም ነው” በሚል ላቀረብነው ጥያቄ ከፓሪስ ያገኘነው ምላሽ ” የሚመጣበትን ቀን ሲቀያይር ስለነበር ሲስተሙ ራሱ ነው ስሙን ያነሳው። በሚቀጥለው ቀን ግን ተስተካክሎለታል። ደራርቱ ቱሉ ራሷ ነች የተቀበለችው። የጉዞ ሰሌዳውን በመቀያየሩ ሳቢያ የተፈጠረ ክፍተትን ህዝብ ዛንድ ወስዶ የዓላማ ማስፈጸሚያ ማድረግ ነውር ነው። ዓላማው አስቀድሞ እንደተባለው የመፈንቅለ ደራርቱ ጥሪ ነው”

” ከሀገሬ ህዝብ ከፍተኛ የሞራል ካሳ እፈልጋለሁ ፣ የኔ የሞራል ካሳ ደግሞ የህዝቡን ከእውነት ጋር ቆሞ የደረሰብኝን የተቀነባበረ ተንኮል እንዲቃወምና ለአትሌቶቻችን ፍትህ እንዲሰጥ ሲያደረግ ነው ” ሲል ጥሪ ያሰማው ገዣኸኝ አበራ እነ መሰረት ደፋርና ቤተሰቦቿን በማሰባሰብ ደራቱ ቱሉ በዚህ መልኩ ነበር የተቀበለችው።
” አትሌቲክሳችን መጫወቻ መሆን የለበትም ህብረተሰቡም በቃ ሊል ይገባል ይሄ ነው የኔ ትክክለኛ ካሳ” ያለው ገዛኸኝ አበራ ቀደም ሲል ሲናገር የነበርውና ሌሎችም አሳቡን እንዲያጎለብቱት የተደረገው የመፈንቅለ ደራርቱ ጥሪ ከኦሊምፒክ መልስ ግልጥልጥ እንደሚል ጉዳዩን የሚከታተሉ እየጠቆሙ ነው።
ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ራሱን ሲያገል ምክትል የነበረቺው ደራርቱ ደጋግም አማላጅ መላኳን፣ ወንበሩን እንደማትረከብና ቦታው ለይሃሌ አግባብነት ያለው እንደሆነ ደጋግማ መግለጿን፣ ሃይሌን ጥይቆ ወይም ሁለቱንም አስቀምጦ ምላሻቸውን የሚያሰማ ቀና አሳቢ ሚዲያ ካለ እውነቱን መረዳት እንደሚቻል የጠቀሱት ክፍሎች፣ ሚዲያው ረግቶ እንዲያጤን መክረዋል። ስምና ዝናን ላይ በመንተራስ የሚረጩ መረጃዎች ውሎ ሲያድር ሌላም ጣጣ ሊያስከትሉ ስለሚችሉ እንዲታሰብበት አሳስበዋል።
የባህል እና ስፖርት ሚንስትር ሚንስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት በወቅታዊ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሁነት ላይ ለትሪቡን ስፖርት የራድዮ ፕሮግራም በላኩት መልዕክት ” የአትሌቲክስ ውጤታማነታችን በአደገኛ ቀውስ ላይ ነው ” ማለታቸው ተሰምቷል። ስጋታቸው መልካምና የሚደገፍ ቢሆንም ይህ የታያቸው ፓሪስ ውድድር ሲጀመር ነው ወይ? “ድንቄም የስፖርት መሪ የሚያሰኝ” ሲሉ የወቀሷቸው እሳቸውንም የዚሁ የዘመቻው ተሰላፊ አድርገዋቸዋል።
ፕፕፕፕፕፕፕፕፕ
አምባሳደሩ በመልዕክታቸው ” የኦሎምፒክ ተሳትፎ ሆነ የአትሌቲክስ ውጤታማነታችን በአደገኛ ቀውስ እና የመንገዳገድ ጎዳና ላይ ነው ፣ ችግራችን ፈርጀ ብዙ ቢሆንም በግልፅ መነጋገር እና ተጠያቂነት ማረጋገጥ መቻል አለብን ” በመርህ ደረጃ የሚደገፍ ቢሆንም፣ ንግግራቸው ወቅቱን ያላገናዘበ ነው። “ገርሞናል” ሲሉ ሚኒስትሩ የዋሉበትን ሰፈር ገልጸው የተቹ “ግምገማም ቢሆን ከውድድሩ በሁዋላና አስቀድሞ እንጂ በውድድር ላይ የሚከናወን ባለመሆኑ ሚኒስትሩ እርማት ሊወስዱ ይገባል። አምባሳደርም አይመስሉም” ሲሉ የደቦው ዘመቻ አካል መሆናቸውን አመላክተዋል።
ከሁሉም በላይ የስፖርት ፌዴሬሽኖ ሉዓላዊ መሆናቸው እየታወቀ “መንግስት ይህን ተግባራዊ ለማድረግ በግልፅ ስራዎችን በመስራት ላይ ነው” ሲሉ መንግስት በቀጥታ ጣልቃ ለመግባት መዘጋጀቱን ማስታወቃቸው አስድንጋጭ ሆኗል። ንግግራቸው የመንግስት አቋም መሆኑ ቢያጠራጥርም ሚንስትር ዴኤታው ለራድዮ ጣቢያው ላኩት የተባለው መልዕክት በጥቅሉ ጥሬ መሆኑን እነዚሁ ወገኖች ተናግረዋል።
ተቺዎቹና አካሄዱን በመረጃ አግኝተነዋል የሚሉት ወገኖች እንደሚሉት የአገሪቱ ስፖርት በበርካታ ችግሮች የተተበተበ በመሆኑ መንግስት በተለይም እሳቸው ብዙ ስራ እንደሚጠብቀባቸው አይክዱም። ነገር ግን በደፈና ” ጀብደኛ ፣ አምባገነን ፣ ሴሬኛ እና ክፉ ሰዎች ስፖርታችንን በግል ንብረት ( እንደ አክስዮን ማህበር ) ጠፍረው ይዘው እያሰቃዩት ይገኛሉ ብሎ ወቅቱን ያልጠበቀ መረጃ መርጨት ፋይዳ የለውም።
ይህን መረጃ ቆጥበው የሰጡ ወገኖች እንዳሉት ደራርቱ ቱሉ ጥፋት ልትሰራና ልትሳሳት ትችላለች። ሰው በመሆኗ የመሳሳት መብትም አላት። ካበዛችውና ስህተቷ ከአቅም በላይ ከሆነ በየሚዲያው መጮህ ሳይሆን ሰክኖ መወያየት ግድ ነው። በውይይትና በመረጃ መግባባት ካልተቻለ በሰነድ አስደግፎ ከአንድም ሁለትና ሶስቴ ማሳሰቢያ መላክ፣ በስብሰባ ቃለ ጉቤዎች ላይ ልዩነትን ማስመዘገብ፣ ይህ የማይሆን ሲሆን ውድድር ሲደርስ ውጤቱ ለማጠልሸት በየሚዲያው ወሬ ከመርጨት አስቀድሞ በአደባባይ ማፍረጥረጥ አግባብ ያለው አካሄድ ነው። ኦሊምፒክ ኮሚቴንም ቢሆን በተመሳሳይ መክሰስ ሲቻል “መንግስት ጣልቅ ይግባ፣ መነግስት ጣልቅ ይገባል” በሚል የጅል አካሄድ መከተል እንደማይጠቅም እነዚሁ ወገኖች ገልጸዋል።
ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በቀጥታ ደብዳቤ ለመጻፍ እንደተዘጋጁ የሚያወሱት እነዚ ወገኖች ለጊዜው ፓሪስ ላሉት የኢትዮጵያ አምባሳደሮች መልካም ውጤት ተመኝተዋል።
ዝግጅት ክፍላችን ይህንኑ ደብዳቤና መፈንቀለ ደራርቱ ቱሉን የሚመሩትን ወገኖች አካሄድና ቡድን ሙሉ በሙሉ የሚገልጽ ጽሁፍ ከውድድር ፋጻሜ በሁዋላ ይፋ እንደሚያደርግ ከወዲሁ ይገልጻል።
ማሳሰቢያ – አስተያየት ሰጪ ወገኖች በምርጫ፣ በአሰራር፣ በዝግጅት ወይም በአጠቃላይ ፌዴሬሽኑ እንዲሁም አመራሮቹ ችግር ወይም ግድፈት የላቸውም የሚል መከራከሪያ ያቀርቡም። ዓላማቸውም እሱ አይደለም። አሁን ከሚሰራጩት ስጋና ደም የተላበሱ የስልጣን ሽኩቻ አጀንዳ በላይ የሰከነና አገርን ሊጠቅም የሚችል ማሳሰቢያ ከአማራጭ መፍትሄ ጋር እንደሚያቀርቡ ጠቅሰዋል።