” ለሚፈጠረው ችግር እኛ ተጠያቂ አይደለንም ” ሲል የትህነግ ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን አስታውቋል። በትህነግ ውስጥ የተከፍለውና በድርጅቱ ባህል “ህንፍሽፍሽ” የሚባለው መሰነጣጠቅ ወደ ሃይል ፍትጊያ እንዳያመራ ስጋቱ አይሏል።
ከጦርነት ማግስት እያገገመ ላለ ህዝብ ዳግም የዕርስ በእርስ ድግስ የሚያሰሙት አካላት ፍትጊያቸው ለስልታን እንደሆነ አንዱ ሌላውን ሲከስ የሚደመጥ ጭብጥ ምክንያት ነው።
ለትግራይ ህዝብ ሳይሆን ለራስ ዝናና ስልጣን ጥማት በትህነግ አመራሮች ውስጥ የተጀመረው ክፍፍል አድጎ ወደ መበላላት መድረሱን የሚጠቁሙ ሁለቱም አካላት ሰራዊት ስላላቸው ወደ አልተገባ ግጭት አምርተው አሳዛኝ ሁኔታ እንዳይፈጠር እያስጠነቀቁ ነው። መንግስት ከተራ ውዝግብ ይልቅ ህዝብን በሚጠቅም ጉዳይ መስራቱ እንደሚጠቅም ገልጾ ቢያስጠነቅቅም የእነ ዶክተር ደብረጽዮን ቡድን አቋሙን አልቀየረም።
በዚህ መነሻ የህወሓት ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ዛሬ ሰኞ ባወጣው ባለ 3 ነጥብ የአቋም መግለጫ ” ጤናማ ያልሆነ ሂደት ውጤታማና መልካም ጉባኤ መፍጠር ስለማይችል የሚያስከትለው አደጋ የከፋ ነው ” ሲል በድጋሚ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።
” ጤናማነት ሂደት የሌለው ውጤታማና መልካም ጉባኤ መፍጠር አይችልም ” ብሎ በማመን ከሚካሄደው ጉባኤ ራሱን ማግለሉን በድጋሚ አሳውቋል። ” በቡድናዊ ማን አለበኝነት የሚካሄድ ” ብሎ የጠራውን ጉባኤ ተከትሎ በሚፈጠረው ማንኛውም ችግር ተጠያቂ አለመሆኑ ክፕሚሽኑ በይፋ አስታውቋል።
ኮሚሽኑ ፤ የህወሓት ህጋዊ እውቅና በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት መመለስ ሲገባው ፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ በተሻሻለው የፓለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ እውቅና መሰጠቱ እንደማይቀበለው ጠቁሟል። የደርጅቱ ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ከሁለት ሳምንት በፊት ከሚካሄደው ጉባኤ ራሱ ማግለሉ ይታወሳል።
በህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት መካከል እና የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን መግባባት ያልተደረሰበት በእልህ የሚካሄደው ጉባኤን እንደሚቃወምም የገለጸው የቁጥጥር ኮሚሽኑ ፤ ” ጉባኤው ተከትሎ በትግራይ ህዝብና በህወሓት የሚፈጠረው አደጋ ተጠያቂው በማንአለበኝነትና በእኔነት ስሜት በመጓዝ ላይ ያለው ቡድን ነው ” ብሏል።
” በህወሓት የተፈጠረው ችግር መፍትሄው የቡድን ፉክክር ፣ እኔነትና እልህ አይደለም ” ያለው ኮሚሽኑ ” ደርጅቱ የሚድነው በስርአታዊና ተቋማዊ ትግል ነው ” ሲል ገልጿል።
በሌላ በኩል የህወሓት የፅ/ቤት ሃላፊና የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ብሄር ትላንት የህወሓት ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት በጉባኤ እንዲሳተፉ በፃፉት ደብዳቤ ” 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ነሃሴ 7/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 3:00 ጀምሮ በመቐለ የሰማእታት ሓወልት አዳራሽ ይካሄዳል ” ብለዋል።
ኮሚሽኑ ግን ራሱን ከጉባኤው አግልሏል። ዛሬ ከጥዋት ጀምሮ ደግሞ ህወሓት በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ነገ ለሚጀምረው ጉባኤ ተሳታፊ የሆኑ አባላት ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ መቐለ እየተጓዙ እንደሆኑ እያሳወቀ ነው።
ቀደም ሲል ” ህወሓትን ለማፍረስ አልሞ በሚካሄደው ጉባኤ አንሳተፍም !! ” ሲሉ የትህነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ፊርማቸውን አኑረው መግለጫ ማሰራጨታቸው ይታወሳል።
” ህወሓትን ለማፍረስ አልሞ በሚካሄደው ጉባኤ አንሳተፍም ” ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ” ጉባኤውን ተከትሎ ለሚመጣው ነገር እኛ የለንበትም ” ሲሉ አስቀድመው አስጠንቅቀዋል።
በጥቂት ቡድኖች ማን አለበኝነት ” የተዘጋጀ ፣የጉባኤው ከፍተኛ ስልጣን ያለው የማእከላዊ ኮሚቴ አመራር ያልወሰነው ፣የድርጅቱ የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ውድቅ ያደረገው ፣ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ መግባባት ያልተደረሰበትና ፣ትግራይ ከጫፍ አስከ ጫፍ ያልተወከለበት፤ ነጻ ያልወጡ አካባቢዎች ባሉበት ሁኔታ የሚካሄድ ነው ሲል አመልክተዋል። ” ጉባኤው የጠባብ ቡድን ጥቅም ለማስከበር ብቻ ያለመ ነው ፤ እኛ ደግሞ በዚህ ላይ አንሳተፍም ” ብለዋል።
” ህወሓትን እና የትግራይ ህዝብ ወደ ከፋ አደጋ የሚያጋልጥ ያልተረጋጋ ጉባኤ ማካሄድ የጠባብ ቡድኑ ጥቅምን ከማረጋገጥ ያለፈ እርባና የለውም ” ሲሉም ገልጸዋል። ይህ ተጠያቂነትን በስልጣን ሸፍኖ ለማለፍ የሚደረግ እንደሆነም ተደጋግሞ ሲገለስ ነበር።
14ቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ” ህወሓትን እና የትግራይ ህዝብ ወደ ሌላ የተወሳሰበ ቀውስ በሚከት በጠባብ ቡድን የተዘጋጀው ጉባኤ አንሳተም ” ብለው ” ጉባኤውን ተከትሎ ለሚፈጠረው ማንኛውም ነገር ተጠያቂው ይኸው ቡድን መሆኑ እናስታውቃለን ” ብለዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ ያሉበት 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ” ጠባብ ቡድን ” እያሉ የገለጻቸውን ጥቂት ቡድኖች በስም አልገለጿቸውም። ፊርማ አኑረው ካሰራጩት ደብዳቤ የተገኘው ዝርዝራቸው ከስር ያለው ነው
- ጌታቸው ረዳ
- በየነ ምክሩ
- ክንደያ ገ/ህይወት
- ሓጎስ ጎዶፋይ
- ሰብለ ካህሣይ
- ብርሃነ ገ/የሱስ
- ሰለሞን መዓሾ
- ሺሻይ መረሳ
- ሃፍቱ ኪሮስ
- ረዳኢ ሓለፎም
- ነጋ ኣሰፋ
- ገ/ሕይወት ገ/ሄር
- ሩፋኤል ሽፋረ
- ርስቁ ኣለማው ናቸው። ሲሆኑ ከዚህም በተጨማሪ
በሌላ ተመሳሳይ የመገለል ዜና ሰባት የመቐለ ከተማና ሁለት የትግራይ ማእከላዊ ዞን ከፍተኛ ካድሬዎች ” ጠባብ ቡድን ” ሲሉ በጠሩ አካል ተጠርቷል ባሉት የህወሓት ጉባኤ እንደማይሳተፉ አስታወቁ። አመራሮቹ ” ባሁኑ ወቅት የሚካሄደው ጉባኤ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን ላለመሳተፍ ወስነናል ” ብለዋል። በጉባኤው እንዳማይሳተፉ በደብዳቤ ያስታወቁ የህወሓት ከፍተኛ ካድሬዎች
ሓጎስ ንጉስ – የዓዴት ወረዳ የአደረጃጀት ሃላፊ ናቸው።
ነጋሽ ኣርኣያ – የመቐለ ጀተማ የህወሓት ፅህፈት ቤት ሃላፊ
ሓለፎም ገ/ህይወት – የሓድነት ክፍለ ከተማ ዋና አስተዳዳሪ (መቐለ)
ኤልያስ ኪሮስ – የዓዲ ሓቂ ክፍለ ከተማ ዋና አስተዳዳሪ (መቐለ)
እያሱ ተካ – የዓይደር ከፍለ ከተማ ዋና አስተዳዳሪ (መቐለ)
ኣስመላሽ ብርሃኑ – የዓዲ ክፍለ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ (መቐለ)
ፍጹም ለገሰን – በትግራይ ማእከላዊ ዞን የዓዴት ወረዳ አስተዳዳሪ
ዜናው ከትህነግ መህበራዊ አውዶች፣ ቲክቫህን ጨምሮ ከተለያዩ መገናኛዎች ተወስዶ የተጠናከረ ነው