በፓሪሱ ኦሊምፒክ የተሰተፉ በነበረበት ወቅት በአበሻ ሬስቶራንት ምግብ ሲመገቡና ሲነጋገሩ በድብቅ ሳያሳውቃቸውና ለሚዲያ ያሰራጨው ያኮረፈ የአትሌ ማናጀር መሆኑ ተሰማ።
የተቀረጸው ድምጽ ከጠዋት ውድድር በሁዋላ ተሰብስበው አበሻ ምግብ ቤት ምግብ ሲበሉ እንደነበር ያስታወቁት የኢትዮ ሪቪው የመረጃ ሰዎች፣ ሲመገቡ የተቀመጡት በግሩፕ ሶስት ጠረጴዛ ላይ እንደነበር አመልክተዋል።
የተቀረጸው ድምጽ ብቻ ሲሆን የቀረጸው የአትሌት ደርቤ ወልተጂ፣ ፍሬወይኒ ሃይሉና እጅጋየሁ ታዬ ማጄር አቶ ዮናስ መኮንን እንደሆነ በማስረጃ መረጋገጡን የዜናው ባለቤቶች አመልክተዋል።
ፍሬወይኒ ባለመወዳደሯ ቅር የተሰኘው ዮናስ በተቀረጸው ድምጽ ውስጥ ድምጹ ከሌሎች ሁሉ ንጹህ ሆኖ መሰማቱ፣ ደራርቱ ዮኒ እየለች ስትጠራውን ምልልስ ሲያደርጉ፣ በተለይም ለብቻው ስታነጋግረው የሌሎች ድምጽ መጥፋቱ፣ ገዛኸኝ ሲመጣ ደራቱ ስትነሳና ልትቀበለው ከዮናስ ስትርቅ ድምጿ እያነሰ መሄዱን የታዘቡ አስቀድመውም ጠርጥረው እንደነበር ከዜናው ሰዎች ለመረዳት ተችሏል።
ጠዋት ላይ የተካሄደው ውድድር ካለቀ በሁዋላ ምስ በልተው ለተሲያት ውድድር ወደ ስታዲየም መመለሳቸውን ያስታወቁትና በስፍራው የነበሩ እንዳሉት በወቅቱ ምንም ከውሃና ከለስላሳ መጠጦች ውጪ የቀረበ አንዳችም መጠጥ እንዳልነበር ገልጸዋል።
አትሌት ጉደፋይ ፀጋዬ የተሻለ ሰዓት ሶላላት፣ አሰለጣኝዋና የትዳር ጓደኛዋ ባሉዋት ሶስት ውድድሮች እንድትወዳደር ካልተፈቀደላት በስተርቀር በሁሉም ውድድሮች እንደማትሮጥ አቋም በመያዙ ሳቢያ ፍሬውይኒ በ1500 ሜትር መወዳደር አለመቻሏ ያናደደው ዮናስ ድምጽ በድብቅ ቀርጾ ለሚድያ መስጠቱን በተለያዩ የቴክኖሎጂ ድጋፎች ማረጋገጣቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል።
የአትሌት ጉደፋይ ፀጋዬ ባለቤትና አስለጣኝ በሶስት ውድድር አሸናፊነት የተሻለ ገንዝብ ለመሰብሰብ የያዘው አቋም ፌዴሬሽኑን በስፋት ማስወቀሱ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ጉደፋይ በርቀቱ ከፍሬወይኒ ይልቅ የተሻለ ሰዓት ስላላትና አንድ አትሌት መስፈርቱን ካሟላ ሶስት ሩጫ የመሮጥ የህግ ድጋፍ ስላለው መፈቀዱን አመልክቷል።
የጉደፋይ ባለቤት በማስልጠን ልምድም ሆነ ከአንደኛ ደረጃ መሰረታዊ ስልጠና ሰሚናር የዘለለ ትምህርት እንደሌለው የሚያውቁ ይህ ስህተት የተፈጸመው በየርቀቱ ነባር አሰልጣኞች ባለመኖራቸውና ብሄራዊ ቡድን የሚባለው ጥብቅ አሰራር በመፍረሱ ሳቢያ እንደሆነ ተናግረዋል። እንደቀድሞው ሃላፊነት ወስዶ የሚወስን አሰልጣኝ ባለመኖሩ አቅም የሌላቸው በግል አትሌቶችን ተቀራምተው ውጤቱ ላይ ጫና ማሳደራቸው በስፋት የተገለጸ ጉዳይ ነው።
ዮናስ መኮንን በድብቅ የቀረጸው ድምጽ በሚዲያ ትንተና እየተሰጠበት መቅረቡ ይታወሳል። ይህን አስመልክቶ ስማቸው የተነሳውን አካላት ለማነጋገር ሞክረን አልተሳካልንም። በስፍራው የነበሩ አንድ ባለሙያ “በወቅቱ በግሩፕ ሆነው ምሳ ከመብላታቸውና ወደ ውድድር ከመመለሳቸው ውጭ መጠጥም ሆነ ማናቸውን ነገሮች እንዳልነበሩ ማረጋገጥ እችላለሁ ብለዋል” ሰዎችን ስያውቁና ፈቃዳቸውን ሳይሰጡ በፊልምም ሆነ በፍምጽ ቀርጾ ለሚዲያ ፍጆታ ማዋል ወንጀል መሆኑ ይታወሳል። ጉዳዩ ወንጀል ቢሆንም ተበዳዮች ምን አቋም እንደያዙ ለጊዜው አልታወቀም።
ዮናስ መኮንን ይገኝበታል በተባለ ስልክ በተደጋጋሚ በአዲስ አበባ ተባባሪያችን በኩል ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። አስተያየት ካለው ለማስተናገድ ዝግጅት ክፍሉ በሩ ክፍት ነው።