አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍላችን በፊንጢጣ አካባቢ የሚከሰቱ የጤና እክሎችን በሙሉ የኪንታሮት ህመም ነው ብሎ ችላ በማለት ወይም በባህላዊ ህክምና ራሳቸውን በማከም ከቆዩ በኋላ ህመማቸው ለውጥ ሳይኖረው ሲቀር እና ስር ሲሰድ ወደ ጤና ተቋም ይመጣሉ።
– እዚጋር ማስተዋል ያለባቹ ነገር የፊንጢጣ አካባቢ ህመም ሁሉ የኪንታሮት ህመም አይደለም። በዋነኝነት በፊንጢጣ አካባቢ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ በሽታዎች
1. የፊንጢጣ ኪንታሮት በሽታ
ምልክቶቹ
✔ ሕመም የሌለው ከፊንጢጣ የሚፈስ ደማቅ ቀይ ደም መኖር
✔ ከፊንጢጣ የሚወጣ ሽታ ያለው ወይም የሌለው ፈሳሽ
✔ በፊንጢጣ አካባቢ ማሳከክ
✔ ከፊንጢጣ የወጣ ሥጋ መሳይ እባጭ
✔ በፊንጢጣ አካባቢ የህመም ስሜት መኖር
✔ ሰገራ ወቶ ከጨረሱ በኋላ ሰገራ ያለ የሚመስል ስሜት መኖር
2. የፊንጢጣ ስንጥቃት
ምልክቶቹ
✔ ሰገራ በሚወጣ ጊዜ ፊንጢጣ ላይ የመቀደድ ወይም በቢላ የመቆረጥ አይነት ስሜት ያለው ህመም መኖር
✔ ሰገራ ከወጣ በኋላ ለደቂቃዎች ወይም ለሰአታት የሚቆይ ቀነስ ያለ የማቃጠል ስሜት መኖር
✔ ከሰገራ ጋር ወይም ሰገራ ከወጣ በኋላ የፊንጢጣ መድማት
✔ በዚህ ምክንያት ሰገራ ለመውጣት መፍራትና ለሰገራ ድርቀት መጋለጥ
3. የፊንጢጣ አካባቢ መግል መቋጠር
ምልክቶቹ
✔ ፊንጢጣ ሲነካም ሳይነካም የሚያም ለመቀመጥ የማያስችል እየጨመረ የሚሄድ እብጠት መኖር
✔ ሰገራ ሲወጣ ህመም መኖር
✔ ተያይዞ ትኩሳት እና ብርድ ብርድ ማለት መኖር
✔ አንዳንዴ በራሱ ከፈነዳ ደም የቀላቀለ መግል መፍሰስ
4. የፊንጢጣ አካባቢ ፊስቱላ (ጤናማ ያልሆነ ክፍተት)
ምልክቶቹ
✔ የማያቋርጥ ከፊንጢጣ አካባቢ የሚፈስ ሽታ ያለው ፈሳሽ መኖር
✔ ከዚ በፊት ፊንጢጣ አካባቢ የነበረ መግል መቋጠር በቀዶ ህክምና ወይም በራሱ ፈንድቶ ከነበር
✔ በፊንጢጣ አካባቢ ማሳከክ ወይም ህመም መኖር
✔ ትንሽ ጠጠር ያለ ፊንጢጣ አካባቢ እብጠት መኖር
5. የፊንጢጣ ካንሰር
ምልክቶቹ
✔ በፊንጢጣ ደም መፍሰስ ወይም ደም የቀላቀለ ሰገራ መውጣት
✔ የሰገራ ከሌላው ጊዜ በተለየ መቀያየር ማለትም የሰገራ በቀጭኑ መውጣት እንዲሁም አልፎ አልፎ የሰገራ ድርቀት መኖር
✔ የሰውነት ክብደት መቀነስ የምግብ ፍላጎት መቀነስ እንዲሁም ምንም ሳይሰሩ የድካም ስሜት መኖር
✔ የፊንጢጣ አካባቢ እብጠት እና መኖር
✔ የፊንጢጣ አካባቢ ህመም ወይም ማሳከክ
✔ ሰገራ ለመቆጣጠር መቸገር
6. የታችኛው ትልቁ አንጀት በፊንጢጣ በኩል መገልበጥ
ምልክቶቹ
✔ ከፊንጢጣ ውስጥ የሚወጣ ስጋ የሚመስል በራሱ ወይም በጣት ተገፍቶ የሚመለስ እብጠት ወይም ከከፋ በጣትም የማይመለስ እብጠት መኖር
✔ የፊንጢጣ ህመም እና ማሳከክ መኖር
✔ ከፊንጢጣ የሚወጣ ፈሳሽ መኖር
✔ ሰገራ ለማውጣት እንዲሁም ለመጨረስ ማማጥ አንዳንዴ በጣት ሰገራ አውጥቶ መጨረስ
7. የአነጀት ጥገኛ ትላትል
ምልክቶቹ
✔ የፊንጢጣ ላይ ህመም
✔ በተለይ ማታ ማታ ላይ የሚብስ የፊንጢጣ ማሳከክ እና እንቅልፍ ለመተኛት መቸገር
✔ ሰገራ ሲወጣ የፊንጢጣ ህመም መኖር
✔ ሰገራ ላይ ትላትል ማየት
✔️ እነዚሀ የጠቀስኳቸው የፊንጢጣ አካባቢ የጤና እክሎች የሚያሳዩት ምልክቶች ከፊንጢጣ ኪንታሮት ጋር ተመሳሳይነት ስላላቸው ህመሙ በጤና ባለሞያ ካልተመረመረ በስተቀር በሽታውን መለየት አይቻልም።
✔️ በተጨማሪ የበሽታዎቹ ባህሪ እና ህክምናቸው ፈፅሞ የተለያየ ስለሆነ በቤት ውስጥም ሆነ በባህላዊ መንገድ የፊንጢጣ ኪንታሮት ነው ብላቹ እየታከማቹ ያላቹ ሰዎች ካላቹ በጊዜ ወደ ጤና ተቋም ሄዳቹ ብትመረመሩ በቀላሉ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ማግኘት ትችላላቹ።
Reference
☑️ Gordon and Nivatvongs’ Principles and Practice of Surgery for the Colon, Rectum, and Anus
☑️ Schwartz’s Principles of Surgery Eleventh Edition
☑️ UptoDate
በዶ/ር ዮናታን ከተማ: – በቅዱስ ፓውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህፃናት ቀዶ ህክምና ሬዚደንት ሐኪም
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring