የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የታዳጊዋን ሄቨን አዎት አሰቃቂ ህልፈተ ህይወት አስመልክቶ ያስተላለፈው መልዕክት!
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር በታዳጊዋ ሄቨን አሰቃቂ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን አሁንም በድጋሜ ይገልጿል።
ከተማ ዳግማዊ ሚኒልክ ክፍለ ከተማ በ7 ዓመቷ ታዳጊ ህጻን ሄቨን ላይ በተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊትና ህልፈተ ህይወት በእጅጉ ማዘኑን ገልፆ የነበረ መሆኑ ይታወሳል።
በህጻናት ላይ የሚፈጸምን ማንኛውም ጥቃት መከላከል በዋነኛነት የመንግሥት ኀላፊነት ሲሆን በሌላ በኩል የሁሉም አካል ተመሳሳይ ድርሻ ያለው መሆኑን እያስገነዝብን ከተማ አሥተዳደሩ እንደዚህ አይነት አስነዋሪና አሳፋሪ ድርጊት በከተማችን በመፈፀሙ በእጅጉ ዛሬም በድጋሜ አዝነናል።
የባሕር ዳር ከተማ ሕዝብ ሰው ወዳድ፣ ሁሉን አክባሪ፣ ባህሉን፣ ወጉንና ታሪኩን ጠባቂ አስተዋይ ጨዋ ሕዝብ ነው ። በዚህ እሴትና ባህል በተገነባ ማኅበረሰብ ውስጥ የተፈፀመው ድርጊት በፍፁም ነውረኛና የከተማውን ሕዝብ የማይገልፅ ሁሉም ሰው ሊያወግዘው የሚገባ ዘግናኝ ተግባር ነው።
ሁሉም እንደሚያስታዉሰዉ ወንጀሉ እንደተፈፀመ የከተማ አሥተዳደሩ የሚመለታቸው ተቋማት በዋነኝነትም ከፖሊስ፣ ከጤና ተቋም ፣ ከፍትሕ እንዲሁም ከተበዳይ ወገኖች ጋር በመቀናጀት ጉዳዩ በሕግ እንዲያዝ በማድረግ ልዩ ትኩረትና ክትትል በማድረግ ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ ተይዞ በ20/06/2016 ዓ.ም በከፍተኛ ፍርድ ቤት የ25 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበት ባሕርዳር ማረሚያ ቤት እንዲገባ ተደርጓል።
በዚህ አጋጣሚ ከተማ አሥተዳደሩ የፍርድ ቤቱን የዳኝነት ነፃነት የሚያከብር ቢሆንም ከተፈፀመው ዘግናኝ ድርጊትና የማኅበረሰቡን ሞራልና ክብር ዝቅ ያደረገ ወጀል በፈፀመው ወንጀለኛ ላይ የተሰጠው ፍርድ አስተማሪነት የሚያንሰው መሆኑን አሥተዳደሩ በፅኑ ያምናል።
ከተማ አሥተዳደሩ ጉዳን በጥብቅ ለመከታተል ባለው ፅኑ አቋም ክልሉን ባጋጠመው ቀውስ ወንጀለኛው ከማረሚያ ቤት አምልጦ የወጣ መሆኑን እንዳወቀ በልዩ ሁኔታ የፀጥታ ኀይሉ ክትትል እንዲያደርግ ዓመራር ተሰጦ ወንጀለኛው ተይዞ ድጋሜ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲገባ ተደርጓል።
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በአሁኑ ወቅት ወንጀለኛው ይግባኝ የጠየቀ እንደሆነ እና ጉዳዩ ለጥቅምት 20/2017 ዓ.ም ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ የሰጠ መሆኑን የከተማ አሥተዳደሩ ያውቃል። የፍርድ ቤቱን ነጻነት በጠበቀ መልኩ ከሕግ አኳያ የይግባኙን ሁኔታ በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በትኩረት የምንከታተለው እና ፍትሕ እንዲረጋገጥ በፅናት የምንታገል እንደሆነ ለማረጋገጥ እንወዳለን።
ከተማ አሥተዳደሩ በልጃችን ህፃን ሄቨን ለደረሰው ግፍ ፍትህ ሲጠይቅ፣ ለጉዳዩ ለሰጠው ትኩረት እና እያደረገ ላለው ትግል ለመላው የሕብረተሰብ ክፍል ምስጋና እያቀረብን በቀጣይም ለፍትሕ መረጋገጥ ለምናደርገው ትግል ሕብረተሰቡ ከጎናችን እንዲይለይ ጥሪያችን እያቀረብን በቀጣይም የህፃናት ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ስለሆነ በትብብር መሥራት ይጠበቅብናል።
ነሐሴ 12/2016 ዓ.ም
ባሕር ዳር
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring