ቀነኒሳ ይህን ካለ በሁዋላ “በፌዴሬሽኑ ውስጥ አትሌቶች ምርጫ ፆታዊ ፍላጎትን ማስፈፀሚያ እየሆነ ነው፤ፆታዊ ትንኮሳም አለ” በሚል የችግሩን ሰንኮፍና ሁሉም ሳይደፍሩ የሚዘሉትን ጉዳይ ገሃድ አውጥቷል። አያይዞም “ጉዳዩ መፅዳት አለበት
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ንግስናውን ማንም የማይገዳደረው ቀነኒሳ በቀለ ብዙም ለሚዲያ ክፍት አይደለም። ቀነኒሳ በሚያውቀውም በማያውቀውም ራሱን አዋቂ አድርጎ ሲዘላብድ አይሰማም። የእውቅና ካባቸውን ተጠቅመው ጫና ለማሳረፍ ሲሞክር የማይደመጠው ቀነኒሳ በፓሪስ የኦሊምፒክ ውድድር ጉዳይ ተጠይቆ አስተያየት ሲሰጥ በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ የጾታ ጥቃት እንደሚፈጸም ማስታወቁ መነጋገሪያ ሆኗል።
በአገር አቋርጭ፣ የትራክ፣ በኢንዶርስ ውድድሮች ተፎካካሪዎን አገርና ቦታ ሳይለይ አረፋ እያስደፈቀ የሚዘርረው ቀነኒሳ በቀለ አሁን ደግሞ በማራቶን ኢትዮጵያን ወክሎ በፓሪስ ከሚንሳፈፉት የኢትዮጵያ ፈርጦች መካከል አንዱ ነው።
በትራክ ውድድር ሲንሳፈፍ “እንደ አቡሸማኔ ይወረወራል” የሚባለው ቀነኒሳ በቀለ ውድድር በመጣ ቁጥር አለመግባባት የሚታይበት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአትሌቶች ምርጫ ውስጥ ወገንተኝነት እና ፆታዊ ትንኮሳ እንዳለ ያስታወቀው በሸገር ኤፍ ኤም በኩል ውድድሩን አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄ መልስ ሲሰጥ ነው።
ውድድር ሊያልቅ ሶቃረብ የሚቦርቀው ቀነኒሳ በአንድ ኦሊምፒክ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ ያጠለቀና አገራቸውን ከልብ የሚወዱ በሃሴት እንዲያነብይ ያደርገው ባለ ደማቅ ታሪኩ ቀነኒሳ፣ አትለቶች ላይ የጾታ ጥቃት እንደሚደርስ ገልጾ መናገሩን ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ አድነቀዋል። ሃላፊነት መውሰድ እንደሚገባው አትሌት በገሃድ ይህን ከባድና ክብረ ነክ ጉዳይ ማንሳቱን አወድሰዋል። ኦሊምፒክ ሲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚናገሩ ከዝግጅት ክፍላችን አመልክተዋል።
በአትሌቲክስ ህይወቱ ሶስት የኦሎምፒክ ፣ አምስት የአለም ሻምፒዮና እንዲሁም አስራ አንድ የአለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ወርቅ ሜዳልያ እና ሌሎች ድሎች ባለቤት የሆነው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከሸገር ስፖርት ጋር በነበረው ቆይታ እንደተናገረው፤አትሌቶች ምርጫ ላይ የሚስተዋለው ጭቅጭቅ፤ወጥ የሆነ ህግ ባለመቀመጡ የመጣ እንደሆነ አመልክቷል። የምርቻው ህግ በስርዓት ቢሆን ሁሉም አትሌት ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉና ውዝግብ ሊቆም እንደሚችል አመልክቷል።
ከፌዴሬሽኑ አመራሮች ለይቶ ሻለቃ ደራርቱ ቱሉን በማንሳት ጥፋት እንዳላየባት ያመልከተው ቀነኒሲ፣ በሌሎቹ የፌዴሬሽኑ አመራሮች ላይ ግን በእርግጠኛነት ይህ ነው ብሎ የሰጠው አስተያየት የለም።
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ ባለው የአሰራር ችግር ሳቢያ ወገንተኝነት ፣ ቅርርብ ፣ በግል ፀብ ምክንያት አትሌቶች እንዳይመረጡ ማድረግ በተደጋጋሚ የሚታይ ጉዳይ እንደሆነ ገልጿል።
ቀነኒሳ ይህን ካለ በሁዋላ “በፌዴሬሽኑ ውስጥ አትሌቶች ምርጫ ፆታዊ ፍላጎትን ማስፈፀሚያ እየሆነ ነው፤ፆታዊ ትንኮሳም አለ” በሚል የችግሩን ሰንኮፍና ሁሉም ሳይደፍሩ የሚዘሉትን ጉዳይ ገሃድ አውጥቷል። አያይዞም “ጉዳዩ መፅዳት አለበት” ሲል አሳስቧል።
ይህንኑ ተከትሎ ዝግጅት ክፍላችንን ያገኙ ቀደምት አትሌቶችና ተቀራራቢ ስራ የሚሰሩ የአትሌቶች ወዳጆች ከጉቦ፣ ኮሚሽንና ከጉዞ ጋር የተያያዙ ሌብነቶች አካተው አትሌቶች ላይ የሚደርሰውን ጾታ ላይ የተመረኮዛ ችግር ይፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
” አሁን ኦሊምፒክ ነው ይለፈን” ያሉት እነዚሁ ወገኖች “ችግሩን ደራርቱ ጨምሮ ሁሉም ያውቁታል። ቀነኒሳ ጀምሮታል። እኛ የምናውቀውን እንናገራለን። አዲሷ የስፖርት ሚኒስትር ሴት እንደመሆናቸው ለጉዳዩ ትኩረት ይሰታሉ ብለን እናምናለን” ብለዋል።
ቀኒሳ ብቃትን አስመልክቶ ሲናገር “በፌዴሬሽኑ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት አትሌቶች አይምሩ አይባልም ነገርግን የተማሩ ሰዎችንም በማምጣት እና በመተጋገዝ እንዲሁም ህጎችን በማስተካከል መስራት ያስፈልጋል ሲል” ሃሳብ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በህክምና፣ በቴክኒክም ሆነ በድጋፍ ሰጪነት የከበቡት ወገኖች ማንንም የማይስተጉ፣ ጡረታ የማያውቃቸው፣ አዳዲስ ሰዎችን የሚገፉና ዙሪያው የተከተረ ቤት አድርገው የያዙት ውስን ሰዎች እንደሆኑ ተደጋግሞ በዚሁ ገጽ መገለጹ ይታወሳል።
በኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በማራቶን የሚወክለው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ውድድሩንና ወቅታዊ አቋሙን አስመልክቶ ጥሩ ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል። “በራሴ እተማመናለሁ ፤ የተቻለኝን አድርጌ ለሀገሬም ለራሴም ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ እፈልጋለሁ” ብሏል።
ቴዲ አፍሮ ” ሮጪ ላሯሩጣቸው” በሚል ዜማ ለሃሳቡ ባለቤት ሪፖርተር ጋዜጣ የወቅቱ ዘጋቢ እውቅና ሳይሰጥ የተቀኘበት የቤጂንግ ኦሊምፒክ ቀነኒሳና ስለሺ የሰሩት ስራ የሚታወስ ነው። ሃይሌ አስቀድሞ ከሪፖርተር የወቅቱ የስፖርት አዘጋጅና የአሁኑ የዚህ ሚዲያ ባለቤት “የምሄደው ሮጪ ላሯሩጣቸው ነው” እንዳለው ውድድሩን አክርሮ ተፎካካሪዎችን ካቃጠላቸው በሁዋላ ማተናቀቂያው ሲቃረብ ደከመ። ዘርዘናይ ከነሱ ጋር ነበርና ሊሄድ ሆነ። ቀነኒሳ ዘረሰናይን እየገረመመ በጥብቅ ቁጥጥር ስር አውሎ ሃይሌን ፍለጋ ይዞር ጀመር። ስለሺም ሃይሌን ፍለጋ እየዞረ ዓይኑንን አንከራተተ። ሁለቱም እየዞሩ ሃይሌን የመጎተት ያህል ዋተቱ።
ሃይሌ ቀጭኑ እግሩ የቀድሞውን ምትሃታቸውን አንሰጥም ብለውት ህመም ላይ ነበር። ከህመሙ ሙሉ በሙሉ አላገገመምና አልቻለም። ይህን ሲያረጋግጡ ስለሺና ቀነኒሳ ተያዘው መንሳፈፍ ጀመሩ። ሊሾልክ አኮብኩቦ የነንበረውን ዘረሰናይን አራገፉት። ተፎካካሪያቸውን በሙሉ ካጸዱ በሁዋላ በሚገርም ፍጥነት ለወርቅ መፋለም ጀመሩ። እንደተለመደው ቀነኒሳ ማብቂያው ላይ አቡሸማኔ ሆነ። ተከታትለው ወርቅና ብር አስገኙ። ሃይሌ ሚዳሊያ ሳያገኝ ቀረ። ግን ተቃቅፈው አንድ ሆኑ። ይህ ህብረት አይረሳም።