ፕሮፌሰሩ ‹‹ በልጅነቴ በጣም የታደልኩ ነበርኩ፡፡ ሶስት ቤተሰቦች ናቸው ያሳደጉኝ ማለት እችላለው ይላሉ ›› በገዛ አንደበታቸው ስለ ራሳቸው ሲናገሩ፡፡ የፕሮፌሰሩ ታሪክ ከዚህ ይጀምራል፡፡
የዛሬው ፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴ ከወላጅ እናታቸው መንበረ ገብረ ማርያም እና ከወላጅ አባታቸው ከእሸቴ ተሰማ ተወልደው በመሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ልጅነታቸውን አሳልፈዋል፡፡
ከእናት እና አባታቸው በመቀጠል ያሳደጓቸው አጎታቸው ጀማነው አላብሰው ወጣትነታቸውን ደግሞ በፓንክረስት ቤተሰቦች ውስጥ እንደ ልጅ በመሆን ትምህርታቸውን እየተከታተሉ በእንክብካቤና በንባብ ራሳቸውን በእውቀትና በልምድ ማጎልበት ችለዋል፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ የዘመናዊ ትምህርት ቤት ፋናወጊ በመሆን በሚጠቀሰው ዳግማዊ ምንሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት ህይወታቸውን ብለው የጀመሩት የያኔው አንድሪያስ እሸቴ በዊልያምስ ኮሌጅ ትምህርታቸውን ተከታትለው ከየል ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን እስካገኙበት ጊዜ ድረስ ሰፊ የንባብ ልምድና የፍልስፍና ሕይወት ውስጥ አልፈው ከሀገር ውጪ በተለያዩ ቦታዎች ከሰሩና በበርካታ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ካስተማሩ በኋላ ወደ ሀገር ውስጥ በመመለስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት በመሆን አገልግለው ቀጥለውም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ አማካሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡ በ1995ዓም የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ሲረቅም በአባልነት የራሳቸውን ሚና አበርክተዋል፡፡
ፕሮፌሰሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት በነበሩበት ወቅት በርካታ ለትውልድ የሚሻገሩ ስራዎችን የሰሩ ሲሆን በፕሬዘዳንትነት ጊዜያቸው ካበረከቷቸው አስተዋፅኦ መካከል በፖሊሲ ደረጃ ውሳኔን በማሳለፍ ዓይነስውራን በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ገብተው ትምህርታቸውን መከታተል እንዲችሉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ምሁር እንደሆኑ ይጠቀሳሉ፡፡ በጋይዳንስ እና ካውንሲሊንግ ስር የነበረውን ለብቻው በማውጣትና ቦታ ሰጥቶ ህንፃ በማሰራት የመጀመርያውን የአካል ጉዳተኞች ተማሪዎች ማዕከል ወይም ( የልዩ ፍላጎት ድጋፍ ማዕከል) ያቀዋቀዋሙት ፕሮፌሰሩ ናቸው፡፡
ለብቻው ሞደርን አርት ሙዚየም በመባል የገብረ ክርስቶስ ስራዎች አሁን ባሉበት መልኩ ተለይተው እንዲቀመጡና እንዲጎበኙ ተያይዞም ጥናትና ምርምር እንዲሰራባቸው አስደርገዋል፡፡ እንዲሁም ከሰባ ዓመታት በላይ ባስቆጠረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲው ታሪክ ውስጥ የመጀመርያዋ ሴት ምክትል ፕሬዘዳንት የዛሬዋ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደ ማርያም የተሾመችው በዚሁ ጊዜ ነው፡፡ በርካታ በፒኤችዲ ደረጃ አዳዲስ የትምህርት ዘርፎች እንዲከፈቱ አበርክቷቸው ይነሳል፡፡
ኢትዮጵያ የመጀመርያዋን የሴት ፕሮፌሰር፡ ፕሮፌሰር የዓለምፀሀይ መኮንን ያገኘችው በዚሁ በፕሮፌሰሩ የፕሬዘዳንትነት ጊዜ ነበር፡፡ በዕለቱም በሽልማት ሁሉ በማበረታታት በደስታ ብዛት ዕንባ ተናንቋቸው ነበር ይላሉ በዕለቱ በመድረኩ የታደሙ ታዳሚዎች ሲመሰክሩ፡፡
ሴቶችን ከማብቃት ጋር ስማቸው በተደጋጋሚ ተያይዞ ይነሳል፡፡ በተጨማሪም በፕሬዘዳንትነት ዘመናቸው ከሰሯቸው ስራዎች ሌላው ከትምህርት ክፍሉ ወጥተው ሙዚቃ፡ቴአትርና ስዕል አንድ ላይ በመሆን ራሳቸውን ችለው እንደ ኮሌጅ ቢቋቋሙ በማለት የተለያዩ ምሁራንን በመጋበዝ ኮሌጁን በእግሩ እንዲቆም ሲያደርጉ ለቴአትር ትምህርት ቤት ታላቁን አዘጋጅ አባተ መኩርያን ወደ ዩኒቨርሲቲው በማምጣት አዲሱ ትውልድ ልምዱን እና እውቀቱን እንዲቀስም ያደረገውም ይኸው ፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴ ነው ይላል ታሪካቸው፡፡
አንድሪያስ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በዋነኝነት በህግ ፍልስፍና ዙርያ ከፍተኛ የራሱን አስተዋፅኦ በማድረግ በርካታ የህትመት ውጤቶችን ከማሳተም ባለፈ ህግና አዋጅ በማርቀቅና የፖሊሲ ማሻሻያ በማድረግ ለሀገርም ሆነ ለአፍሪካ የራሱን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረግ የቻለ ፈላስፋ ነው ይሉታል ሌሎች የሀገራችን ምሁራን ሲገልፁት፡፡
አንድሪያስ ገና በወጣትነቱ በመጀመርያ ያሳተመው ሪቻርድ ፓንክረስት በሚያሳትሙት ‘’ Ethiopia observer ‘’ የተሰኘው መፅሔት ላይ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ብዙም ያልተወራለት የኢትዮጵያ የመረዳጃ ሀብቶች ስለሆኑት ስለ እድር፤ እቁብ እና ማህበራት ዙርያ ከሪቻርድ ፓንክረስት ጋር በመሆን ‘’ self-help in Ethiopia “ በሚል ርዕሰ አርቲክል በመፃፍ ባህላችን ከሌላው ዓለም ጋርም ምን ዓይነት መስተጋብር እንዳለው በመዳሰስ እና በመዘርዘር በተጨማሪም አገር በቀል እውቀትና ባህልን አጉልቶ በማሳየት አንድሪያስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ነበራቸው፡፡
አንድሪያስ በስራ ዘመናቸው በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓለም ዓቀፍ የስራ ተሞክሯቸው በዩኔስኮ የሰብአዊ መብት፣ የሰላም እና የዲሞክራሲ ሊቀ-መንበር በመሆን አገልግለዋል፡፡ ብራውን ዩሲኤልኤ፡ዩሲ-በርክሌይ እና ፔን በማስተማር ያገለገለባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡
በአሜሪካን ሀገር በነበሩበት ወቅት በሰበዓዊ መብቶች ንቅናቄ ላይ ንቁ ተሳታፊ ነበሩና በብላክ ፓንተር ፓርቲ ውስጥም ተሳትፎ የነበራቸው ምሁር ነበሩ፡፡ በሞራል እና ፖለቲካዊ ፍልስፍናዎች እንዲሁም ስነ-ምግባር ላይ ያተኮሩ የድርሰት ውጤቶችን በበርካታ መንገዶች ለህትመት አብቅቷል፡፡ ከፍልስፍና ባሻገር ስለ ኢትዮጵያ አጫጭርም ሆነ ረጃጅም አርቲክሎችን በተለያየ ወቅት አስነብቦናል፡፡
ፕሮፌሰሩ በሙሉ ጊዜያቸው ተምረዋል፡ አስተምረዋል፡ ተፈላስፈዋል፡፡ አንድሪያስ እሸቴ በአስተማሪነት ካገለገለባቸው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በአሜሪካን ሀገር በሚገኘው ብራውን ዩኒቨርሲቲ፡ ዩሲኤልኤ፤በርክሊን፣ ፔንሲልቬንያ ዩኒቨርሲቲ ከሀገር ውጪ ያስተማረባቸው ቦታዎች ሲሆኑ በርካታ ተማሪዎችም ማፍራት ችሏል፡፡
የተለያዩ ቦታዎች ማስተማር ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የትምህርት ዓይነቶችንም በማስተማር ይታወቅ ነበር፡፡ ከፍልስፍና እስከ ስነ-ምግባር፣ከሀይማኖት እስከ ስነ-ውበት፣ ከወንድማማችነት እስከ ነፃነት በርካታ ፍልስፍናዎችን ማጋራት ችሏል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን ካተረፉ ዝነኞች ውስጥ በአሜሪካ ከዋነኞቹ የፖለቲካ ፈላስፋ መሀል ጆሴፍ ኮን እንዲሁም የሂውማን ራይትስ ዎች ፕሬዘዳነት ኬኔት ሮፍ ከፕሮፌሰሩ ተማሪዎች ውስጥ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ፕሮፌሰሩ ገና በወጣትነታቸው በኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ወቅት ታዋቂ ምሁር ከነበሩት ውስጥ አንዱ ነበር፡፡ በብዕር ተጋድሎአቸው፣ በጥቁሮች መብት ጋር ባለው አቋም፣ በአንባቢነቱ በምሁርነቱ ዙርያ የሚያሻማ ሀሳብ ባይኖርም በኋላ በመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ(መኢሶን) ፓርቲ ውስጥ በመታቀፍ አባል ሆኖ ለሀገሩ ያበረከተው ፖለቲካዊ አስተዋፅኦ አብሮ ይነሳል፡፡
ፕሮፌሰሩም ቢሆን ከታላላቆቹ ፈላስፎች ውስጥ የፕሌቶ፣የማርክስ እና ሄግልስ አድናቂ ሲሆኑ ከሀገር ውስጥ ምሁራን እነ ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ እና መንግስቱ ለማ ስራዎችን ማንበባቸውን እና መውደዳቸውን ሳይሸሽጉ ለስነ-ፅሁፍም ከፍተኛ ፍቅርና ክብር እንዳላቸው ይናገራሉ፡፡
ከማስተማር እና የዩኒቨርሲቲ ህይወት ባሻገር በተለያዩ ዘመናት በጦርነት ሰበብ በርካታ የሀገር ቅርሶች፣ የቤተክርስትያን እና የሀገር መዛግብት፣መስቀል እንዲሁም የብራና መፅሐፍቶችን ወደ ሀገር ውስጥ ለመመለስ ታስቦ በተቋቋመው ተወሰዱ እና የተዘረፉ የኢትዮጵያ ቅርሶችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስመለስ በነበረው ኮሚቴ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ከፍተኛ ሙግት በመግጠም እና በማሳመን የተወሰኑትን ሀብቶች በጊዜው ማስመለስ ከቻሉ የኮሚቴ አባላት ውስጥ አንዱ አንድሪያስ እሸቴ ናቸው፡፡
የአድዋ ጦርነት መቶኛ ዓመት መታሰቢያ በሚከበርበት ወቅትም አስተባባሪ የነበሩ ሲሆን አድዋ አባቶቻችን ከሰሩዋቸው ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ሳይሆን መላ ጥቁርን የሚያኮራ ታሪክ እንደሆነ ፈላስፋው በፅኑ የሚያምኑበት ነው፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በ1995 ህገ-መንግስት በሚሻሻልበትና በሚረቅበት ወቅት የህገ-መንግስት እና አስተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪ አባል በመሆን አገልግለዋል፡፡ በቦርዱም ውስጥ ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ እንደነበራቸው ይነገርላቸዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት የሰብአዊ መብቶች መታሰቢያ ፕሮጀክት ጊዜያዊ ቦርድ ሊቀ-መንበር እና አባል በመሆን ፓን አፍሪካንነትን በፅኑ ከሚያቀነቅኑ ምሁር ውስጥ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡ እንዲሁም የጣና ፎረም ከፍተኛ ደረጃ መድረክ ሊቀ-መንበር በመሆን እና የፌዴሬሽን መድረክ ቦርድ አባል በመሆን አገልግለዋል፡፡
ከጽሑፎቹ መካከል ስለ “ወንድማማችነት” የጻፈው ድርሰቱ በኢትዮጵያ በተግባራዊ ሥራው ውስጥ ትልቅ ሚና የተጫወተ ይመስላል። ከሦስቱ አስተሳሰቦች፣ “ነፃነት፣ እኩልነት እና ወንድማማችነት”፣ የምዕራቡ ዓለም የፖለቲካ ፈላስፋዎች “ነፃነት እና እኩልነት” ላይ ያተኮሩ እና “ወንድማማችነትን” ችላ ብለዋል በኢትዮጵያ የብሄር ፌደራሊዝም አውድ ውስጥ “ወንድማማችነት” የሚለውን ሃሳብ የጋራ ቋንቋ እና ባህል ላላቸው ብሄረሰቦች መተግበር አስተማማኝ ይመስላል።
“ብሔርተኝነትን” በ “የጎሣ ማንነት” በመተካት የወንድማማችነት ምሳሌ በመሆን ብሔርተኝነትን የሚመለከት ተመሳሳይ መከራከሪያ ማቅረብ ይቻላል።
ፕሮፌሰሩ ከስራ ህይወታቸው ባሻገር የቅርብ ወዳጆቻቸው ሲገልጧቸው አንድሪያስ አንባቢና ሙሉ ፈላስፋ ነው፡፡ የምትተማመኑበት ጓደኛ፣አዋቂ እና ተጫዋች ነው፡፡ ስስ የሆነ ነፍስ አለው የተጎዳ ሰው ካየ በዕንባ ሀዘኑን ይገልፃል፡፡ ደግና ለሴቶች መብት አብዝቶ የሚጨነቅ ሰው ነው ብለው ይገልፁታል ወዳጆቹ፡፡ በኢትዮጵያ ቁልፍ የታሪክ ሁነቶች ውስጥ ታዛቢ ብቻ ሳይሆኑ ቁልፍ ተሳታፊም ነበሩ፡፡
ፕሮፌሰር የግል ህይወቱ በጥልቅ ንባብና ልምድ የዳበረ፣ ያመነበትን የሚኖር ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ ነው በማለት የስራ ባልደረቦቹ ይገልፁታል፡፡ አንድሪያስ ከወለደው ልጁ አሉላ አንድሪያስ በተጨማሪ የአባት ፍቅር እየሰጠ ያሳደጋቸው የቀድሞ ባለቤቱ የእሙዬ አስፋው ሁለት ልጆችን ታጠቅ እና አደይን ጨምሮ የሶስት ልጆች አባት ነበር፡፡
(Via ተወዳጅ ሚዲያ)
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring