በአንካራ በሶማሊያ እና ኢትዮጵያ መካከል በመካሄድ ላይ ያለው ቀጥታዊ ያልሆነ ውይይት ዛሬም መቀጠሉ ተገለጸ!
በአንካራ በሶማሊያ እና ኢትዮጵያ መካከል በመካሄድ ላይ ያለው ውይይት ዛሬ ነሃሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም እንደቀጠለ መሆኑ ተገለጸ፣ የሁለቱም ሀገራት ተወካዮች ፊት ለፊት ተገናኝተው አለምምከራቸውም ተጠቁሟል።በትላንትናው ዕለት ነሃሴ 6 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሁለቱ ሃገራት መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ለመፍታት ያለመ ሁለተኛ ዙር ንግግር በቱርክዬ አንካራ መጀመራቸው ይታወቃል።
የሁለቱም ሀገራት ተወካዮች ፊት ለፊት ሳይገናኙ በቱርክዬ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን አስተባባሪነት ውይይታቸውን እያካሄዱ እንደሚገኙ የቱርክ የዜና ወኪል አናዶሉ በዘገባው አስታውቋል።
የቱርኩ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁለቱንም ተደራዳሪዎች በተናጠል በማወያየት ልዩነቶቻቸውን እንዲያጠቡ ጥረት እያደረጉ ነው ሲል ዘገባው ጠቁሟል፤ ትላንት ነሃሴ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ሃካን ፊዳን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታየ አቅፀስላሴ እና ከሶማሊያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አህመድ ሞአሊም ፈቂ ጋር መምከራቸውን ዘገባው አመላክቷል።ከሩሲያ ቱዴይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ ውይይቱ መልካም ነገር ይዞ ይመጣል ብለው እንደሚጠብቁ ገልጸዋል፤ ቱርክየ እየተጫወተች ያለው ዲፕሎማሲያዊ ሚናን አወድሰዋል።
የቱርክዬ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶሃን ከኢትዮጵያ ጨ/ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) እና ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ ጋር በስልክ መወያየታቸው መዘገቡ ይታወሳል።የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን ነሐሴ 4 ቀን ከጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ (ዶ.ር) ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከር እና ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር የገባችበትን ውዝግብ በሰለማዊ መንገድ ለመፍታት መምከራቸው ተገልጿል።
Via Addis_Reporter