የሰው ልጅ ያለ አጥንት፣ መገጣጠሚያ እና ተያያዥ የሰውነት አካላት ቆሞ መራመድም ሆነ መቀመጥ፣ መነሳት በጥቅሉ መንቀሳቀስ አይችልም።
የሰውነትን ክብደት ሙሉ ለሙሉ የሚሸከመው አጥንት ሲሆን በዚህም በዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ አጥንት ላይ ከፍተኛ ጫና ከመብዛቱ ባለፈ በተለያዩ አደጋዎች ሳቢያ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ አደጋ ይደርስበታል።
ይህንን ተከትሎ የአጥንት ጤና ችግሮች በርካታ ናቸው፡፡
ከእነዚህ ውስጥ ጥቂቶችን እንመልከት፡-
፨ በአደጋዎች ምክንያት የሚመጣ የአጥንት ስብራትና የመገጣጠሚያ አካላት ውልቃት – የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በዋናነት በትራፊክና በግንባታ ቦታ በሚደርሱ ልዩ ልዩ አደጋዎች ሳቢያ የሚከሰት ነው።
፨ በተጨማሪም በመውደቅ፣ በዱላና በድንጋይ በመመታት፣ በጦርነትና በግጭት ጊዜ፣ በሥራ ቦታ በማሽን በመቆረጥ፣ አጥንት ሲሳሳ በትንሽ ምክንያት መሰበር ሌላም ሌላ የአጥንት ስብራትና የመገጣጣሚያ አካላት ውልቃት የሚያጋጥሙበት ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው።
፨ ሌላው በቂ የፀሐይ ብርሃን ካለማግኘት ጋር ተያይዞ በቫይታሚን ዲ እጥረት ሳቢያ የአጥንት መሳሳት፣ መጣመም፣ የተለያዩ ቦታዎች ላይ መሰበር ነው፡፡
፨ እንዲሁም የእግር መቆልመምና መጣመም፣ የጀርባ መንጋደድ፣ የጉልበት መጣመም፣ የቅርጽ መበላሸትና ሌሎች በተፈጥሮ የሚመጡ የአጥንት ህመሞች በስፋት ይስተዋላሉ።
፨ የአጥንት ካንሰር እና እጢም የአጥንት የጤና ችግሮች ናቸው፤ የአጥንት ካንሠር ልክ እንደሌሎች የካንሰር አይነቶች በጊዜ ከተደረሰበት ስለሚድን፤ ችግሩ የገጠማቸው ሰዎች ህመሙ ስር ሳይሰድ በጊዜ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ህክምና መከታተል ይኖርባቸዋል።
፨ ሌላው ከባህላዊና ዘመናዊ የስፖርት ጨዋታዎች ጋር ተያይዞ የሚመጡ እና ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ የሚመጡ የአጥንት የጤና ችግሮች አሉ።
በአጠቃላይ አጥንት ለተለያዩ ጉዳቶች የተጋለጠ በመሆኑ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ለአጥንት ጥንካሬ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ለአጥንት ጥንካሬ የሚጠቅሙ ሙዝ፣ ወተት እና የወተት ተዋፅኦዎች እንዲሁም አረንጓዴ ቅጠላ ቅጠሎችን የመሳሰሉ በካልሺየም የበለፀጉ ምግቦችን አዘውትሮ መመገብ ይመከራል ፡፡
ከዚህ በተቃራኒው በብዛት የካርቦን ይዘታቸው ከፍ ያለና ጣፋጭ ለስላሳ መጠጦችን ጨምሮ፣ ለረጅም ጊዜ የሚወሰዱ መድሀኒቶችን (ስቴሮይድ፣ ወዘተ) የሚጠቀሙ፣ በርካታ አልኮል የሚጠጡና ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ለአጥንት መሳሳት፣ መሰበር እና መበስበስ ሊጋለጡ ይችላሉ።
ስለዚህ ማንኛውም ሰው ጥንቃቄ የተሞላበት እንቅስቃሴ ማድረግና አጥንትን የሚያጠነክሩ ምግቦችን ደጋግሞ መመገብ አለበት።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ገጽ
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring