የሁለተኛው ዙሩ የውሃ ሙሌት ሲጠናቀቅ “ኢትዮጵያ ኒኩሌር ታጠቀች” በሚል የገባቸው መሰከሩ። ያልገባቸው አገር፣ ፕለቲካ፣ መጪ ትውልድና ብሄራዊ ጥቅም አደበላለቀው አሁን ድረስ ይኮንናሉ። ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች አድረው ያተራምሳሉ። አብይ አህመድ ሰሞኑን “አብዣኛው ህዝብ የህዳሴው ግድብ ቁም ነገሩና ስትራቴጂው ገብቶት ቢሆን ኖሮ ይህን ያህል መስዋዕትነት አንከፍልም ነበር” ሲል በደስታ ውስጥ የተከፍለውን ዋጋ ይፋ አድርገውዋል። ” ከሰማነው ያልሰማነውን ወደፊት ጊዜ የሚገልጸው ብዙ ጉዳይና መኖሩን አመልክተውናል” ሲሉ ንግግራቸውን የሰሙ እየገለጹ ነው።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአፍሪካ ሁሉ ኩራት፣ ብርታትና መለወጥ እንችላለን እንዲሉ የሚቀሰቅስ ኃይል ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሲገልጹ እዛው እግድቡ ላይ ሆነው 3ኛው እና 4ኛው ተርባይኖች ሥራ መጀመራቸውን ሲያበስሩ ነው።
” አብይ አህመድ የህዳሴው ግድብ ለግብጽ ተላልፎ እንዲሰጥ የመፍቀድ ያህል ሂኖንየተዘጋጀውን ሰነድ የኢትዮጵያ ልዑካን እንዲፈርሙ በስልክ ትዕዛዝ ሰጡ” ሲሉ የዲፕሎማት ምንጮች ሹክ እንዳሉዋቸው የገለጹ አሁን ደርስ አይናቸውን በጨው እንዳጠበቡ ነው። “ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአባይን ግድብ ሸጡ” በሚል በገሃድ ሲናገሩ የነበሩ አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ዛሬ ድረስ ህዝብ ፊት ቆመው ይናገራሉ።
መከላከያ ሰራዊት ለግድቡ ግንባታ ከሲሚንቶ ጀምሮ ማናቸውም ዕቃዎች ሲላኩ ፈንጂ ላይ እየተራመደ፣ ሊያጠፉ ከሚመጡት የተሸጡ አድፋጮች ጋር እየተፋለም፣ በደምና አጠንቱ ህዳሴው እወን እንዲሆን የሰራው ታሪኩን የተጻፈው ምትክ በሌለው በነብስ ነው። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ መቀነቱን ፈቶ ማህተቡን በማተም ነው። ለጠላት አድረው ሲጎትቱና ሲዋጉን የነበሩ፣ በሴራ ሲተባበሯቸው የነበሩ፣ በማህበራዊና በዪቲዩብ ሚዲያዎች፣ እንዲሁም በውጭ ሃይሎችና አገራት እየትቀለቡ አገራቸው ላይ መርዝ ሲረጩ በነበሩ የአየር ላይ ባንዳዎች ሳይደናቀፍ ተግባር የሆነው የህዳሴው ግድብ ለመላው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ኩራት ሆኗል።
ስንዴውም፣አረንጓዴ አሻራም፣ኮሪደር ልማቱና ህዳሴ በዋዛ ፈዛዛ ሊሳካ እንደማይችልና አድካሚ ነገር መሆኑን በማወቅ ትብብርና መደመር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው፤ ህዳሴና አረንጓዴ ዐሻራ ከመንግሥት ጋር ምንም ትስስር የለውም፤ግድቡ ቀጥታ ከኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ፣ቀጣይነት ካለው የትውልድ ቅብብሎሽ የሀገርን ህልውና ከማስቀጠል ጋር የሚያያዝ መሆኑን አስረድተዋል። ከስር ከአዲስ ዘመን የተዋስነውን ንግግራቸውን ያንብቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስለ ግድቡ የሥራ ሂደትና አሁናዊ ቁመና በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት፤በአሁኑ ጊዜ አራት ተርባይን ኃይል እያመነጨ ሲሆን፤ ከአራት ወር በኋላ ተጨማሪ ሦስት ተርባይኖች ሥራ ይጀምራሉ።ይህ በአፍሪካ ግዙፉ ግድብ የአፍሪካ ሁሉ ኩራት፣ ብርታትና መለወጥ እንችላለን እንዲሉ የሚቀሰቅስ ኃይል ነው።
እስከ መጪው ታኅሳስ ወር ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ70 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ ውሃ መያዝ እንደሚችልም አመልክተዋል።
በታኅሳስ ወር የግድቡ የሲቪል ሥራ ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራው በሚቀጥሉት ስድስት ወራት መልክ እየያዘ እንደሚሄድና አጠቃላይ የግድቡ ሥራ ደግሞ የዛሬ ዓመት ገደማ የመጠናቀቅ ምዕራፍ ላይ እንደሚደርስ ጠቁመዋል።
ህዳሴን ከሞላ ጎደል ጨርሰነዋል፤ ከእንግዲህ በኋላ የገንዘብና የቴክኒክ እንብዛም ስጋት የለንም ያሉት ዐቢይ (ዶ/ር)፣ሊያደናቅፉን ያሰቡ ሰዎች ገለውን፣ሰዎችን አፍነው፣ጉዳት አድርሰው ሊሆን ይችላል ግን አላቆሙንም ሥራውን ጨርሰነዋል ብለዋል።
ህዳሴው የዛሬ አምስት ዓመት ምንም ውሃ አልያዘም፣ግድቡም የአሁኑ ምልከታና ዕይታ አልነበረውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ዛሬ የህዳሴ ግድብ ወደ ኋላ ከ205 ኪ.ሜ በላይ ውሃ የያዘ ሲሆን፤ ወደታች ጥልቀቱ 133 ሜትር ደርሷል ብለዋል።
ህዳሴ ከንግግር በላይ በመሆኑ ብዙዎች አይተው፣ ነክተው ካላወቁት በቀር ምን ያህል ግዙፍ ሥራ እንደሆነ መገንዘብ እንደማይችሉ ጠቅሰው፤ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሃሳብና ገንዘብ እንዲሁም ጊዜ ብቻ አልገነባውም፤ በደምም ጭምር የተገነባ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ባለፉት አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ በተለያየ ግንባር ተይዛ ሳለች 15 ሺህ የሚጠጉ የተለያዩ ቡድኖችን በህዳሴ ጉዳይ ተሰማርተዋል ያሉት ዐቢይ (ዶ/ር)፣ ሲሚንቶ ከማምረት ጀምሮ አጓጉዞ ቦታው ላይ እስኪደርስ የተለያየ ስም ያላቸው የተገዙ ሰዎች ሥራው አሁን ያለበት ደረጃ እንዳይደርስና እንዳይቋጭ ብዙ ጊዜ ገንዘብና ህይወት አጥፍተዋል ብለዋል።
ላለፉት ሦስት ዓመታት ሲሚንቶን ከደርባ አንስቶ ህዳሴ ለማድረስ መከላከያ መንገድ እየጠገነ፣ፈንጂ እየለቀመ፣እየተዋጋ ግድቡ እንደተሠራ ጠቅሰው፤ ህዳሴን ብዙ ሰውተንበት፣ደምተንበት እና ደክመንበት ነው የሠራነው ሲሉ ገልጸዋል።
ህዳሴ ላይ የከፈልነውን ዋጋ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ቁም ነገሩን፣ ስትራቴጂክ እሳቤውን በወጉ ተገንዝቦ ቢሆን በዛ ደረጃ ዋጋ ባልከፈልን ነበር ሲሉም ተናግረዋል።
እንደሀገር ያለ የሌለ አንጡረ ሀብታችንን ሰብስበን፣ ለምነን፣ ዜጎች ያላቸውን አዋተው ግድቡ መሠራቱን ገልጸው፤ ሌሎች ደግሞ ያላቸውን ሀብት፣ጊዜ አውጥተው ዓለምአቀፍ ጫና ለመፍጠር፣በሀገር ውስጥ ለማስታጠቅ ሀብት መድበው የሚሠሩ መኖራቸውንም አስረድተዋል።
በዚህ ሁሉ ውስጥ ነው ዛሬ ህዳሴ አስደማሚ በሆነ መንገድ ውሃውን ይዞ ያየነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያዊያን ከወትሮው በተለየ መንገድ መደማመጥ፣ መናበብ፣ለጋራ ዓላማ አብሮ መቆም ባለን ጉልበት፣አቅምና ገንዘብ ሁሉ መተባበር አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ስንዴውም፣አረንጓዴ አሻራም፣ኮሪደር ልማቱና ህዳሴ በዋዛ ፈዛዛ ሊሳካ እንደማይችልና አድካሚ ነገር መሆኑን በማወቅ ትብብርና መደመር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው፤ ህዳሴና አረንጓዴ ዐሻራ ከመንግሥት ጋር ምንም ትስስር የለውም፤ግድቡ ቀጥታ ከኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ፣ቀጣይነት ካለው የትውልድ ቅብብሎሽ የሀገርን ህልውና ከማስቀጠል ጋር የሚያያዝ መሆኑን አስረድተዋል።
በድህነት ለተሳለቁብን፣ከዚያ ካላችሁበት አረንቋ አትወጡም ፣የብልጽግናን ሽታ አታዩትም፣መልማት አይቻላችሁም ማለታቸውን በመግለጽ፤ መሻገር አይሆንላችሁም፣ለእናንተ የተፈቀደና የተገባ አይደለም ላሉን ግለሰቦችና ቡድኖች ሕዝብና ሀገር ከወሰነ ምን ሊያመጣ እንደሚችል ህዳሴና አረንጓዴ ዐሻራ ማሳያ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ አድጋ፣ ተለውጣ፣ በልጽጋ ወንድሞቻችን እንዲራቡ የሚፈቅድ እሳቤ ካለን ብልጽግና አልገባንም ማለት ነው ሲሉ ጠቅሰው፤ ብልጽግና ከገንዘብ በላይ ሆኖ ማሰብ ሲሆን፤ እሳቤው ገንዘብ ሰብስቦ ምግብ መብላት ሳይሆን የብዙዎችን ህይወት መቀየር መሆኑን ገልጸዋል።
ህዳሴ የአፍሪካ ሁሉ ኩራት፣ ብርታት መለወጥ እንችላለን እንዲሉ የሚቀሰቅስ ኃይል መሆኑን ገልጸው፤ ህዳሴ ሱዳንና ግብጽ በጣም መደገፍ ያለባቸው ግድብ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በተርባይን ከሚያልፈው ውሃ በተጨማሪ በግድቡ ማስተንፈሻ በሮች በአንድ ሰከንድ 2 ሺህ 800 ሜትር ኪዮብ ውሃ ወደ ተፋሰስ ሀገራት መልቀቅ መጀመሩን ገልጸው፤ ውሃው የጋራ ሀብታችን በመሆኑ እንደ ሀገርና ሕዝብ የሚገባንን ያክል ተጠቅመን የሚገባቸውን ያክል ደግሞ ለወንድሞቻችን ማካፈል ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ማርቆስ በላይ