ግብፅ ወታደሮቿንና ጦር መሳሪያዎችን በሶማሊያ ማሰማራት ጀምራለች
የግብፅ ወታደሮች፣ መሳሪያዎችና ወታደራዊ አውሮፕላኖች የሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ መድረሳቸው ተገለጸ። ይህ ሂደት 10 ሺህ የሚደርሱ የግብፅ ወታደሮችን በሶማሊያ ለማሰማራት የታቀደው አካል ነው።
ወታደሮቹ በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር አካባቢ ማለትም በጌዶ፣ በሂራን እና በባይ ባኮል ስፍራዎች ላይ እንደሚሰፍሩ እየተገለጸ ይገኛል።
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ እና የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በካይሮ በቅርቡ የተፈራረሙትን የመከላከያ ስምምነት ተከትሎ c-130 የተባሉ ሁለት የግብፅ ወታደራዊ አውሮፕላኖች በአደን አዴ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አርፈዋል ተብሏል።
ግብጽ ወታደሮቿንና የጦር መሳሪያዎችን በሶማሊያ ያሰማራችው በቅርቡ በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ መካከል የተፈረመው የባህር በር የመግባቢያ ስምምነትን ተከትሎ በቀጠናው ውጥረት በነገሰበት ወቅት ነው።
የሁለቱ ወታዳራዊ ትብብር በፈረንጆቹ 2025 የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ በሶማሊያ (አትሚስን) ለመተካት በታቀደው በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ ተልዕኮ AUSOM አካል መሆኑ ቢገለፅም – በሶማሊያ የግብፅ ጦር መገኘት ታላቁ የህዳሴ ግድብን በመቃወም ኢትዮጵያ ላይ ዙሪያ ለቋጠረችው ቂም እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ለሚኖረው ፍላጎቶች እንደ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ተደርጎ ይወሰዳል ሲል የፑትላንዱ ጋሮዌ ኦንላይን መጣጥፍ ይጠቁማል – ይህም ከግብፁ ሰሞንኛ እንቅስቃሴ ጀርባ በርካቶች የሚስማሙበት መነሾ ነው።
(እስሌይማን አባይ)
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring