የውጭ ሀገር ዜጎች እና ድርጅቶች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለይዞታ የሚሆኑበት አግባብ ለመደንገግ የሚውል ረቂቅ አዋች በዝግጅት ላይ ነው ተብሏል።
ይህን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት በወላይታ ሶዶ ከተማ በረቂቅ አዋጁ ላይ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።
ረቂቅ አዋጁ ወደ ሀገራችን ካፒታል በመሳብ እዚህ ተሰርቶ ሌሎች ሀገራት የሚፈሰውን መዋዕለ ንዋይ በመሳብ ብሎም ሀገሪቱ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ሁኔታዎችን የአፍሪካ መዲና መሆኗን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ሲሉ የፍትህ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳጋቶ ኩምቤ በበኩላቸው ረቂቅ አዋጁ አዳዲስ ባለሀብቶች በመሳብ እውቀትና ልምዳቸውን ብቻ ሳይሆን ሀብታቸውንም በኢትዮጵያ እንዲያፈሱ አዲስ እድል ይፈጥራል ብለዋል።
በረቂቅ አዋጁ እንደተጠቀሰው፦
አንድ የውጭ ሀገር ባለይዞታ በአንድ ጊዜ ከሦስት በላይ መኖሪያ ቤቶች ወይም ባለይዞታነት መብት ሊኖረው እንደማይችል ይጠቅሳል።
በተጨማሪም የውጭ ሀገር ዜጋ ወይም ድርጅት ለአንድ መኖሪያ ቤት ግንባታ የሚሰጥ የሊዝ መሬት፦
- ከፍተኛ መጠን
- የሚይዘው የአንድ መኖሪያ ቤት አጠቃላይ ወለል ስፋት እና ህንጻ ከፍታ፤
- የውጭ ሀገር ዜጋ ወይም ድርጅቶች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት መሆን የማይችሉባቸው ልዩ ቦታዎች ወይም የድንበር አከባቢዎች ዝርዝር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት ይወሰናል ተብሏል።
የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ሀገር ሰዎች የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅድ ሕግ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአንድ መድረክ መጥቀሳቸው አይዘነጋም።
Vua Addis_Reporter