የህጻናት ዳሌ ዉልቃት ልጆች ሲወለዱ ጀምሮ ወይንም ከተወለዱ ቡሃላ የሚከሰት የዳሌ መገጣጠሚያ ዉልቃት ሲሆን ይህም የታፋ አጥንት ኳስ ከዳሌ ጣራ ዉጭ ሲቀመጥ ነዉ፡፡
የዳሌ መገጣጠሚያ ባንድ በኩል ብቻ ወይንም በሁለቱም በኩል ወልቆ ሊገኝ እንደሚችልም ተገልጿል፡፡
አሁን ላይ ችግሩ በሃገራችን በስፋት እየተስተዋለ መጥቷልም ተብሏል፡፡
የዚህን የህጻናት የዳሌ ዉልቃት በኢትዮጵያ ዉስጥ ምንያክል ሰፊነዉ የሚለዉን ለማወቅ እና ስርጭቱን ለማወቅ ከጥቁር እንበሳ፤ ከቅዱስጳዉሎስ ሆስፒታል እና ከአበበች ጎበና ጋር በመተባበር ጥናት እያካሄዱ መሆኑን በኪዩር ኢትዮጵያ የህፃናት ሆሰፒታል የአጥንት ስፔሻሊስት እንዲሁም የህፃናት አጥንት ሰብ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ቴዎድሮስ ጥላሁን ነግረዉናል፡፡
ለመሆኑ የዳሌ ዉልቃት እንዲከሰት የሚያደርጉ አጋላጭ ምክንያቶች ምንድናቸዉ?
-የህጻንን እግር ጠፍሮ መያዝ ወይንም በማይመከር መንገድ መጠቅለል ፡፡
-በቤተሰብ ዉስጥ ተመሳሳይ ችግር ካለ
-በወሊድ ወቅት የልጅ አመጣጥ በመቀመጫዉ ወይንም በእግር ሲሆን ለዚህ ችግር ይጋለጣሉ ተብሏል፡፡
ብዙጊዜ ለዚህ ችግር የመጀመሪያ ልጆች እና ሴት ልጆች ተጋላጭ ናቸዉም ተብሏል፡፡
ልጆችን በልጅነታቸዉ አዝሎ ወይንም አቅፎ አለመያዝ ለችግሩ መከሰት አስተዋፅ አለዉም ብለዉናል፡፡
የበሽታዉ ምልክቶች
-የህጻናት ዳሌ ዉልቃት ልጆች መራመድ ከሚጀምሩበት እድሜ በፊት ወላጆች የሚያት እና የሚለዩበት ምልክት የለም፡፡
-ህመም ባለመኖሩ እናቶች ልጆቻቸዉን ሲያጥቡ የተለየ ሁኔታ ሊያስተዉሉ ይችላሉ ከተለመደዉ ዉጭ የአጥን መገጣጠሚያ ድምፅ፡፡ ከዚህ ባለፈ፤-
-የወለቀዉ ዳሌ ከደናዉ ጋር ሲነጻጻር እንቅስቃሴዉ የተገደበ ይሆናል
-መራመድ ከመጀመራቸዉ በፊት ማነከስ ወይንም በጣት የመሄድ ሁኔታ ይፈጠራል
-የእግር መበላለጥ ይፈጠራል
ህጻናት የዳሌ ዉልቃት እንዳለባቸዉ እንዴት ማወቅ ይቻላል?
ዶክተር ቴድሮስ ሁሉም ህጻናት ሲወለዱ የዳሌ ምርመራ ያስፈልጋቸዋል ብለዉናል፡፡
-እድሜያቸዉ ከስድስት ወር በታች ለሆኑ ህጻናት ዉልቃቱ እንዳለ የሚታወቀዉ ሃኪም ዳሌያቸዉን በማንቀሳቀስ በሚያደርገዉ ምርመራ እና የዳሌ አልትራሳወንድ ነዉ፡፡
እድሜያቸዉ ከስድስት ወር በላይ ከሆነ ደግሞ በራጅ (x-ray) ይታወቃል ተብሏል፡፡
የዳሌ ዉልቃት ለገጠማቸዉ ህጻናት የሚደረግ ህክምና
-ከስድስት ወር በታች ለሆኑ ህጻናት የዳሌ ድጋፍ ወይንም በህክምና አጠራሩ pavlic harness በማድረግ ብቻ ዉልቃቱን ወደቦታዉ መመለስ ይቻላል ብለዋል፡፡
-ሁለተኛዉ የህክምና አይነት የጄሶ ህክምና ነዉ፡፡
– የመጨረሻዉ ህክማና የሚሆነዉ ከባድ እና ረዥም ጊዜ የሚወስድ ሲሆን ቀዶጥገና ነዉ ተብሏል፡፡ይህ ህክምና አጥንቱን እስከ መስበር ሊደርስ እድሚችል ተጠቁመዋል፡፡
እንዴት መከላከል ይቻላል?
ከስድስት ሳምንት እስከ ስድስት ወር ያሉ ህጻናት ከላይ የተገለጹት አጋላጭ ሁኔታዎች ከነበሩ አካላቸዉን መስመርመር እና ከተፈጠረ በቶሎ ማሳከም ይገባል፡፡
ይህ መሆኑ የዳሌ መገጣጠሚያቸዉ ጤናማ ሆኖ እድገቱን እንዲቀጥል እና በቶሎ ችግሩን ለመቅረፍ ስለሚያግዝ ነዉ ሲሉ በኪዩር ኢትዮጵያ የህፃናት ሆሰፒታል የአጥንት ስፔሻሊስት እንዲሁም የህፃናት አጥንት ሰብ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ቴዎድሮስ ጥላሁን ነግረዉናል፡፡
*ከዚህ ችግር መዳን የሚቻል ነዉ በቶሎ ከታወቀ እና አስፈላጊዉ እርምጃ ከተወሰደ መሆኑን ዶክተር ቴዎድሮስ ጥላሁን ነግረውናል፡፡
በልዑል ወልዴ
ነሐሴ 07 ቀን 2016 ዓ.ም
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring